No summary available.
የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካቾች፡- አቶ ምትኩ ኃይለ ጠበቃ ለገሰ ማሞ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ መስፍን ጥላሁን የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ጋር ተያያዥነት ያለው እና በስራ ላይ የደረሰን ጉዲት ካሳ መሰረት ያደረገ ክርክር የሚመለከት ሲሆን የተጀመረው በደቡብ ብሓ/ብሓ/ህዝቦች ብሓ/ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት መደበኛ ችልት ነው። ቀርቦ የነበረውም ክስ በተጠሪ ድርጅት ውስጥ ላልተወሰነ ጊዜ በእንጨት መሰንጠቂያ ማሽኒስትነት በወር ብር 750 /ሰባት መቶ ሀምሳ ብር/ እየተከፈለኝ በማገልገል ላይ እያለሁ በጥር 08 ቀን 2002 ዓ.ም የማሽኑ መጋዘን በግራ እጅ ላይ ባደረሰው የመቆረጥ አደጋ ሶስት ጣቶቼ ተቆርጠው ከፍተኛ ጉዲት ደርሶብኛል። በዚህ የተነሳ ከዚህ በኋላ ስራ ላይ ተሰማርቼ ስራ መስራት እንዲልችል አድርጎኛል። በመሆኑም በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 109/1/ መሰረት ለደረሰብኝ ጉዲት ካሳ እና የህክምና ወጪ እንዱከፈለኝ በማለት ባጠቃላይ ብር 45,000 /አርባ አምስተ ሺህ ብር/ እንዱከፍለኝ በማለት ነው። የቀረበው ክስ ለተከሳሽ ደርሶት መልስ እንዱሰጥበት ታዞ ባቀረበው መልስ አመልካች በድርጅቱ ውስጥ በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 10/1/ሐ/ሰ/መሰረት የስራ መብዛት በሚኖርበት ጊዜ ስራው እስኪያልቅ ድረስ ብቻ ለመስራት የተዋዋለ በመሆኑ፣አመልካች ከተጠሪ ጋር ብቻ ሳይሆን ከላላ ስራ ተቋራጭ ጋርም የሚሰራ በመሆኑ፣የጉዲት መጠኑንም የሚያሳይ ነገር ያላቀረበ በመሆኑ፣አመልካች ጉዲት የደረሰበት አዕምሮውን በሚገባ መቆጣጠር በማይችልበት ሁኔታ በመጠጥ ሰክሮ በስራ ላይ በመገኘት በመሆኑ በራሱ ላይ ሆነ ብል እንዲደረሰ ስለሚቆጠር፣በወቅቱ ከሳሽ ወደ ድርጅቱ ሲመጣ ሰክሮ ስለነበር ወደ ስራ እንዲይገባ በአሰሪው ጭምር ትዕዛዝ ቢሰጠውም እምቢተኛ በመሆን በመስራት ላይ እንዲለ ጉዲት የደረሰበት በመሆኑ፣ኃላፉነት የላለብኝ ቢሆንም እንኳ በሰብአዊነት የህክምና ወጪውን የሸፈንኩ በመሆኑ፣ከዚያም በመዲን ወደ ስራው ተመልሶ ስራውን ሲሰራ ቆይቶ የማሽን ካፕስተሮችን በመለወጡ በፈጸመው ጥፊት ምክንያት ከስራ የተሰናበተ በመሆኑ ያቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም የሚል ነው።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የክልለ የመጀ/ደረጃ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት እና ማስረጃ በመቀበል ከሳሽ በስራ ገበታው ላይ የተገኘው በስካር መንፈስ ስለመሆኑ እና በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ መስራት እንደላለበት የተላለፈለትን የስራ ኃላፉውን ትዕዛዝ በመተላለፍ በመስራት ላይ እንዲለ የደረሰበት ጉዲት በመሆኑ በስራ ላይ የደረሰ ጉዲት ነው ተብል የማይወሰድ በመሆኑ የቀረበው የካሳ ክፍያ ጥያቄ ውድቅ ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። ከሳሽ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት የበታች ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.348/1/ መሰረት አጽንቶታል። ሆኖም የክልለ የሰበር ሰሚ ችልት የቀረበለትን ቅሬታ በመቀበል የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት በግራ ቀኙ መካከል የስራ ውል ስለመኖሩ ተከሳሽ /የአሁን አመልካች/ ያረጋገጠው ነጥብ ባለመኖሩ፣ስራው ደግሞ የአደገኝነት ጠባይ ያለው በመሆኑ እና በፍትሐብሕር ህግ ቁ.2088/1/ መሰረት የኃላፉነት ደንቦችን በመጥቀስ አመልካች ከኃላፉነት ሉድን ስለማይችል የደረሰውን ጉዲት የመካስ ኃላፉነት አለበት በማለት የካሳ መጠኑን በርትህ 20,000 ብር/ሀያ ሺህ ብር/ እንዱከፍል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚሁ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ የግራ ቀኙን ክርክር በጽሐፍ ሰምተናል። ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ከተያዘው ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመረውም ጉዲዩ ቀደም ሲል ለዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ሲባል ተይዞ የነበረው ጭብጥ በዚህ ጉዲይ አመልካች ኃላፉ ነው የመባለን አግባብነት ከአዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 96/ሀ/እና/ለ/ አኳያ ለመመርመር በሚል በመሆኑ ከዚሁ ጭብጥ አኳያ የተያዘውን ጉዲይ ተመልክቶ እልባት መስጠት ተገቢነት ይኖረዋል ማለት ነው።
በዚሁ መሰረት ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ በመጀመሪያ ደረጃ የክልለ የሰበር ሰሚ ችልት የአሁን ተጠሪ የአመልካች ድርጅት ሰራተኛ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም በሚል ያነሳውን ነጥብ በተመለከተ የአሁን ተጠሪ ራሱ ክሱን ሲያቀርብ የአመልካች ድርጅት ሰራተኛ ስለመሆኑ እና በወር የሚያገኘውን የደመወዝ መጠን በማመልከት በመሆኑ ተጠሪ የአመልካች ድርጅት ሰራተኛ ስለመሆኑ አከራካሪ ባልሆነበት ሁኔታ እና ተጠሪም ራሱ ክሱን ሲያቀርብ አመላክቶ ያቀረበውን ነጥብ ፍርድ ቤቱ በራሱ ማንሳቱ እና ሰራተኛ ስለመሆኑ አመልካች አላረጋገጠም ወደ የሚለው መደምደሚያ መድረሱ አግባብነት ያለው ሁኖ አልተገኘም። በመሆኑም በግራ ቀኙ መካከል የተጠሪ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ሰራተኛ መሆን አከራካሪ ባልሆነበት ሁኔታ የክልለ የሰበር ሰሚ ችልት በራሱ በማንሳት ሰራተኛ አይደለም ወደሚለው መደምደሚያ መድረሱ ተቀባይነት ያለው ድምዲሜ ባለመሆኑ አልተቀበልነውም።
በልላ በኩል በበታች ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡትን ፍሬ-ነገሮች ስንመለከት ተጠሪ በስራ ላይ ደረሰ የተባለው ጉዲት በደረሰበት ዕለት ጠዋት ወደ ስራ ከገባ በኋላ፣የስራ ኃላፉው ለላላ ስራ ሲወጣ ተከትል እንደወጣ እና የስራ ኃላፉው ተመልሶ ሲመጣ ተጠሪም ተከትልት እንደመጣ፣በዚህን ወቅት ተጠሪ በስካር ውስጥ እንደነበር ወይም ይንገዲገድ እና የመጠጥ ጠረንም እንደነበረዉ፣ከዚህ የተነሳ አመልካች እንዲትሰራ በማለት አስጠንቅቆት እንደነበር፣ሆኖም አመልካች ለስራ ሲወጣ አስፈቅዲለሁ በማለት ለመደወል በሚል የሞባይል ስልክ በመያዝ እንደወጣ፣ተመልሶም አሰሪው ፈቅድልኛል በማለት እምቢተኛ በመሆኑ መስራት እንደጀመረ፣ስራውን መስራት ከጀመረ ብዙም ሳይቆይ አደጋው እንደተከሰተ፣ከአደጋውም በኋላ አመልካች ወደ ተለያዩ የህክምና ቦታዎች የወሰደው እና በመዲንም ስራ የጀመረ ስለመሆኑ፣ ሆኖም ስራውን ከጀመረ በኋላ አንዱቀይር የተሰጠውን የማሽን ካፕስተሮችን በማጥፊቱ በፈጸመው ጥፊት ከስራ የተሰናበተ ስለመሆኑ ነው።
ከላይ የተረጋገጡትን ፍሬ-ነገሮች ይዘን አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች ስንመለከት በእርግጥ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 96/1/ን ስንመለከት አንድ አሰሪ በስራ ላይ በሰራተኛው ለሚደርስ ጉዲት ለመካስ ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ ይደነግጋል። ሆኖም ጉዲት የደረሰበት ሰራተኛ ሆነ ብል በራሱ ላይ ላደረሰው ማንኛውም ጉዲት አሰሪው ኃላፉነት እንደላለበት፣በተለይም አሰሪው አስቀድሞ በግል የሰጡትን የደኅንነት መጠበቂያ መመሪያዎች በመጣስ ወይም የአደጋ መከላለከያ ደንቦችን በመጣስ ወይም አካለን ወይም አዕምሮውን በሚገባ ለመቆጣጠር በማይችልበት ሁኔታ በመጠጥ ወይም በአደንዛዥ ዕፅ ሰክሮ በስራ ላይ በመገኘቱ የደረሰ ጉዲት በሰራተኛው ሆን ተብል የደረሰ ተደርጎ ስለሚወሰድ አሰሪው ለመካስ ኃላፉነት የላለበት ስለመሆኑ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 96/ሀ//ለ/ ስር ተደንግጎ ይገኛል።
ተጠሪ ጉዲት በደረሰበት ቀን ሰክሮ በስራው ላይ የተገኘ ስለመሆኑ፣እንዲይሰራ ተብል በስራ ኃላፉውም የተሰጠውን መመሪያ በመጣስ በእምቢተኝነት ወደ ስራ በመግባት ስራ የጀመረ ስለመሆኑ እና በወቅቱም ይንገዲገድ የነበረ ስለመሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ የደረሰው ጉዲት በስራ ላይ እንደደረሰ ተቆጥሮ ለደረሰው ጉዲት አሰሪው/አመልካች/ ኃላፉነት የለበትም በማለት በክልለ የመጀ/ደረጃ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰኑ በአግባቡ ነው ከሚባል በስተቀር የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለመኖሩ አያሳይም። የክልለ የሰበር ሰሚ ችልትም ግራቀኙ ያልተካካደበትን እና ተጠሪ በአመልካች ድርጅት ሰራተኛ ስለመሆኑ ተጠሪ ራሱ ባልካደበት ሁኔታ ሰራተኛ መሆኑ አልተረጋገጠም በሚል፣በግራቀኙ መካከል ተፈጻሚነት ያለው የህግ የአሰሪና ሰራተኛ ስለመሆኑም በላከራከረበት ሁኔታ የፍተሐብሓር ህግ ድንጋጌ በመጥቀስ እና የአመልካች ድርጅት ስራ የአደገኝነት ባሕርይ ያለው ነው በማለት አመልካች ኃላፉነት አለበት ወደ ሚለው መደምደሚያ መድረሱ አግባብነት የላለውና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ባጠቃላይ በተጠሪ ላይ የደረሰው ጉዲት በስራ ላይ የደረሰ ጉዲት ያለመሆኑ ከተረጋገጡት ፍሬነገሮች እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻል ሆኖ እያለ የክልለ የሰበር ሰሚ ችልት የበታች ፍርድ ቤቶች ሰጥተውት የነበረውን ውሳኔ በመሻር አመልካች ኃላፉነት አለበት በማለት መወሰኑ አግባብነት የላለውና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል።
በመሆኑም ቀጥል የተመለከተዉን ውሳኔ ስጥተናል።
የደቡብ ብሓ/ብሓ/ህዝ/ብሓ/ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ሰሚ ችልት በመዝ.ቁ.51342 በቀን 22-7-2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.348(1) መሰረት ተሽሯል።
የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝ ቁ.08825 በቀን 25-1-2003 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የሀዋሳ ከተማ የመጀ/ደ/ፍርድ ቤት በመዝ.ቁ. 00347 በቀን 15-11-2002 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.348(1) መሰረት ጸንቷል።
በአሁን ተጠሪ ላይ የደረሰው ጉዲት በስራ ላይ የደረሰ ጉዲት ባለመሆኑ አመልካች የደረሰውን ጉዲት ለመካስ ኃላፉነት የለበትም ብለናል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.