No summary available.
መጋቢት 10 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አመልካች፡- ሜድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግል ማህበር - ነ/ፈጅ ወርቆ ምራጭ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- አቶ ሰይፈ ተፈሪ - በላለበት የሚታይ ነው መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት በሚገዛው ግንኙነት ውስጥ ሰራተኛው ስራውን ከመልቀቁ በፉት የወሰደውን ብድር ሳይመልስ ስራውን በገዛ ፈቃደ ሲለቅ አሰሪው ለሰራተኛው ሉከፍለው ከሚገባው የፔሮቪደንት ፈንድ ገንዘብ ቀንሶ ለማስቀረት የሚችልበትን የሕግ አግባብ የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው ሲሰሩ ከቆዩ በሁዋላ በገዛ ፈቃዲቸው ስራቸውን መልቀቃቸውን ገልፀው የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፍሎቸው ይወሰን ዘንድ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። ተጠሪ ሉከፍለኝ ይገባል በማለት ከዘረዘራቸው የክፍያ ዓይነቶች አንደ የፔሮቪደንት ፈንድ ሲሆን አመልካች ለዚሁ ለተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ በሰጠው መከላከያ መልስ ተጠሪ የፔሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ መሆኑን ሳይክድ ለተጠሪ ብር 9,000 /ዘጠኝ ሺህ/ መስጠቱን፣ ቀሪውን በተመለከተ ግን አመልካች ለተጠሪ ብድር አበድሮት እንደነበረና ብድሩን ሙለ በሙለ ባለመክፈለ በመካከላቸው ባለው ስምምነት መሰረት ያስቀረው መሆኑን ጠቅሶ ልከፍለው አይገባም በማለት ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤትም በዚህ ረገድ የቀረበውን የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ተጠሪ ብር 9,000 መውሰዲቸውንና ከአመልካች በብድር የወሰደት ገንዘብ መኖሩን ያለመካዲቸው ተረጋግጧል በማለት አመልካች ከተጠሪ ለእዲ መክፈያነት ያስቀረውን የፔሮቪደንት ፈንድ ቀሪ ለመክፈል ሉገደድ አይገባም በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የፔሮቪደንት ፈንድ ከደመወዝ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ካላቸው ክፍያዎች አንደ መሆኑን ገልጾና ያለተጠሪ ስምምነት ደግሞ አሰሪ የሆነው አመልካች ለእዲ መክፈያነት የፔሮቪደንት ፈንድ ቆርጦ ለማስቀረት የማይችል ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 59/1/ ስር የተመለከተ መሆኑን በዋቢነት ጠቅሶ አመልካች ቀሪ የፔሮቪደንት ፈንድ ክፍያ ብር 11,000.00 /አስራ አንድ ሺህ ብር/ ለተጠሪ ይክፈላቸው በማለት የስር ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የሰጠውን የውሳኔ ክፍል ሽሮታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪ በድርጅቱ ሕብረት ስምምነትና በብድር ፕሉሲ መሰረት የወሰደትን ብድር ሳይከፍለ ስራውን በገዛ ፍቃዲቸው ከመልቀቃቸውም በላይ ብድሩ መኖሩንና ስምምነት መኖሩንም ሳይክደ አመልካች ከፔሮቪደንት ፈንድ ቆርጦ እዲውን ማስቀረት አይችልም ተብል መወሰኑ የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 59 ድንጋጌን ይዘት፣ የግራ ቀኙን ክርክርና የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በድርጅቱ የብድር ፕሉሲ ላይ ሉያስከትል የሚችለውን አለታዊ ተፅእኖ በአግባቡ ባላገናዘበ መልኩ ነው በማለት ውሳኔው እንዱሻር ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም ተጠሪ ከስራ ስንብቱ በፉት የነበረበትን እዲ ከፔሮቪደንት ፈንድ ላይ ሉቆረጥ/ሉቀነስ/ አይገባውም በማለት በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ ከተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ከአመልካች ጋር የመሰረቱትን የስራ ውል ግንኙነት ያቋረጡት በገዛ ፈቃዲቸው መሆኑን፣ የስራ ውለ ከመቋረጡ በፉት ደግሞ በሰራተኝነታቸው ከአሰሪው በተሰጣቸው መብት መሰረት ብድር ወስደው ብድሩን እንደተጠቀሙና እዲውን ሙለ በሙለ ሳይከፍለ የስራ ስንብት ጥያቄን ያቀረቡ መሆኑን፣ ብድሩ ያለባቸው መሆኑንም ደግሞ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር ያመኑ መሆኑ መረጋገጡን እንዱሁም የብድሩ መሰረትም በአሰሪው ድርጅት ውስጥ ያለው የሕብረት ስምምነት እና የብድር ፕሉሲ መሆኑ አከራካሪ ያለመሆኑን ነው። ከፍ ሲል እንደተገለፀው የአሁኑ ተጠሪ ዕዲ የለብኝም በሚል ያቀረበው ክርክር የለም ተብል በስር ፍርድ ቤት የታለፈ ስለሆነ አመልካች እዲው የተጠሪ መሆን ያለመሆኑን ላላ ክስ እንዱመሰረት የሚጠበቅበት ሕጋዊ ምክንያት የለም።
የአዋጁ አንቀጽ 59/1/ በሕብረት ስምምነት በተወሰነው መሰረት ከሰራተኛው ደመወዝ ላይ መቀነስ እንደሚቻል የሚያስረዲ ሲሆን የፔሮቪደንት ፈንድ ከደመወዝ ጋር ጥብቅ ቁርኝነት ያለው የክፍያ ዓይነት ነው ቢባል እንኳ ተጠሪ እዲ ያለባቸው ስለመሆኑ በክርክሩ ሂደት ባልካደት ሁኔታ ላላ ግልጽ ስምምነት የሚያስፈልግበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። በመሆኑም ተጠሪ ከአመልካች ድርጅት የወሰደትን የብድር ገንዘብ ሳይመልሱ በገዛ ፈቃዲቸው ስራቸውን በለቀቁበትና እዲው መኖሩንም በስራ ክርክር ችልት ባመኑበት ሁኔታ እዲውን ከፔሮቪደንት ፈንድ ቆርጦ ለማስቀረት ላላ ግልጽ የሆነ ስምምነት ያስፈልግ ነበር ተብል በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮችን ከድንጋጌው መንፈስ እና ይዘትጋር ያላገናዘበ በመሆኑ ተቀባይነት የላለው ሁኖ አግኝተናል።
በአጠቃላይ በዚህ ጉዲይ የአሁኑ ተጠሪ የወሰደውን የብድር ገንዘብ ሙለ በሙለ ሳይመልሱ ስራውን በገዛ ፈቃዲቸው በለቀቁበትና እዲውም የሚመለከታቸው መሆኑን በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር በአመኑት ሁኔታ ከፔሮቪደንት ፈንድ እዲውን ቀንሶ ለማስቀረት ግልጽ ስምምነት የለም ተብል በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰኑ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 59/1/ ስር የተመለከተውን የድንጋጌውን መንፈስ ከአመልካች ድርጅት የሕብረት ስምምነት እና የብድር ፕሉሲ ጋር ባለገናዘበ መልኩ በመሆኑ ውሣኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ በ06/11/200 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በፋ/የመጀ/ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ በ19/08/2003 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.348/1/ መሰረት ጸንቷል።
አመልካች ከተጠሪው ፔሮቪደንት ፈንድ በዕዲው ምክንያት ቀንሶ የወሰደውን ገንዘብ ሉመልስ አይገባም ብለናል።
በዚህ ፍ/ቤት ለተካሄደው ክርክር ግራ ቀኙ ወጪያቸውን በየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.