No summary available.
ሐምል 03 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ - ጠበቃ ሜላት ወርቅ ኃይለ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ መዘምር መክብብ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 "ን" መሰረት አድርጎ የቀረበውን የግል የስራ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የተጠሪ ክስ ይዘት ሲታይም ከአመልካች ጋር የመሰረቱት የስራ ውል ግንኙነት ያለጥፊት የተቋረጠባቸው መሆኑን ገልፀው የአመልካች እርምጃ ሕገ ወጥ ነው ተብል ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስም ተጠሪ ከስራ የተሰናበቱት በድርጅቱ ግቢ ውስጥ ድብደባ ፣ ጾታዊ ትንኮሳ እና የጠብ አጫሪነት ተግባር በመፈፀማቸው ስለመሆኑ ገልፆ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በሁዋላ ጉዲዩን መርምሮ ተጠሪ በአመልካች ኤዱፑ ካምፔ እና ለሰራተኞች መኖሪያነት በተሰራው ግቢ ውስጥ /በስራ ቦታ/ የድርጅቱን ሰራተኛ በመደብደብና የዛቻ ተግባር መፈፀማቸው መረጋገጡንና ለዚህም ተጠያቂ መሆናቸውን ገልፆ የአመልካች እርምጃ ሕጋዊ ነው በማለት የተጠሪን ክስ ውድቅ አድርጎታል። በዚህ ወሳኔ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ተጠሪ የድብደባ ተግባሩን የፈፀሙት ከስራ ሰዓት ውጪ በመሆኑ ድርጊቱ በስራ ቦታ ላይ እንደደረሰ የሚቆጠር አይደለም በሚል ምክንያት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሙለ በሙለ በመሻር አመልካች ለተጠሪ የስድስት ወር ውዝፍ ደመወዝ ከፍል ወደ ስራ እንዱመልሳቸው ተብል ተወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤተታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪ ለስራ ስንብቱ ምክንያት የሆነውን የድብደባ ተግባር ስለመፈፀማቸው ከመረጋገጡም በላይ ድርጊቱ የተፈፀመው በስራ ቦታ ላይ ስለመሆኑ በማስረጃ ተረጋግጦ እያለ ድርጊቱ ከስራ ሰዓት ውጪ የተፈፀመ ተግባር ነው በሚል ጠባብ ምክንያት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ መሻሩ ያላግባብ ነው በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖበት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪም ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በሰጡት መልስ በይግባኝ ሰሚው ችልት የተሰጠው ውሳኔ በማስረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገርና አግባብነት ያለውን ሕግ መሰረት ያደረገ በመሆኑ ሉጸና ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ የተደረገው ተጠሪ አምባጓሮ ፈጥሮ የስራ ባልደረባውን መደብደቡን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተቀብል ድብደባው የተፈፀመው ተጠሪና የግል ተበዲይ አመልካች ባዘጋጀላቸው የስራና የመኖሪያ ግቢ ካምፔ ቢሆንም ድብደባው የተከናወነው ከስራ ሰዓት ውጪና በመፀዲጃ ቤት አካባቢ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27(1(ረ)) ስር የተደነገገውን አያሟላም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ውድቅ ማድረጉና ወደ ስራው ይመልሰው የመባለን አግባብነት ለማጣራት በሚል ነው።
ከሥር ፍ/ቤት መዝገብ መረዲት የተቻለው ተጠሪው የአመልካች ድርጅት ሰራተኛ ላይ የስራ ቦታ በሆነው የአመልካች ካምፔ እና በስራ ጉዞ ላይ የድብደባ ፣ የዛቻ ተግባር መፈጸማቸውን ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ የሰማው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያረጋገጠው ጉዲይ መሆኑንና ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ቢሆን የድብደባውና የዛቻው ተግባር በተጠሪ በመፈፀሙ ረገድ ከስር ፍርድ ቤት የተለየ ድምዲሜ የላለው መሆኑ ነው። በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት በተደረገው ክርክርም ተጠሪ የድብደባውን ተግባር ስለመፈፀማቸው ግልፅ የሆነ የክህደት ክርክር የላላቸው መሆኑን ተገንዝበናል። የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠው የተጠሪ ድርጊት የአዋጁ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/ረ የተደነገገውን ጥፊት አያሟላም ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰው የአመልካች ሰራተኛ የተደበደበችው ማታ ከመሆኑም በላይ የድብደባው ተግባር የተፈጸመው አመልካች ለሰራተኞቹ በመኖሪያነት ባዘጋጀው ቦታ መጸዲጃው አከባቢ ስለመሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ በሕጉ አነጋገር የስራ ቦታ እና ሰአት የሚለውን መለኪያ የሚሸፈን አይደለም በሚል ነው። አመልካች ሰዓቱም ሆነ ቦታው የስራ ቦታ ነው የሚል ክርክር አቅርቧል። የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድምዲሜን ተገቢነት ለመመርመር የተጠቃሹን ድንጋጌ ይዘትና ዓላማ በዝርዝር መመልከት ተገቢነት ይኖረዋል። የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27/1/ረ ድንጋጌ ይዘት ሲታይ፡- “ እንደጥፊቱ ክብደት በሥራው ቦታ አምባጓሮ ወይም ጠብ እጫሪነት ተጠያቂ መሆን ” ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ለማቋረጥ ከሚያስችለ ምክንያቶች አንደ ስለመሆኑ ያስገነዝባል። በዚህ ድንጋጌ ውስጥ ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ሐረግ "….በስራው ቦታ…." የሚለው ሲሆን ይኸው ሐረግ ሰራተኛው ስራውን በስራ ሰዓት የሚያከናውንበትን ቦታ ወይም የአሰሪውን ትዕዛዝ በስራ ላይ ሉያውል የተገኘበትን ቦታ ሁለ የሚያጠቃልል ስለመሆኑ ከአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 97 እና 4 ድንጋጌዎችን ይዘት በማገናዘብ የምንረዲው ጉዲይ ነው። ይህ ደግሞ አሰሪው ስራው በሚሰራበት ካምፔ ውስጥ ለሰራተኛው በመኖሪያነት የመደበውን ቦታ እና በዚህ ቦታ ሰራተኛው ያለበትን ሰዓት ጭምር ሁለ ሉጠቃልል እንደሚችል ከሕጉ መንፈስ መገንዘብ ይቻላል።
በመሆኑም ሰራተኛው በስራ ሰዓት ስራውን በሚያከናውንበት ቦታ ወይም የአሰሪውን ትዕዛዝ በስራ ላይ ሉያውል በተገኘበት ቦታ ላይ እንደጥፊቱ ክብደት በሥራው ቦታ አምባጓሮ ወይም ጠብ እጫሪነት ድርጊት መፈፀሙ ከተረጋገጠበት የስራ ውለን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ የሚያስችል ድርጊት ነው። የዚህ ድንጋጌ አይነተኛ አላማም በሥራ ቦታ ሰላም እንዱሰፍን በማድረግ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ነው ተብል ይታመናል። በመሆኑም ድንጋጌው ሉተረጎም የሚገባውም ይህንኑ የድንጋጌውን ዓላማ መሰረት በማድረግ ላሆን እንደሚገባም እሙን ነው።
በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ የአመልካችን ሰራተኛ መደብደቡ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠና በተጠሪም የታመነ ፍሬ ነገር መሆኑን ከመዝገቡ መረዲት ችለናል። ይህ የተጠሪው ድርጊት ከተጠቀሰው ድንጋጌ አንፃር ሲታይ የጠብ አጫሪነት ድርጊት መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። ከላይ በተደጋጋሚ እንደተገለጸው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ፍ/ቤት ተጠሪው የድብደባውን ድርጊት መፈፀማቸውን ተቀብል ድርጊቱ የተፈጸመው ከስራ ሰዓት ወጪ ነው በማለት የአመልካችን ክርክር ውድቅ ያደረገው በፍሬ ነገር ደረጃ ከተረጋገጠውና ከሕጉ መንፈስና አላማ ውጪ ነው። አንድ ሰራተኛ የአሰሪው ወይም የሥራ ኃላፉው ትእዛዝ በማክበር ካምፐ በሚገኝበት ቦታ መኖሪያ ተሰጥቶት በመኖር ላይ ባለበት ሁኔታ በዚሁ አካባቢ በድርጅቱ ሰራተኛ ድብደባ ከተፈፀመበት የድብደባውን ተግባር የፈፀመው ሰራተኛ ተግባሩን የፈፀመው በስራ ጊዜና ቦታ አይደለም ተብል ድምዲሜ ላይ መድረስ ሕጉ ሉያሳካ ያሰበውን ፤ በስራ አካባቢ ሰላምን በማስፈን ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ የሚለውን አላማ ያላገናዘበ ነው ከሚባል በስተቀር ላላ ትርጉም ሉሰጠው የሚገባ ሁኖ አላገኘነውም። ስለሆነም ተጠሪ የድብደባውን ተግባር የፈፀሙ ስለመሆኑና ድብደባውን የፈፀሙትም ለስራ ጉዲይ ከተጠሪ ጋር እንዱሄደ በአመልካች የታዘዙትን ሴት ሰራተኛ ቀኑን ሙለ ሲያስቸግሯቸው ውለው አሰሪው በስራው ቦታ ውስጥ ባዘጋጀው የሰራተኞች መኖሪያ ቤት መፀደጃ ቤት ሰራተኛዋ ቆይተው ሲወጡ ማታ ላይ መሆኑ የተጠሪን ድርጊት ጥፊት ከባድነት አመልካች ነው። ስለሆነም የተጠሪው ድርጊት የአዋጁን አንቀጽ 27/1/ረ የተመለከተውን ጥፊት አያሟላም ሲል የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት የደረሰበት ድምዲሜ ሕጉ ያስቀመጠውን የሰራተኛውን ግዳታ የሚመለከተውን ድንጋጌ እና የጥፊቱን አደገኛነት ከተጠቃሹ ድንጋጌ አይነተኛ አላማ አንፃር በአግባቡ ሳያገናዝብ መሆኑን ስለተረዲን ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
አመልካች ተጠሪን ያሰናበተው በሕጉ አግባብ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.