No summary available.
የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤላክትሪክ ኃይል ኮርፕሬሽን ደቡብ ሪጅን ሰርከብርሃን ተክላ ቀረበ ተጠሪ፡- አቶ ተፈራ ሹና የቀረበ የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የተነሳውን የስራ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በይርጋ አለም ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ ያኔ ከሣሽ የነበረው ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተው የስራ ውላ ከሕግ ውጪ ስላቋረጠብኝ ውዝፍ ደመወዜን በመክፈል ወደስራዬ እንዱመልሰኝ ይወሰንልኝ በማለት ነው።
አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርቧል። አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያነሳው ነጥብ ተጠሪ ወደ ስራ ልመለስ በማለት ያቀረቡት ክስ በሶስት ወር ይርጋ የሚታገድ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃ ደግሞ የስራ ውለ ሉቋረጥ የቻለው ተጠሪ ተመድበው በሚሰሩበት በይርጋዓለም ዱስትሪክት በለኩ ቅርንጫፍ ጣቢያ በተለያዩ ጊዜያት በእዲ ምክንያት ተቆርጦ ከተመለሰ ቆጣሪ የኤላክትሪክ ፍጆታ ወደ ድርጅቱ መግባት የሚያስፈልገውን ክፍያ ለእራሱ አውል ከሕጉ ውጪ በሆነ መንገድ ከአስራ ሶስት በላይ የሆነ ቆጣሪ ለመግጠም በዱስፔሉን ጉድለት በሪጅኑ የዱስፔሉን ኮሚቴ አጣርቶ በሕብረት ስምምነትና በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27(1(ሐ))እና((መ)) ነው በማለት ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል።
ክሱን የሰማው ፍ/ቤትም ክርክሩን ከመረመረ በኋላ ተጠሪ ለስራ የታገደት በስራ ላይ ባጠፈት ጥፊት ነው ፣ ይህ ጥፊትም በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27(1(ሐ))((መ)) መሰረት የስራ ውለን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ የሚያስችል ነው በማለት የስራ ውለ የተቋረጠው በሕጉ መሰረት ነው ሲል ወስኗል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ ውሳኔውን በመቃወም ለሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረባቸው ክርክሩ በድጋሚ የተሰማ ሲሆን ፣ በመጨረሻም ፍ/ቤቱ በይርጋዓለም ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በመሻር ተጠሪ የአስር ወር ውዝፍ ደመወዝ ተከፍልአቸው ወደ ስራው ይመለስ በማለት ወስኗል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪ በስራ ላይ እያለ የአመልካችን ድርጅት ጥቅም ለግል ጥቅማቸው ማውላቸውና ማጭበርበራቸው በዱስፔሉን ኮሜቴ ተረጋግጦ እያለ ይኸው ማስረጃ በቂ አይደለም ተብል ተጠሪ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም የዱሲፔሉን ኮሜቴ ውሳኔ በቂ አይደለም ተብል ተጠሪ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በሰጡት የፅሐፍ መልስ የዱስፔሉን ኮሜቴ የዲኝነት ሥልጣን የላለው አካል በመሆኑ ውሳኔው ውድቅ መደረጉ ባግባቡ በመሆኑ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሉፀና ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። አመልካች በበኩለ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ከአላቸው ውሳኔዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ክስ የመሰረቱት ከአመልካች ጋር የመሰረቱት የስራ ውል ከሕግ ውጪ ተቋርጧል በሚል ሲሆን አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ የስራ ውለ የተቋረጠው ተጠሪ በስራ ላይ በፈፀሙት የማጭበርበርና የእምነት ማጉደል ድርጊት ምክንያት መሆኑን ገልፆ መከራከሩንና ግራ ቀኙ ወገኖች ክርክራቸውን ይደግፈልናል የሚሎቸውን ማስረጃዎችን ማቅረባቸውን ፣ የተጠሪ ምስክሮች ቃል የስራ ውለ ከሕጉ ውጪ መቋረጡን ለማስረዲት የማይችል መሆኑ በሁለቱም ፍርድ ቤቶች ስምምነት ያገኘ ነጥብ መሆኑን ፣ የበታች ፍርድ ቤቶች የተለያዩበት ነጥብ የአመልካች መስሪያ ቤት የሪጅን ዱስፔሉን ኮሜቴ ውሳኔ በማስረጃነት ስላላው ተቀባይት ላይ መሆኑን ነው። አመልካች በዱሲፔሉን ኮሜቴው የተሰጠው ውሳኔ ተጠሪ በስራ ላይ የማጭበርበርና የእምነት ማጉደል ድርጊት መፈፃማቸውን እንደሚያስረዲ ገልፆ ይኸው የዱስፔሉን ኮሜቴ ውሳኔ የአመልካችን ክርክር የሚደግፍ መሆኑን የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚያሳይ ሲሆን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዱሲፔሉን ኮሜቴው ውሳኔ የተጠሪን የማጭበርበር ወይም የእምነት ማጉደል ድርጊት ለማስረዲት በቂ አይደለም በማለት ውድቅ ያደረገው የኮሚቴው ውሳኔ በገልለተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠ አይደለም ፣ በኮሜቴው ፉት የተሰሙት ምስክሮችም በፍርድ ቤት ያልተሰሙ በመሆኑ የኮሜቴው ውሳኔ ተጠሪ የአመልካችን ጥቅም ለራሳቸው ጥቅም ማዋላቸውን ወይም የማጭበርበር ድርጊት መፈፀማቸውን አያሳይም በሚል ምክንያት ነው። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው የኮሚቴው ውሳኔ በቂ አይደለም ተብል የሥራ ውለ ከሕግ ውጪ ነው የተቋረጠው በማለት ውሳኔ የመሰጠቱን አግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር ፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከላይ እንደተገለፀው አመልካች ተጠሪን ከስራ እንዱሰናበት ያደረገው ተመድበው በሚሰሩበት የይርጋዓለም ዱስትሪክት ለኩ ንዐስ ጣቢያ በተለያዩ ወቅቶች በእዲ ምክንያት ተቆርጠው ተመላሽ የተደረጉትን የኤላክትሪክ ፍጆታ ቆጣሪዎችን ለአመልካች መግባት የነበረበት ክፍያ ለግል ጥቅሙ በማዋለ በሕገ ወጥ መንገድ ከአስራ ሶስት የፍጆታ ቆጣሪዎች በላይ በመግጠም በአመልካች ድርጅት ጥቅም ላይ ጉዲት አድርሰዋል በማለት ሲሆን ይህ የተጠሪ አድራጎት ስለመኖሩ የዱሲፔሉን ኮሜቴው ጉዲዩን አጣርቶ በፍሬ ነገር ረገድ አረጋግጧል። አመልካች የስራ ውለን ያቋረጠው ይህን መሰረት በማድረግ እንደሆነም አላከራከረም። በአሰሪና ሰራተኛ መካከል ተመስርቶ የነበረውን የስራ ውል ስለሚቋረጥባቸው ሕጋዊያን ምክንያቶች በሚመለከት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 በዝርዝር ተመልክቶአል። በዚህ መዝገብ ለተያዘው ክርክር አወሳሰን ተገቢነት ያለው የአዋጁ አንቀጽ 27 ሲሆን፣ ይህም ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል የሚቋረጥባቸውን ምክንያቶች በዝርዝር አስቀምጦአል። ተጠሪ በአሰሪው (በአመልካች) ጥቅም ላይ በማጭበርበር ድርጊት ጉዲት ማድረሱ የዱሲፔሉን ኮሜቴ ውሳኔ በሰነድ ማስረጃነት ቀርቦ ተረጋግጧል። በዱሲፔሉን ኪሜቴ የተሰጠ ውሳኔ በስራ ክርክር ችልት ለሚቀርብ ክርክር በዱስፔሉን ኮሚቴ ፉት ቀርበው የመሰከሩት ምስክሮች የስራ ክርክር በሚሰማው አካል ወይም ፍርድ ቤት ፉት ቀርበው ካልተሰሙ የእነዚህን ምስክሮች ቃል መሰረት በማድረግ የተሰጠ የዱስፔሉን ኮሚቴ ውሳኔ በስራ ክርክር ጉዲይ የሰራተኛውን ጥፊት ለማስረዲት ለማስረጃነት ላቀርብ አይገባም የሚባልበት ሕጋዊ አግባብ የለም። በመሆኑም የዱሲፔሉን ኮሚቴ ውሳኔ ለማስረጃነት ላቀርብ የሚገባ ሲሆን ይኸው የሰነድ ማስረጃ በተጠሪ ማስረጃ ያልተስተባበለ መሆኑን የክርክሩ ሂደት ያሳያል። የኮሚቴው ውሳኔ ተጠሪ በስራ ላይ የማጭበርበርና በአመልካች ላይ ጥቅም ላይ ጉዲት ማድረሳቸውን የሚያረጋግጥ በመሆኑና እነዚህ ድርጊቶች ደግሞ ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል ከሚያቋርጡ ምክንያቶች መካከል እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27(1(ሐ)) እና((መ)) ስር ተመልክተዋል። እንግዱህ ሕጉ ይህን ያሕል ግልጽ ከሆነ ከዚህ በተቃራኒ መወሰን የሚቻልበት ምክንያት አይኖርም። ሲጠቃለል የስራ ውለ የተቋረጠው በሕግ አግባብ መሆኑ ግልጽ ሆኖ ሳለ የሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በተቃራኒው መወሰኑ ውሳኔው በማስረጃ አቀባበል ረገድ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
የሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 23119 ጥቅምት 10 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረው የስራ ውል የተቋረጠው በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 27(1(ሐ)እና((መ)) በመሆኑ በሕግ አግባብ ነው ብለናል። ስለዚህም የይርጋዓለም መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሥራ ውለ የተቋረጠው በሕጉ አግባብ ነው በማለት በመ/ቁ.
00612 ሰኔ 09 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው የውሳኔ ክፍል በውጤት ደረጃ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቶአል።
No topics extracted.