No summary available.
ሰኔ 19 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፉሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ሳሳካዋ ግልባል 2000 ፔሮጀክት ነ/ፈጅ ባልቻ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ ሸዋድንበር ደቻሳ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ የተጀመረው በአደአ ወረዲ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ የሰበር ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ ነበር። ክሱም ተከሳሽ ከህግ ውጪ የስራ ውላን ስላቋረጠብኝ የተለያዩ ክፍያዎችን በድምሩ ብር 93,288.338 እንዱከፍል ይወሰንልኝ የሚል ነው። ተጠሪው በበኩለ ባቀረበው የመ/ደ/መቃወሚያ ተከሳሽ ድርጅት ለትርፍ ያልተቋቋመ በመሆኑ ክሱ በአዋጅ ቁጥር 377/96 በአንቀጽ 3(2) (መ) መሰረት ውድቅ ላሆን ይገባል ብሎል።
የወረዲው ፍርድ ቤትም ተከሳሽ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 3 (2) መሰረት የተከሳሽ ተቃውሞ ተቀባይነት ያለው ነው በማለት የከሳሽን ክስ ውድቅ አድርጓል።
ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በበኩለ በመልስ ሰጪና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የተፈጸመው ውል አንቀጽ 3(5) እንደሚገልጸው ድርጅቱ ለትርፍ ያልተቋቋመ ቢሆንም ባለሙያዎችን ሲያሰራ የቅጥር ውል የሚፈጽመው በኢትዮጵያ ህግ መሰረት እንደሆነ በውለ በግልጽ ተጠቅሷል እንደመልስ ሰጪ ያለ ድርጅቶች የሚመሩበትን ደንብ የሚንስትሮች ም/ቤት እስካላወጣ ድረስ ደግሞ ሰራተኞቹ የሚተዲደሩት በአዋጁ መሰረት ይሆናል። በመልስ ሰጪውና ይግባኝ ባይ መካከል በተመሰረተው የቅጥር ውል መነሻ ይግባኝ ባይ ደመወዝ እየከፈለ ሲያሰራ መቆየቱ የታመነ ሲሆን በዚሁ የቅጥር ውል መሰረት ለይግባኝ ባይ መፈጸም የሚገባውን ግዳታ አለመፈጸሙ ተገቢነት የለውም በሚል የወረዲውን ፍርድ ቤት ትእዛዝ በመሻር በፍሬ ነገሩ ላይ አከራክሮ እንዱወስን ክርክሩን በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/343 (1) መሰረት የመለሰው ሲሆን የክልለ ሰበር ሰሚው ችልትም በከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለውም በማለት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ውድቅ አድርጓል።
የአሁኑ አመልካችም በከፍተኛውና በክልለ ጠ/ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል የሰበር አቤቱታውን ለዚህ ችልት ያቀረበ ሲሆን በዋናነት የጠቀሰው የቅሬታ ነጥብም፡- ሲጠቃለል አመልካች ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እ.ኤ.አ ዱሴንበር 2008 በተፈረመ ስምምነት የተቋቋመ ሲሆን በዚሁ ስምምነት አንቀጽ 2 (3) መሰረት ለትርፍ ያልተቋቋመ ፔሮጀክት በመሆኑ በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 3(2) (መ) መሰረት በዚህ አዋጅ ሉከሰስ አይገባም በሚል ያቀረብነውን መቃወሚያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ባለመቀበል ከተከራከርንበት ጭብጥ በመውጣት ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 3(3)(ለ) መሰረት መርምሮ ያቀረብነውን የመ/ደ/መቃወሚያ ውድቅ ማድረጉና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልትም ይህንኑ ማጽናቱ ተቀባይነት የለውም የሚል ነው። ተጠሪው በበኩለ በሰጠው መልስ አመልካች በአዋጁ ልዲኝ አይገባም ይበል እንጂ ክልከላው በሚንስትሮች ም/ቤት በሚወጣው ደንብ ሽፊን ስለማግኘቱ ያስረዲው ነገር የለም። በመሆኑም አመልካች በዚህ አዋጅ መሰረት ሉከሰስ የማይችልበት ምክንያት ስለላለው አቤቱታው የህግ መሰረት ያለው አይደለም በማለት ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከዚህ በላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የአመልካች ድርጅት ለትርፍ ያልተቋቋመ በመሆኑ ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 377/96 ስር የሚሸፈን አይደለም በማለት ያቀረበውን መቃወሚያ ከፍተኛው ፍርድ ቤትና ሰበር ሰሚው ችልት ውድቅ ማድረጋቸው በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
ተጠሪው ከአመልካች ድርጅት ጋር በተደረገው የቅጥር ስራ ውል መነሻ በአመልካች ድርጅት እየሰራ መቆየቱን ገልጾ የሚከራከር ሲሆን አመልካች ድርጅትም በመካከላቸው የቅጥር ስራ ውል የለም ሲል ያቀረበው ክርክር የለም። ሆኖም አመልካች በዋናነት የሚከራከረው ድርጅቱ ለትርፍ ያልተቋቋመ በመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 ለጉዲዩ ተፈጻሚነት የለውም በሚል ነው። ለዚሁ ክርክር በማስረጃነት በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው የጽሁፍ ሰነድም በአመልካችና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል በ2000 ዓ/ም የተፈረመውን የተሻሻለውን የመግባቢያ ሰነድ( Memorandum of Understanding) ነው። በዚሁ በተሻሻለው የመግባቢያ ሰነድ አንቀጽ 3 (5) ደግሞ ድርጅቱ የአገር ውስጥ ሳይንቲስቶችን፣የሰብል ምርት ልዩ ባለሙያዎችን፣ ቴክኒሽያኖችን፣የፅህፈት እና አስተዲደራዊ እንዱሁም የኦፔሬሽን ድጋፍ ሰጪ ፏርሶኔልችን በኢትዮጵያ መንግስት አግባብ ባላቸው ህጎች መሰረት የምደባና የቅጥር ሁኔታዎችን እና ገደቦችን እንደሚያስቀምጥ ተመልክቷል። የመግባቢያው ሰነድ በዚሁ መልክ ከተቀመጠና በአመልካችና በተጠሪው መካከል የስራ ቅጥር ውል መደረጉ በአመልካች እስከታመነ ድረስ ለትርፍ ያልተቋቋመ የውጪ ድርጅት ቢሆንም ለጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 ተፈጻሚነት ይኖረዋል። አዋጁ ተፈጻሚነት ሉኖረው የማይችለው በአዋጁ አንቀጽ 3(3) የተደነገገው ልዩ ሁኔታ ሲኖር ብቻ ነው። ይሄውም እንደአመልካች ያለ ድርጅቶችን በተመለከተ አዋጁ ተፈጻሚነት አይኖረውም በሚል የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ያወጣ ከሆነ ወይም ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች የተወሰነ ከሆነ ነው። በዚህ በተያዘውም ጉዲይ እንደአመልካች ያለ ድርጅቶችን በሚመለከት የወጣ የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ካለመኖሩም ላላ ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶችም እንደ አመልካች ያለ ድርጀቶች በሀገር ውስጥ የሚቀጥሩአቸውን ሰራተኞች በተመለከተ አዋጅ ቁጥር 377/96 ተፈጻሚነት የለውም በሚል በግልጽ የተደረገ ስምምነት የለም። እንዱያውም በዚህ በሚያከራክረው ጉዲይ የስራ ቅጥር በኢትዮጵያ ህግ መሰረት ይደረጋል በሚል በስር ፍርድ ቤት አመልካች ባቀረበው የመግባቢያው ሰነድ ላይ መስፈሩ አዋጁ ተፈጻሚነት ያለው ስለመሆኑ የሚረጋግጥ ነው።
በመሆም ከዚህ በላይ በተጠቀሱት ህጋዊ ምክንያቶች የተነሳ የስር ከፍተኛ እና የክልለ ጠ/ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች ድርጅት የተቋቋመው ለትርፍ ባለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 ተፈጻሚነት የለውም ሲል ያቀረበውን ክርክር ውድቅ በማድረግ በፍሬ ጉዲዩ ላይ ክርክር እንዱደረግ ክርክሩን ወደ ወረዲ ፍርድ ቤት መመለሳቸው ተቀባይነት ያለው ስለሆነ በውሳኔያቸው ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ባለማግኘታችን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/26939 በቀን 27/07/2003 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠውን ውሳኔ እና የክልለ ጠ/ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ቁ/129113 በቀን 11/08/2003 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠውን ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ 348 (1) መሰረት አጽንተናል።
ለተያዘው ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አግባብነት አለው ተብል ጉዲዩ በዚሁ አዋጅ መሰረት እንዱታይ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና በክልለ ጠ/ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የተወሰነው ተገቢ ነው ብለናል።
የዚህን ፍርድ ቤት ወጪና ኪሳራ የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.