No summary available.
ሐምል 03 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፉሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዩጵያ መድን ድርጅት - ነ/ፈጅ ማህላት ዓለሙ ቀረቡ ተጠሪ፡- 1.አቶ ክፍለዩሐንስ ተሰማ 2.አቶ ታምራት ተሰማ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ በሞት ምክንያት የሥራ ውል ሲቋረጥ የሰራተኛው ጉዲት ካሳ በመድን ፕሉሲ ተሸፍኖ ሲገኝ ካሳውን ሉጠይቁ የሚችለትን ወገኖችን ማንነት አተረጓጏም የሚመለከት ነው።የተጠሪዎች ወንድም አቶ ተገኔ ተሰማ በወንጂ ስኳር ፊብሪካ ተቀጥረው በስራ ላይ እያለ ሕይወታቸው በማለፈ አሰሪው የሆነው የወንጂ ስኳር ፊብሪካ ብር 20,286.60 (ሃያ ሺህ ሁለት መቶ ሰማንያ ስድሰት ብር ከስልሳ ሳንቲም)፣የአሁኑ አመልካች ደግሞ በስራ ላይ ለሚደረስ የሰራተኛ ጉዲት ካሳ በመድን ፕሉሲው በገባው ግዳታ መሰረት ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) ለመክፍል የመድን ፕሉሲ ሽፊን መሰጠቱን ገልጸው ይኸው ገንዘብ እንዱከፍል ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል።በአሰሪነቱ የተከሰሰው የወንጂ ስኳር ፊብሪካም ለክሱ በሰጠው መልስ ተጠሪዎች በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 107 መሰረት ካሳውን ለማግኘት የማይችለ መሆኑን ጠቅሶ ክሱ ውድቅ እንዱሆንለት የጠየቀ ሲሆን በአማራጭም የአሁኑ አመልካች ለሰራተኛች የጉዲት ካሳ የመድን ፕሉሲ ሽፊን የሰጠ መሆኑን ገልፆ ወደ ክርክሩ እንዱገባለት ጠይቋል። በዚህም መሰረት የአሁኑ አመልካች ወደ ክርክር እንዱገባ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ በሰጠው መልስ ወደክርክሩ ሉገባ የሚችልበት አግባብ የላለ መሆኑንና ተጠሪዎች ካሳውን ለመጠየቅ የሚችለበት ሕጋዊ ምክንያት የላለ መሆኑን ገልፆ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ የአሁኑን አመልካችና የስር ተከሳሽ የሆነውን የወንጂ ስኳር ፊብሪካን ለክሱ ሃላፉ አድርጎ አመልካች ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺኅ)፣አሰሪ የሆነው ፊብሪካው ደግሞ ብር 20,286.60 (ሃያ ሺህ ሁለት መቶ ሰማንያ ስድሰት ብር ከስልሳ ሳንቲም) እንዱከፍለ ሲል ወስኗል።በዚኅ ውሳኔ አመልካችና የወንጂ ስኳር ፊብሪካው ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ የስኳር ፊብሪካውን ካሳውን ከመክፈል ነፃ ሲያደርገው የአሁኑን አመልካች ግን ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ለተጠሪዎች ሉከፍል ይገባል ሲል ወስኗል።በዚኅ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት የሰበር አቤቱታውን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም አመልካች ወደ ክርክሩ እንዱገባ የተደረገበት አግባብ ስነ ስርዓቱን የተከተለ ያለመሆኑንና ተጠሪዎች የጉዲት ካሳውን ሉከፈላቸው ይገባል ተብል የተሰጠው ውሳኔም በአመልካችና በወንጂ ስኳር ፊብሪካ መካከል የተደረገውን የሰራተኞች የጉዲት ካሳ የመድን ፕሉሲውን ይዘትና መንፈስ ከአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 107፣110 እና 134(2) ድንጋጌዎች ጋር ያላገናዘበ መሆኑን የሚገልፅ ሁኖ አመልካች ለተጠሪዎች የጉዲት ካሳውን ሉከፍል አይገባም ተብል እንዱወሰን ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።አቤቱታው ተመርምሮም ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በሰጡት መልስ ካሳው ለሟች ሕጋዊ ወራሾች እንደሚከፈል የሕብረት ስምምነቱም በግልፅ የሚሳይ መሆኑን ጠቅሰው በመድን ፕሉሲው ብር 150,000.00 ለሰራተኛ መሞት እንደሚከፈል በተገለጸው መሰረት ተጠሪዎች የሟች ህጋዊ ወራሾች መሆናቸው ስለተረጋገጠ የማይከፈልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም በማለት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሉጸና ይገባል ሲለ ተከራክረዋል።አመልካች የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን ሰጥቷል።
የክርክሩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።እንደመረመረውም ጉዲዩ ለዚህ ችልት እንዱቀርብ የተደረገው አመልካች ለወንጂ ስኳር ፊብሪካ ሰራተኞች በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት የጉዲት ካሳ ለመክፈል በመድን ፕሉሲው መሰረት ግዳታ መግባቱ በድርጅቱ ወንጂ ስኳር ፊብሪካና ሰራተኞች መካከል የተደረገውን የህብረት ስምምነት መሰረት በማድረግ የሚመጣውን የሰራተኞች የጉዲት ካሳ ኃላፉነት ጭምር ያጠቃልላል? ወይስ አያጠቃልልም? የሚለውን ጭብጥ ለመፍታት ተብል ነው። በዚህም መሰረት ጉዲዩን እንደሚከተለው ተመልክተናል።
በክርክሩ ሂደት የተጠሪዎች ወንድም የሆኑት አቶ ተገኔ ተሰማ በስራ ላይ እንዲለ ሕይወታቸው ማለፈም ሆነ የአሁኑ አመልካች በስራ ላይ ለሚደርስ የሞት ጉዲት እስከ ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ድረስ የመድን ሽፊን መስጠቱ ያላከራከሩ ነጥቦች መሆናቸውን ተገንዝበናል።
በመሰረቱ አንድ ሰራተኛ በሥራ ላይ በሞት የተለዩ ስለመሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ የሞት ጉዲት ካሣ ለጥገኞች ስለሚከፍልበት ሁኔታ በአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 110 ስር በዝርዝር የተመለከተ ጉዲይ ነው።በተጠቀሰው አዋጅ አንቀጽ 110/1/ የተመለከተው ሉከፈል የሚገባው የክፍያ ዓይነት ሲሆን ከዚህ ውስጥ አንደ ለጥገኞች የሚከፈል ካሣ ነው።ለጥገኞች የሚከፈል ካሣ መጠን እና ጥገኞች የሚባለት እነማን እንደሆኑ ድንጋጌው በቀጣይ ንኡስ አንቀጾች በዝርዝር አስፍሯል።
የሟች ጥገኞች ብል ሕጉ የዘረዘራቸው የሟች ልጆች ሆነው 18 ዓመት በታች የሆኑ፣የሟች ሕጋዊ ባል ወይም ሚስት እና በሟች ሰራተኛ ድጋፍ ይረደ የነበሩ የሟች ወላጆች መሆናቸውን አንቀጽ 110/2/ በመዘርዘር ከዚኅ ውጪ ያለት ወገኖች የሟች ጥገኞች ያለመሆናቸውን በሚያስገነዘብ መልኩ ሕጉ መቀረፁን የድንጋጌው ይዘትና መንፈስ ያሳያል።በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት ለሚቀርበው የሞት ጉዲት ካሳ ጥያቄ ሉያቀርቡ የሚችለ ወገኖችን ማንነት ሕጉ ከላይ በተጠቀሰው አኳኋን በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን አሁን ለክርክሩ መሰረት የሆነው የሞት ጉዲት ካሳ ጥያቄ መሰረት አድርጓል በማለት ተጠሪዎች የሚከራከሩትም ይኸው ድንጋጌ በዚህ መልክ የተቀረፀ መሆኑን መከራከሪያ ሳያቀርቡ ለጥያቄው ሕጋዊ መሰረት ነው በማለት የሚጠቅሱት የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 134(2) ድንጋጌን ነው።ይኸውም የሕብረት ስምምነቱ ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 የተሻለ መብት የሚሰጥ ከሆነ በዚሁ መሰረት የሰራተኛው መብት ሉጠበቅለት ይገባል፣ሟች ተቀጥረው ይሰሩበት የነበረው ድርጅት ህብረት ስምምነት ሰራተኛው በስራ ላይ እያለ ከሞተ የጉዲት ካሳው ለሕጋዊ ወራሾች ይተላለፊል በማለት አስቀምጧል የሚለትን ምክንያቶችን በማንሳት ነው።
በእርግጥ የህብረት ስምምነት ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ሕግ የተሻለ ጥቅም የሚያስገኝ ከሆነ ይኸው ስምምነት ተፈፃሚነት ያለው ስለመሆኑ የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 134(2) ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል። የህብረት ስምምነት ማናቸውም የስራ ግንኙነቶችና የስራ ሁኔታዎችን የሚመለከቱ ጉዲዮች እንዱሁም አሰሪዎችና ማህበሮቻቸው ከሰራተኞች ማህበራት ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት ሉሸፈን እንደሚችል በአዋጁ አንቀጽ 128 ስር በግልፅ የሰፈረ ሲሆን ይህ ባአጠቃላይ እንደተጠበቀ ሁኖ የህብረት ስምምነት ይዘት በዚሁ አዋጁ ወይም በላልች ሕጎች ለሕብረት ስምምነት የተተዉ ጉዲዮች ስለሚወሰኑበት፣የሰራተኛ የሙያ ድህንነትና ጤንነት ስለሚጠበቅበት ሁኔታዎች፣ እንዱሁም የማህበራዊ አገልግልቶች ስለሚስፊፈበት፣ስለሰራተኞች ተሳትፍ፣በተለይም በእድገት፣በደመወዝ፣በዝውውር፣በቅነሳ እና በዱሲፔሉን አፈጻጸም ስለሚኖራቸው ተሳትፍ፣ስለ ስራ ሁኔታ፣ ስለስራ ደንብና ስለቅሬታ አቀራረብ ስነ ሥርዓት፣ስለስራ ሰዓት ድልደላና በስራ መካከል ስለሚሰጥ እረፍት እና የሕብረት ስምምነት ስለሚሽፍናቸው ወገኖች ጸንቶ ስለሚቆይበት ጊዜ መያዝ እንደሚችል በአንቀፅ 129 ተዘርዝሯል።ከዚኅም በተጨማሪ የህብረት ስምምነት ልዩ ሁኔታዎች ሉባለ በሚችለትና በአዋጁ አንቀጽ 133 ስር በተዘረዘሩት ምክንያቶች እንዳት መፈፀም እንደአለበት ተጠቃሹ ሕግ ያሳያል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ ለጉዲዩ አግባብነት አለው የተባለው የህብረት ስምምነት ስለተፈፃሚነት ወሰኑ በአንቀፅ 2 ስር የደነገገ ሲሆን ህብረት ስምምነቱ በድርጅቱ የስራ መሪዎች መተዲደሪያ ደንብ ከታቀፈት የስራ መሪዎች በስተቀር በቋሚ፣ ቁርጥና በወርሃዊ/ሲዝናል ሰራተኞች ላይ ተፈፃሚነት እንደሚሆን በተጠቃሹ ድንጋጌ ቁጥር አንድ ስር የተቀመጠ ሲሆን የህብረት ስምምነቱ ስለህብረት ስምምነቱ አተረጓጎምና ያልተጠቀሱ ጉዲዮችን በተመለከተ የሚገዛ ድንጋጌም በአንቀፅ 4 ስር በግልጽ አስፍሯል። በዚህም መሰረት የሕብረት ስምምነቱ አንቀጽ 4(1) ድንጋጌ በህብረት ስምምነቱ ውስጥ ባለት ድንጋጌዎች የአተረጓጎም ወይም ግልጽ ያልሆኑ/ያልተጠበቁ ጉዲዮች ላይ ድርጅቱና የሰራተኛው ማህበር በውይይት መፍትሓ እንደሚፈልጉ፣ጉዲዩ በውይይት የማይፈታ ከሆነ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 እና ቀደም ሲል በተሻሻለትና ወደፉትም በሚወጡት ማሻሻያ አዋጆች መሰረት እንደሚፈፀም ያስቀምጣል።እንግዱህ በተያዘው ጉዲይ አከራካሪ የሆነው እና ትርጉም የሚያስፈልገው ሁኖ የተገኘው ነጥብ በህብረት ስምምነቱ በአንቀጽ 40(1) ስር ስለጉዲት ካሳ ተጠቃሚዎች በሚመለከት የተቀመጠው ድንጋጌ በስራ አደጋ ለሚመጣ ኢንሹራንሽ/የመድን ዋስትና የአካል ጉድለትና ጉዲት ካሳ ተጠቃሚ የሚሆኑት የሰራተኛው ሕጋዊ ወራሾች ስለመሆናቸው ተገልፆ ከተቀመጠው ድንጋጌ ውስጥ ሕጋዊ ወራሾች የሚለው ሐረግ የትርጉም አድማሱ በውርስ ሕግ የሚታወቁትን በሕጋዊ ወራሽነት የሚታወቁትን ነው ወይስ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 110 ስር የተዘረዘሩትን ብቻ ነው የሚመለከተው ለሚለው ጥያቄ የሕብረት ስምምነቱ ግልጽ የሆነ ምላሽ አይሰጥም።ይሁን እንጂ በህብረት ስምምነቱ ትርጉም ሲያስፈልግ በምን አግባብ ሉተረጎም እንደሚችል በአንቀፅ 4(1) የተመለከተ ሲሆን ትርጉሙ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 እና ቀደም ሲል በተሻሻለትና ወደፉትም በሚወጡት ማሻሻያ አዋጆች መሰረት እንደሚፈፀም የተመለከተ በመሆኑ በህብረት ስምምነቱ ሕጋዊ ወራሾች የሚለው ሐረግ የሚያመላክተው በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 110 ስር የተመለከቱትን የተጎጂ ሰራተኛ ጥገኞችን ነው። እነዚህ ሰዎች እነማን እንደሆኑ ሕጉ መዘርዝሩን ከላይ ተመልክተናል። እንዱህ ከሆነ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 110 ስር ከተዘረዘሩት ውጪ ያለትና በውርስ ሕጉ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 842 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ስር የተመለከቱት ሕጋዊ ወራሾች በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት በስራ አደጋ ለሚመጣ ኢንሹራንስ/የመድን ዋስትና የአካል ጉድለትና ጉዲት ካሳ ተጠቃሚ ሉሆኑ የሚችለበት ሕጋዊ አግባብ አይኖርም።
አመልካችና ተጠሪ በአደረጉት የመድን ዋስትና ፕሉሲ ስር በስራ ላይ ለሚደርሱ የሞት፣ለአካል ጉዲት፣በስራ ላይ ለሚከሰት በሽታ ጉዲቶች በኢትዩጵያ ሕግ መሰረት የጉዲት ካሳ መከፈል ያለበት ስለመሆኑ የተመለከተ ሲሆን በፕሉሲው"……if at any time the period of insurance any worker in the insured’s immediate service engaged in a category of work described in the Schedule shall sustain death or bodily injury by accident or occupational disease occurring at the place assigned to him for work or arising from his work and during the time of his work by the insured in the Business and if the insured shall be liable to pay compensation for such death, bodily injury, or occupational disease under Ethiopian law,……" በሚል ከተቀመጠው አረፍተ ነገርም መገንዘብ የሚቻለው መድን ሽፊኑ በስራ ላይ ለሚደርሱ የሞት፣ለአካል ጉዲት፣በስራ ላይ ለሚከሰት በሽታ ጉዲቶች በሚገዛው የኢትዮጵያ አሰሪና ሰራተኛ ሕግ መሰረት የሚታይ መሆኑን ግራ ቀኙ ስምምነት የደረሱ መሆኑን ነው። ይህ አተረጓጎም ተዋዋይ ወገኖች በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት ጉዲዩ ይታያል ብለው ሲስማሙ ሐሳባቸው ምን ነበር? የሚለውን የውል አተረጓጎም ደንብን በመከተልም የምንገነዘበው ጉዲይ ነው።
በመሰረቱ በውል ውስጥ የተጠቀሱት ቃላትና ድንጋጌዎች ግልጽ ባልሆኑ ጊዜ ከፍ/ሕ/ቁጥር 1732፣1735-1738 ድረስ ባለት ድንጋጌዎች ስር በሰፈሩት ደንቦች መሰረት መተርጏም የተፈቀደ ነው። በዚህም መሰረት ለተያዘው ጉዲይ አግባብነት ያላቸው ደንቦች በፍ/ሕ/ቁጥር 1734፣1735 እና 1736 ሲሆኑ የተዋዋዮች፡ ሐሳብ፣ በውለ ላይ የኢትዮጵያ ሕግ በሚለው የተቀመጠው ጠቅላላ አነጋገር በመድን ፕሉሲው ስር የተዘረዘሩት የጉዲት አይነቶችን እርስ በርሳቸው በማስተሳሰር በመድን ፕሉሲው የኢትዮጵያ ሕግ የሚለውን ሐረግ ለማስቀመጥ የፈለጉትበት ሁኔታ ሐሣባቸውን ምን እንደነበር ለማወቅ መሞከር እና የውልችን ቃልች አንደን ከአንደ ጋር እያዛመደ በመመልከት ለውለ ጉዲይ አግባብነት ያለውን ትርጉም በመስጠት አዎንታዊ ውጤት እንዱኖረው ማድረግ ተገቢ ስለመሆኑ ተጠቃሽ ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ። ከዚህም አንፃር የተያዘው ጉዲይ ሲታይ በመድን ፕሉሲው ስር የጉዲቶቹ አይነቶች መዘርዘራቸውና በኢትዮጵያ ሕግ አግባብ ተብል መቀመጡ ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት የሚገዛ መሆኑን በመፈለግ ውለን ያደረጉ መሆኑን የሚያስገነዝበን ሁኖ አግኝተናል። በመሆኑም ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለው አዋጅ ቁጥር 377/1996 ስለመሆኑ የግራ ቀኙ ፍላጎት ነበር ከተባለ ደግሞ ተጠሪዎች በአዋጁ አንቀጽ 110(2) ድንጋጌ አገላለፅ መሰረት የወንድማቸው የሞት ጉዲት ካሳ በውርስ ህጉ ሕጋዊ ወራሽ ነን፣የሕብረት ስምምነቱም የተሻለ ተጠቃሚነትን የሚሰጥ ነው በሚል የሞት ጉዲት ካሳውን የሚጠይቁበትና የሚያገኙበት ሕጋዊ መሰረት የለም።ለአንድ ሰው የመብት ጥያቄ መሰረቱ ውል ወይም ሕግ ሲሆን ተጠሪዎች የሞት ጉዲት ካሳውን ለመጠየቅ ከሕጉም ሆነ ከውል የመነጨ መብት ወይም ጥቅም የላቸውም። እንዱህ ከሆነ ተጠሪዎች ክስ መመስረታቸውም ሆነ የስር ፍርድ ቤቶች የሞት ጉዲት ካሳ ለተጠሪዎች ይገባል በማለት መወሰናቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 33(2) ስር የተመለከተውን መመዘኛ እና በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 110፣128፣129፣134 እና በሕብረት ስምምነቱ አንቀጽ 2 እና 4 እንዱሁም 40(1) ስር ያለን ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ከውል ሕግ አተረጓጎም ደንቦችና ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1731 ድንጋጌ አንፃር ያላገናዘቡ በመሆኑ በዚህ ረገድ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 49598 ግንቦት 30 ቀን 2003 ዓ.ም ለተጠሪዎች የሞት ጉዲት ካሳ ሉከፈል ይገባል ተብል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል፣ይህንኑ ውሳኔ ክፍል በማፅናት በአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 11906 ነሐሴ 13 ቀን 2003 ዓ.ም፣በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በ30/12/2003 ዓ.ም የተሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት በድምፅ ብልጫ ተሽሯል።
ተጠሪዎች ሟች ወንድማቸው አቶ ተገኔ ተሰማ በስራ ላይ ለደረሰባቸው የሞት አደጋ የሟቹ አሰሪ በገባው መድን ውል መሰረት የጉዲት ካሳ የሚገባቸው ሰዎች አይደለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.