No summary available.
የሰ/መ.ቁ.744ዐዐ ግንቦት 7 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማዉ ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ግዮን ኢንደስትሪያልና ኮሜርሺያል ኃ/የተ/የግል ማህበር-ነ/ፈጅ ያሬድ ወርቅዬ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ኃይለ ናርዬ ጠበቃ ገ/እግዚአብሓር ኪዲኔ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት የሚስተናገደውን የግል የስራ ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። ተጠሪ ከአመልካች ጋር የመሰረቱት የስራ ግንኙነት ውል ከሕግ ውጪ የተቋረጠባቸው መሆኑን ገልፀው የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈሎቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም ከተጠሪ ጋር የስራ ውል ግንኙነት ስለመኖሩ ሳይክድ የስራ ውለ የተቋረጠው ተጠሪ ሲያሽከረክሩ በነበሩት በአመልካች ድርጅት ንብረት ላይ በግጭት ጉዲት ያደረሱ በመሆኑ ነው በማለት ስንብቱ ሕጋዊ ነው ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩ በዚህ መልክ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ጉዲዩን በመመርመር ተጠሪ ጉዲት አድርሷል በማለት አመልካች የሚከራከረው የአመልካች ድርጅት እህት ኩባንያ የሆነው የግዮን ጋዝ ኃ/የተ/የግል ማህበር ንብረት በሆነው ተሽከርካሪ ላይ መሆኑ መረጋገጡን፣ ተጠሪ የስራ ቅጥር ውል የፈፀሙት ከአመልካች ጋር እስከሆነ ድረስ የአመልካች ድርጅትና የግዮን ጋዝ ኃ/የተ/የግል ማህበር ባለቤት አንድ መሆን ድርጅቶቹ የራሳቸው ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው እስከሆነ ድረስ በአመልካች ድርጅት ንብረት ላይ ተጠሪ ጉዲት አድርሰዋል ለማለት የማያስችል መሆኑን በምክንያትነት ይዞ የአመልካች እርምጃ ሕገወጥ ነው በማለት ደምድሞ ለተጠሪ የተለያዩ ክፍያዎች ሉከፈላቸው ይገባል በማለት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ከእህት ኩባንያው ለስራ ተከራይቶ ሲጠቀም በነበረው ተሽከርካሪ ተጠሪ ጉዲት ያደረሱ ሁኖ እያለ ኩባንያዎቹ የተለያየ የሕግ ሰውነት ያላቸው ናቸው በማለት ስንብቱን ሕገወጥ ነው በማለት መወሰናቸው ያላግባብ ነው የሚል ነው። የሰበር አቤቱታው ተመርምሮም ተጠሪን የቀጠረውና ጉዲት የደረሰበት ተሽከርካሪ የአመልካች ድርጅት ሆኖ እያለ በአመልካች ድርጅት የደረሰ ጉዲት የለም ተብል ስንብቱ ሕገወጥ ነው የተለያዩ ክፍያዎች ለተጠሪ ይፈጸሙ ተብል መወሰኑ በአግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ድርጅት የተጠሪ ቀጣሪ ፣ ተጠሪ ጉዲት አደረሰ የተባለበት ተሽከርካሪ ደግሞ የአመልካች ድርጅት ባለቤት የሆኑት ግለሰብ ባለቤት የሆኑበት ሁኖ ጉዲቱ ደረሰ በተባለበት ጊዜ አመልካች ድርጅት ተሽከርካሪውን ለራሱ ጥቅም በመገልገል ላይ በነበረበት ሁኔታ ተጠሪ ግጭት ያደረሱ ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ ስለመሆኑ የክርክሩ ሂደት የሚያሳይ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የህግ ሰውነት ያለው ሲሆን በዚህ ሕጋዊ ችልታ የመከሰስም ሆነ የመከሰስ ችልታ ይኖረዋል። አንድ የተፈጥሮ ሰው ከአንድ በላይ ኃ/የተወሰነ የግል ማህበሮች ባለቤት ሁኖ መገኘት በአንደ ድርጅት ውስጥ ያለ ሰራተኛ በልላኛው እህት ድርጅቱ ንብረት ላይ ለሚያደርሰው ጉደት በልላኛው ድርጅት ውስጥ በሕጉ አግባብ የተቀጠረውን ሰራተኛ በድርጅቱ ንብረት ላይ ጉዲት አድርሰሃል በማለት የስራ ውለን በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27/1/ሸ/ መሰረት ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ የሚስችለው ሕጋዊ ምክንያት አይደለም።
በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27/1/ሸ/ መሰረት የስራ ውለን ያለማስጠንቀቂያ አሰሪው ሉያቋርጥ የሚችለው ሰራተኛው በአሰሪው ንብረት ወይም ከድርጅቱ ስራ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ባለው ማናቸውም ንብረት ላይ ሆነ ብል ወይም በከባድ ቸልተኝነት ጉዲት ማድረሱ ሲረጋገጥ ነው። ይህ ድንጋጌ ከያዛቸው ቁም ነገሮች ውስጥ “የአሰሪው ንብረት” እና “ከድርጅቱ ስራ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ባለው ማናቸውም ንብረት” የሚለት ሐረጎች ይገኙበታል። ስለዚህ ጉዲት ደርሷል ለማለት መሟላት ካለባቸው ነገሮች አንደ ንብረቱ የአሰሪው መሆኑና በቀጥታ ከድርጅቱ ስራ ጋር የሚገናኝ መሆኑ ነው። አሰሪ ማለት ደግሞ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ሰዎችን በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 4 በተመለከተው መሰረት ቀጥሮ የሚያሰራ ግለሰብ ወይም ድርጅት ስለመሆኑ በተጠቃሹ አዋጅ አንቀፅ 2/1/ ስር ትርጉም የተሰጠበት ጉዲይ ነው።
በዚህ መሰረት የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ተፈጥሯል ልባል የሚችለው የስራ ወለ በአዋጁ አንቀጽ 4 መሰረት ሲመሰረት መሆኑንና በዚህ አግባብ የስራ ውለ መመስረቱ ከተረጋገጠ የስራ ውል ግንኙነት በሕጉ አግባብ የሚገዛው ይህንኑ ውል በመሰረቱት ሰዎች መካከል ብቻ ይሆናል። የስራ ውል ግንኙነት በልላቸው ሰዎች መካከል የአዋጅ ቁጥር 377/1996 ተፈፃሚ የሚሆንበት ምክንያት የለም።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች ተጠሪ ጋር የስራ ውል ግንኙነት መመስረቱ የተካደ ጉዲይ አይደለም። አመልካች ተጠሪን ማሰናበቱን ሕጋዊ ነው በማለት የሚከራከረው የግዮን ጋዝ ኃ/የተ/የግል ማህበር የሆነ መኪና ላይ በግጭት ምክንያት ጉዲት አድርሰዋል በማለት ነው።
ይሁን እንጂ ተጠሪ ከዚህ የተሽከርካሪው ባለቤት ከሆነው ድርጅት ጋር የፈፀሙት የቅጥር ውል የላለ ሲሆን ተሽከርካሪውን አመልካች ለስራ ምክንያት ተኮናትሮ ሲጠቀምበት የነበረ ወይም ንብረቱ ከድርጅቱ ስራ ጋር ቀጥታ ግንኙነት የነበረው ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ያልተረጋገጠ ነጥብ ነው። እንዱህ ከሆነ አመልካች ድርጅት ተጠሪ በልላ ድርጅት ንብረት ላይ ጉዲት አድርሰዋል በማለት በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት የተመሰረተውን የስራ ግንኙነት ውል ለማቋረጥ የሚስችል አይደለም። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ የስራ ውለን ከአመልካች ጋር መመስረታቸውንና ጉዲት ደርሶበታል የተባለው ተሽከርካሪም የአመልካች ድርጅት ባለቤት የሆኑት ግለሰብ የሆኑበት ግዮን ጋዝ ኃ/የተ/የግል ማህበር መሆኑን በማረጋገጥ ስንብቱ ሕገወጥ ነው በማለት የሰጡት ውሣኔ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 2/1/ ፣ 4 እና 27/1/ሸ/ እና በንግድ ሕጉ ኃላፉነታቸው የተወሰነ የግል ማህበራት ስላላቸው ሕጋዊ ችልታን በተመለከተ የተደነገጉትን ድንጋጌዎችን ያገናዘበ ነው ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ፈጽመዋል ለማለት የሚያስችል ሁኖ አልተገኘም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት 25 ቀን 2003 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 16 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
የአመልካች እርምጃ ሕገወጥ ነው ተብል ለተጠሪ የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈለ መወሰኑ ባግባቡ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
በዚህ ችልት መጋቢት ዐ5 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል። ይፃፍ።
No topics extracted.