No summary available.
ሐምል 17 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪ አመልካቾችን ያሰናበተው በአግባቡ ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት አመልካቾች በከሳሽነት ቀርበው የተቀጠርንበት የሥራ ግዜ ሳይጠናቀቅ፣ የተመደብንበት የሥራ ባህሪ ቀጣይነት ያለው ሆኖ እያለ ተከሳሽ /አመልካች/ የኢፋዱሪ ትምህርት ሚኒስቴር በ2003 ዓ.ም የርቀት ትምህርት ተማሪዎችን እንዲይቀበለ መመሪያ አውጥቷል በሚል ምክንያት የሰራተኞች አቀናነስ ሥርዓትን በተመለከተ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ የተደነገገውን ሳይከተል በሕገወጥ መንገድ የሥራ ውል ያቋረጠ በመሆኑ የተለያዩ ክፍያዎችን እንዱከፍል ይወሰንልን በማለት ክስ አቅርቧል። ተጠሪ በበኩለ ትምህርት ሚኒስትር ባወጣው መመሪያ አዱስ ተማሪዎች እንዲንቀበል በመመሪያ የከለከለን በመሆኑ በድርጅቱ መዋቅርና የሥራ እንቅስቃሴ በከፉል፣ በቀጥታና በዘለቄታው እንዱቀንስና እንዱቀዘቅዝ አድርጓል። በዚህ ምክንያት አሁን ያለንን ተማሪዎች ለማስጨረስ የሚያስችለ መምህራኖችን ብቻ በማስቀረት ከሳሾችን በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ መሰረት ማስጠንቀቂያ በመስጠት አሰናብተናቸዋል። ስንብቱ ሕጋዊ በመሆኑ ከሳሾች የጠየቁትን ክፍያ የመክፈል ኃላፉነት የለብኝም በማለት ተከራክሯል። የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተጠሪ አመልካቾችን ከሥራ ያሰናበተው ስለሰራተኛ ቅነሳ በአዋጅ ቁጥር 377/96 የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ሳይከተል በመሆኑ ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው።
ስለዚህ ተከሳሽ /አመልካች/ ለከሳሾች /አመልካቾች/ የስድስት ወር ደመወዛቸውን ይክፈላቸው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ተጠሪ አስራ ዘጠኝ ሰራተኞችን ከሥራ በማሰናበት የወሰደው እርምጃ ካለት ሰራተኞች ከአስር ፏርሰንት በታች በሚሆኑት ላይ የተደረገ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 29 መሰረት የሰራተኛ ቅነሳ አለመኖሩን ያሣያል።
ተጠሪ የአመልካቾችን የሥራ ውል ያቋረጠው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 28 ንዐስ አንቀጽ 1/ሀ/ መሰረት በመሆኑ ስንብቱ ሕጋዊ ነው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካቾች ይህ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ጥቅምት 29 ቀን 2004 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል።
ትምህርት ሚኒስትር በ2002 ዓ.ም ያወጣው መመሪያ በጥቅምት ወር 2003 ዓ.ም ማሻሻያ ተደርጎበታል። በተመሣሣይ ሁኔታ የተባረረ ሰራተኛ ወደ ሥራው እንዱመለስና የስድስት ወር ክፍያ እንዱከፈለው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ወስኗል። ተጠሪ የሰራተኛ ቅነሳ አድርጌአለሁ ቢልም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 29 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት አላደረገም። ሰራተኛ ለመቀነስ የሚያስገደድ ሁኔታ አልተፈጠረም። ተጠሪ ሰራተኛ ለመቀነስ ይገደዲል ቢባል እንኳን ቅነሳው የተሻለ የትምህርት ደረጃና የሥራ ልምድ ያለንን ከሥራ በማሰናበት፣ ከእኛ በታች የትምህርት ዝግጅትና ልምድ ያላቸውን እንዱቀጥለ በማድረግ በዘፈቀደ እንዱወስን የሚፈቅድለት የሕግ ድንጋጌ የለም። ይህም የተጠሪ የሰራተኛ አቀናነስ በዘፈቀደ የተከናወነና በግለሰብ ምርጫ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ያሳያል። ተጠሪ የሥራ መደባችንን በመመሪያው የማይነካ ሰራተኞችን ያካተተ ነው። ስለዚህ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስንብቱ ሕጋዊ ነው በማለት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪ የካቲት 19 ቀን 2004 ዓ.ም በተፃፈ መልስ በመንግስት መመሪያ መሰረት የተጠሪ ሥራ ቀንሷል። ካለን ሰራተኞች 3-8 ፏርሰንት የሚሆኑ መምህራንና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞችን በሕግ አግባብ ተጠሪ ቀንሷል። የተማሪዎች ቁጥር አለመቀነሱ ከስንብቱ ጋር ግንኙነት የለውም። ተጠሪ ሰራተኛ ቀንሷል ብል ለመደምደም የሚያስችል ሁኔታ የለም። አመልካቾች በሚሰሩበት የሥራ ክፍልች እንደገና እንዱከፈቱ አልተፈቀደም። ተጠሪ አመልካቾችን ሲያሰናብት በሕጉ መሰረት ማስጠንቀቂያ የሰጠና መክፈል የሚገባውን ክፍያ የከፈለ በመሆኑ፣ አመልካቾች ያቀረቡት ጥያቄ የሕግ መሰረት የለውም በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካቾች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የፅሐፍ ክርክር እና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተጠሪ የአመልካቾችን የሥራ ውል ያቋረጠው በሕግ መሰረት ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪ ከሥራ ያሰናበታቸው ሰራተኞች በአጠቃላይ ካለት ሰራተኞች ቁጥር 3- 8 ፏርሰንት ብቻ በመሆኑ ተጠሪ የአመልካቾችን የሥራ ውል ያቋረጠው በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ 373/96 ቁጥር 29 ንዐስ አንቀጽ 1 በተደነገገው የሰራተኞች ቅነሣ መሰረት እንዲልሆነ የሥር ፍርድ ቤትም ሆነ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በውሣኔያቸው ገልፀውታል።
ተጠሪ ከትምህርት ሚኒስትር በተላለፈው መመሪያ መሰረት አዲዱስ ተማሪዎችን የማይቀበል በመሆኑ የሥራ እንቅስቃሴው የቀነሰና በዚህ ምክንያት በፉት የነበሩትን መምህራንና ሰራተኞች ይዞ ለመቀጠል ባለመቻለ የአመልካቾችን የሥራ ውል ማስጠንቀቂያ በመስጠት በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 28 ንዐስ አንቀጽ 1/መ/ መሰረት እንዲቋረጠ በማንሣት የተከራከረ ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ይህንን የተጠሪን ክርክር በመቀበል የሥራ ስንብቱ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ 377/96 ቁጥር 28 ንዐስ አንቀጽ 1/መ/ መሰረት የተከናወነና ሕጋዊ ነው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
መንግስት ባስተላለፈው መመሪያ የተጠሪ የሥራ መጠን የቀነሰና የተቀዛቀዘ ቢሆንም አመልካቾች የሚያስተምሩበት የትምህርት ክፍልና ይሰሩበት የነበረው የሥራ ክፍል ሙለ በሙለ ያልተዘጋና ያልተሰረዘ መሆኑንና ተጠሪ ቀደም ብል የተቀበላቸውን ተማሪዎች የጀመሩትን ትምህርት ለማስጨረስ የሚችለ መምህራንና ሰራተኞች በማስቀረት አመልካቾችን ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ የሥራ ውለን ያቋረጠ መሆኑን ተጠሪ በሥርም ሆነ በሰበር በግልፅ ክርክር ያቀረበበት መከራከሪያ መሆኑን ተረድተናል። እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ አመልካቾች የሚያስተምሩበት የትምህርት ክፍልና የሥራ ክፍል ሙለ በሙለ ባልተዘጋበትና ባልተሰረዘበት ሁኔታ ተጠሪ የሥራ መጠኑን መቀነሱንና ሥራው መቀዝቀዙን መነሻ በማድረግ ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ሰራተኞችን ለማስቀረትና ሥራ የማይኖራቸውን ሰራተኞች ለማሰናበት ውሣኔ ሲሰጥ የተጠቀመባቸው መስፈርቶች ምንድን ናቸው። ተጠሪ ሉጠቀምባቸው የሚገቡ መስፈርቶችስ ምንድን ናቸው? የሚለት ነጥቦች ናቸው።
አመልካቾች ተጠሪ እነሱን ከሥራ ለማሰናበት ሲወስን ምንም አይነት ተጨባጭነት ያለው መስፈርት ያልተጠቀመ መሆኑንና ተጠሪ በትምህርት ደረጃ በሥራ ልምድና የሥራ አፈፃፀማቸው ከአመልካቾች የሚያንሱ መምህራንና ሰራተኞችን በማስቀረት እነሱን በዘፈቀደ ከሥራ ያሰናበታቸው መሆኑን በሥር ፍርድ ቤት፣ በይግባኝና በሰበር ደረጃ የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪ አመልካቾችን ከሥራ ለማሰናበትና ላልችን ለማስቀጠል የተጠቀመባቸው ተጨባጭ መመዘኛዎች ያለ ለመሆኑ አልተጣራም፤ አሰሪው ሲሰራው የነበረው ሥራ በመቀነሱ ወይም በመቀዝቀዙ ምክንያት ካለት ሰራተኞች ከአስር ፏርሰንት በታች የሆኑትን የሥራ ውል ማቋረጡ የግድ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ካለት ሰራተኞች የተወሰኑትን የሥራ ውል በዘፈቀደ እንዱያቋርጥና የተወሰኑትን የሥራ ውላቸው እንዱቀጥል ለማድረግ የማይፈቀድለት መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 28 ንዐስ አንቀጽ 8 እና የአዋጅ ቁጥር 29 ንዐስ አንቀጽ 3 ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘትና ዓላማ በማየት ለመገንዘብ ይቻላል። በልላ አነጋገር ሰራተኞች የሚሰሩበት የሥራ ክፍል ሙለ በሙለ ባልተሰረዘበት ወይም ባልተዘጋበት ሁኔታ የአሰሪው ሥራ በመቀዝቀዙ ምክንያት ከነበሩት ሰራተኞች የተወሰነ ቁጥር ያላቸውን ሰራተኞች የሥራ ውል ማቋረጥ የግድ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ አሰሪው የሚሰናበቱትንና የሚቀጥለትን ሰራተኞች ለመለየት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 29 ንዐስ አንቀፅ 3 የተደነገጉትን መመዘኛዎች በመጠቀም በትምህርት ክፍለና በሥራ ክፍለ ያለትን ሰራተኞች አወዲድሮ ከሥራ የሚሰናበቱትንና በሥራ ላይ የሚቆዩትን ሰራተኞች በመለየት በሥራ ለማይቀጥለ ሰራተኞች ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ የሥራ ውለን ያቋረጠ መሆኑን የማስረዲት ግዳታ አለበት ከዚህ አንፃር ሲታይ፡-
ተጠሪ አመልካቾች በሚያስተምሩበት የትምህርት ክፍልና በሚሰሩበት የሥራ ክፍል የሚገኙትን ሰራተኞች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 29 ንዐስ አንቀፅ 3 በተቀመጡት መመዘኛዎች መሰረት በማወዲደር የአመልካቾችን የሥራ ውል አቋርጧል ወይስ አላቋረጠም?
ተጠሪ የአመልካቾችን የሥራ ውል ማስጠንቀቂያ በመስጠት ያቋረጠው አመልካቾች በትምህርት ደረጃቸው በሥራ ልምዲቸውና በሥራ አፈፃፀማቸው አመልካቾች በሚያስተምሩበት የትምህርት ክፍልና የሥራ ክፍል የሥራ ውላቸው እንዱቀጥል ከተደረጉ ሰራተኞችና መምህራን አንሰው በመገኘታቸው ነው ወይስ አይደለም?
ተጠሪ የአመልካቾችን የሥራ ውል ያቋረጠው አመልካቾችና በሥራ እንዱቀጥለ የተደረጉ ሰራተኞች ተመሣሣይ የትምህርት ደረጃ ፣ የሥራ ልምድና የሥራ አፈፃፀም ውጤት ኖሯቸው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 29 ንዐስ አንቀፅ 3 ከ/ሀ/ እስከ /ረ/ የተዘረዘሩትን ቅደም ተከተል በመጠቀም ነው ወይስ አይደለም? የሚለት ጭብጦች በሥር ፍርድ ቤት ያልተረጋገጡና ያልተጣሩ ነጥቦች ናቸው። ስለሆነም ተጠሪ የአመልካቾችን የሥራ ውል ያቋረጠው በአግባቡ ነው ወይስ ከህግ ውጭ ነው ብል ለመወሰን ከላይ የገለፅናቸው ነጥቦች መጣራትና በማስረጃ መረጋገጥ ያለባቸው ሆኖ እያለ እነዚህን ጭብጦች በመያዝ ሣያጣሩና በማስረጃ ሳያረጋግጡ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስንብቱ ህገወጥ ነው በማለት የሰጠው ውሣኔና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ ከላይ የጠቀስናቸውን የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ያላደረገና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ከተራ ቁጥር 1 እስከ ተራ ቁጥር 3 የተያዙት ጭብጦች ለማስረዲት በግራ ቀኙ በኩል የቀረቡ ማስረጃዎችንና ክርክሮችን በመመርመርና አስፈላጊ የሆኑ የሰነድ ማስረጃዎችን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 145/1/ መሰረት በማስቀረብ ተጠሪ አመልካቾችን ያሰናበተው በሕግ አግባብ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥና ተያያዥነት ያላቸውን ጉዲዮች እንዱወስን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343/1/ መሰረት ጉዲዩን መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.