No summary available.
መጋቢት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሤ አመልካች፡- ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ - ተስፊዬ ምንዲገኝ ቀረበ ተጠሪ፡- ወ/ሮ በርገኔ ኢንኮ አልቀረበም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የመንግሥት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ድንጋጌዎችን በመተላለፍ የተወሰደ የጡረታ አበል /ገንዘብ/ ይመለስልኝ በማለት አመልካች በመሰረተው ክስ መነሻነት የተደረገውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት በወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች ተጠሪን የከሰሰው በጡረታ መለያ ቁጥር ወ/407216 ተመዝግቦ ከጥቅምት 1 ቀን 83 ዓ.ም ጀምሮ በየወሩ የጡረታ አበል ሲቀበል የቆየ ሲሆን፣ በተከሰሰበት ወንጀል በመጋቢት 23 ቀን 1995 ዓ.ም የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተፈርድበታል። ስለዚህ የጽኑ እስራት ቅጣት ከተወሰነበት በኋላ ከሕጉ ውጪ የወሰደው ገንዘብ /ብር 7,892.27/ ከነወለደ ይመልስ ዘንድ ይወሰንልኝ በማለት ነው። ተጠሪ በበኩለ ለክሱ በሰጠው መልስ የጡረታ አበለን በኃይል አልተቀበልኩም። በወንጀል ከተፈረደብኝ በኋላ ገንዘቡን የወሰድኩት ከፊዮቹ እኔ ጋ እየመጡ ስለሰጡኝ በመሆኑ የምመልስበት ምክንያት የለም በማለት ተከራክሮአል። ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ የሁለቱን ወገኖች ክርክር የመረመረ ሲሆን፣ በመቀጠልም ተጠሪ በወንጀል ተከሶ ከተፈረደበት በኋላ በሥራ ላይ ያለው የመንግስት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁ.345/95 ተጠሪ የወሰደውን ገንዘብ ለማስመለስም ሆነ ለወደፉቱ እንዲይከፈለው ለማድረግ የሚያስችል አይደለም የሚል ምክንያት በመስጠት ክሱን ውድቅ አድርጎአል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት ጠ/ፍ/ቤትም ውሳኔው ጉድለት የለበትም በማለት የአመልካችን ይግባኝ ሰርዞአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ኀዲር 15 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልቱ እንዱታይ የተደረገው የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ በሥር ፍ/ቤቶች ውድቅ የተደረገው በአዋጅ ቁ.345/95 አንቀጽ 52/1/ የተቀመጠውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ስለመሆን አለመሆኑ ሉመረመር ይገባል በመባለ ነው። በመሆኑም ይህን ነጥብ አቤቱታው ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከሥር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር እና ከተሰጠው ውሳኔ ይዘት መገንዘብ እንደቻልነው ተጠሪ በተከሰበበት ወንጀል ጥፊተኛ ሆኖ የተገኘው እና የቅጣት ውሳኔ የተላለፈበት በመጋቢት 23 ቀን 1995 ዓ.ም ስለመሆኑ አላከራከረም። ቅጣቱም የእድሜ ልክ ፅኑ እሥራት እንደሆነ ተመልክተናል። አመልካች ክስ የመሰረተው ሦስት ዓመት እና ከዚያ በላይ ፅኑ የእሥራት ቅጣት የተወሰነበት ተጧሪ የጡረታ መብቱን ያጣ ዘንድ በመንግሥት ሰራተኞች የጡረታ /ማሻሻያ/ አዋጅ ቁ.5/1967 አንቀጽ 34 ተደንግጓል የሚል መነሻ ምክንያት በመያዝ ነው። ክሱን የሰማው ፍ/ቤት የአመልካችን ክስ ውድቅ ያደረገው ተጠሪ በወንጀል ተከሶ ቅጣቱ በተወሰነበት ጊዜ ሥራ ላይ የነበረው የመንግሥት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁ.345/1995 ሥራ ላይ ያለ አይደለም።
ተፈፃሚነት የላለው እና ተከሣሽ የተቀበለውን ገንዘብ ለማስመለስም ሆነ ለወደፉቱም እንዲይከፈለው ለማገድ የሚችልም አዋጅ አይደለም የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት ነው።
በበኩላችን እንዲየነው ለክርክሩ አወሳሰን በቅደም ተከተል ሉታዩ የሚገባቸው አዋጆች አዋጅ ቁ.5/1967 እና አዋጅ ቁ.345/1995 ናቸው። የመጀመሪያው “የመንግሥት ሰራተኞች የጡረታ /ማሻሻያ/ አዋጅ ቁ.5/1967 ዓ.ም” በሚል የወጣው ሲሆን፣ ተጧሪ የነበረ የመንግሥት ሰራተኛ የጡረታ መብቱ የሚያጣበትን ሁኔታ በአንቀጽ 34 ደንግጎአል። ይህ አንቀጽ “የወንጀል ቅጣት” የሚል ርእስ ያለው ሁኖ ይዘቱም፡- "አንድ የመንግሥት ሰራተኛ ወይም ጡረተኛ ተከሶ ጥፊተኛ መሆኑ በሕግ በተቋቋመ ፍ/ቤት ሲረጋገጥና ቢያንስ የሦስት ዓመት ጽኑ እሥራት ቅጣት ሲወሰንበት የጡረታ መብቱን ያጣል። ወይም በመከፈል ላይ ያለውን የጡረታ አበል ይቀርበታል።" የሚል ነው። ይህ አዋጅ የወጣው ቀደም ሲል የወጣውን አዋጅ ቁ.209/55 `ን‘ ለማሻሻል ሲሆን በዚህ መልክ የተሻሻለው አዋጅ /ቁ.ቁ.209/55/ ደግሞ ከሰኔ 1 ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ በዋለው “የመንግሥት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁ.345/1995” ተሽሮአል /ተተክቶአል/። የሥር ፍ/ቤት የአመልካችን ክስ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ምክንያት ሲታይም የቀድሞውን አዋጅ በሻረው አዱሱ አዋጅ ተጧሪ የነበረ የመንግስት ሰራተኛ የጡረታ መብቱን ስለሚያጣበት ሁኔታ በሚመለከት በግልጽ ያስቀመጠው ድንጋጌ የለም የሚል መነሻ እንዲለው መገመቱ አያስቸግርም።
እንደሚታየው የቀድሞዎቹ አዋጆች ማለትም ቁ.5/67ም ሆነ ቁ.209/55 በአዋጅ ቁ.345/95 ሙለ በሙለ እስከተተኩ ድረስ ለተያዘው ክርክር አወሳሰን በዋቢነት ሉጠቀሱ አይችለም። በልላ በኩል ግን እነሱን የተካው አዱሱ አዋጅ ለክርክሩ አወሳሰን ስላለው አግባብነት በሚመለከት ሉፈተሹ የሚገባቸው ድንጋጌዎችን ስለመያዝ አለመያዙ መመልከት ተገቢ እንደሆነ ልብ ልባል ይገባል። በብዙ አዋጆች እንደሚታየው አዋጅ ቁ.345/95 ‘ም‘ የመሸጋገሪያ ድንጋጌ አለው። ይህም በአንቀጽ 52 የተቀመጠውን ሲሆን፣ አዋጁ ከመጽናቱ በፉት ለተፈጠሩ ሕጋዊ ሁኔታዎች ቀደም ሲል ሲሰራባቸው የነበሩ ሕጎችና መመሪያዎች ተፈፃሚ እንደሚሆኑ በንዐስ አንቀጽ/1/ ባስቀመጠው ድንጋጌ አመልክቷል። ቀጥለው ያለት ንኡስ አንቀጽ /2/ እና /3/ም በተመሣሣይ ሁኔታ አዋጁ ከመጽናቱ በፉት የነበሩ አሰራሮች እንደሚቀጥለ ያመለክታለ።
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስ በአዋጅ ቁ.5/1967 አንቀጽ 34 የተቀመጠው የጡረታ መብት የሚታጣበት አግባብ በአዋጅ ቁ.345/95 በግልጽ አልተሻረም። ይልቁንም በአዋጁ የተፈጠሩ ሕጋዊ ሁኔታዎችም ሆኑ ሲሰራባቸው የነበሩ ሕጎችና መመሪያዎች በነበሩበት ሁኔታ ተፈፃሚ እንደሚሆኑ ነው የኋለኛው አዋጅ /ቁ.345/95/ በግልጽ ያመለከተው። በወንጀል ተከሶ ሦስት ዓመት ጽኑ የእሥራት ቅጣት የተወሰነበት ተጧሪ የጡረታ መብቱን እንዱያጣ እየተደረገ እንደቆየ ግልጽ ነው። የአዋጁ አስፈፃሚ የሆነው የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ /አመልካች/ ሥራውን ሲሰራ የቆየው የአፈፃፀም መመሪያ እያወጣ እንደሆነም ማሰቡ ተገቢ ነው። በመሆኑም ተጠሪ በወንጀል ተከሶ ጥፊተኛ ሆኖ የተገኘው እና በእድሜ ልክ ጽኑ እሥራት እንዱቀጣ የተወሰነበት አዋጅ ቁ.345/95 ሥራ ላይ ባለበት መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ የጡረታ መብቱን እንዱያጣ መደረጉ ተገቢ ነው። የሥር ፍ/ቤቶች የተሳሳተ መደምደሚያ ላይ ሉደርሱ የቻለት ሥራ ላይ የነበረው አዋጅ ቁ.345/95 በአንቀጽ 52 ያስቀመጠውን ድንጋጌ ባለመመርመራቸው እና በአግባቡ ባለመተርጎማቸው ነው። ከዚህ የተነሣም አቤቱታው የቀረበበት ውሳኔ በሕጉ አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ችለናል። ተከታዩንም ወስነናል።
የወላይታ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 11964 ሰኔ 22 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ጠ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 30909 መስከረም 27 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
ተጠሪ የጡረታ መብቱን ካጣ በኋላ የወሰደው ገንዘብ ብር 7,892.27 /ሰባት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ሁለት ብር ከሃያ ሰባት ሣንቲም/ ለአመልካች ይመልስ ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.