No summary available.
ጥር 16 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሀመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአገልግልት ክፍያ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪዎች ባሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው።የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡-በተጠሪ ድርጅት መጋቢት 05 ቀን 1983 ዓ.ም በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ተቀጥረው ሲሰሩ ቆይተው በየካቲት ወር 2003 ዓ.ም ስራቸውን በገዛ ፈቃዲቸው የለቀቁ ቢሆንም ተጠሪ የአገልግልት ክፍያ ሉከፍላቸው ፈቃዲኛ ላሆን ያለመቻለን በመግለጽ የአገልግልት ክፍያ እንዱከፈላቸው፣ክፍያው ለዘገየበት ጊዜ ደግሞ ተገቢውን ክፍያ እንዱፈጽም እንዱሁም ለ3ኛ ተጠሪ ያላግባብ የቆረጠባቸውን የስድስት አመት ከስድስት ወር እረፍት ወደ ገንዘብ ተለውጦ እንዱከፍላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስም 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች በድርጅቱ ከ20 ዓመታት በላይ ማገልገላቸውን፣3ኛ አመልካችም ከ10 ዓመት በላይ ማገልገላቸውን ገልፆ አመልካቾች በጡረታ አዋጅ ቁጥር 345/1995 አንቀጽ 2 ንዐስ ቁጥር 13 እና 14 ድንጋጌዎች መሰረት የጡረታ አበል ተመላሽ ተጠቃሚ ስለሚሆኑ የስራ ስንብት ክፍያ ሉከፈላቸው አይገባም፣የታመኑ ክፍያዎች ለአመልካቾች ተሰጥተዋል፣3ኛ አመልካችም የተቆረጠባቸው የአመት እረፍት ፈቃድ የለም በማለት ክሱ ውድቅ እንዱሆን ገልጾ ተከራክሯል።ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማና ከማህበራዊ ዋስትና አመልካቾች የጡረታ ተሸፊኝ ለመሆን የሚያበቃ የአገልግልት ጊዜ እና የእድሜ ጣሪያ ያሟለ መሆን ያለመሆኑን በሚመለከት ተጣርቶ እንዱቀረብለት ትእዛዝ ሰጥቶ ይኸው አካል አመልካቾች የጡረታ ተሸፊኝ ያለመሆናቸውን ከአረጋገጠለት በሁዋላ ጉዲዩን መርምሮ ተጠሪ ለአመልካቾች የስራ ስንብት ክፍያ ሉከፍል ይገባል፣ላልች የዲኝነት ጥያቄዎች ግን ተቀባይነት የላቸውም በማለት ወስኗል፡ተጠሪ የስራ ስንብት ለአመልካቾች ሉከፍል ይገባል ተብል በተሰጠው የውሳኔ ክፍል ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ አመልካቾች የጡረታ ተመላሽ ተጠቃሚ ናቸው በሚል ምክንያት የስራ ስንብት አገልግልት ክፍያ አይገባቸውም ወደሚለው ድምዲሜ ደርሶ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሽሮታል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም አመልካቾች የተመለሰላቸው ራሳቸው ያዋጡት የጡረታ ገንዘብ ሁኖ እያለ የፋዳራለ ከፍተኛ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሙለ የጡረታ መብት ተጠቃሚ እንደሆኑ በመቁጠር የአገልግልት ክፍያ አይገባቸውም በማለት መወሰኑ የአዋጅ ቁጥር 345/1995 አንቀፅ 2(13)(14) እና አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 39 እና ይህንኑ ድንጋጌ ለማሻሻል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 494/1998 አንቀፅ 2(ሸ) ድንጋጌን ያላገናዘበ ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።አቤቱታው ተመርምሮም አመልካቾች የጡረታ መዋጮአቸው ተመላሽ የተደረገላቸው በመሆኑ የስራ ስንብት ክፍያ ሉከፈላቸው አይገባም የመባለን አግባብነት ለመመርመር ሲባል መዝገቡ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ አመልካቾች የጡረታ ተመላሽ የሆነውን ገንዘብ ከወሰደ የስራ ስንብት ክፍያ ሉያገኙ የሚችለበት ሕጋዊ መሰረት የለም በማለት በጽሐፍ መልሱን ሰጥቷል።አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋለው።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሯል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካቾች በተጠሪ ድርጅት ውስጥ ከአምስት አመታት በላይ ያገለገለና ስራቸውን በገዛ ፈቃዲቸው የለቀቁ መሆኑን፣አመልካቾች ለጡረታ መብት የሚያበቃ እድሜና ያገልግልት ዘመን ላይ ያልደረሱ መሆኑን የሚመለከተው አካል ማረጋገጡንና አመልካቾች ራሳቸው ለጡረታ ያዋጡት 4% መዋጮ ብቻ ተመላሽ የሆነላቸው መሆኑን ነው።
ተጠሪ የስራ ስንብት ክፍያውን መክፈል የለበኝም የሚለው የጡረታ መዋጮ የተመለሰላቸው በመሆኑ በጡረታው ሕግ መሰረት የጡረታ አበል ተጠቃሚነታቸው ተረጋግጧል የሚል የመከራከሪያ ነጥብ በማንሳት ነው።
ወደ ሕጉ ስንመጣ የፔሮቪደንት ፈንድ ሽፊን ያለው ወይም የጡረታ መብት ያለውና በጡረታ ሕግ የተመለከተው መደበኛ የጡረታ እድሜ ደርሶ ከስራ የተገለለ ሰራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት እንደላለው በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 (ማሻሻያ) አዋጅ ቁ. 494/98 አንቀጽ 2(2)(ሰ፣ሸ) ተመልክቶአል።ሰራተኛ የስራ ውለ ሲቋረጥበት የስራ ስንበት ክፍያ የሚፈጸምለት ለአሰሪው አገልግልት ስለሰጠና ሉቋቋመው የማይችል ድንገተኛ የገንዘብ ችግር እንዲይገጥመው በሚል እሳቤ መሆኑ ይታመናል።ይህ ከሕጉ በስተጀርባ ያለው አስተሳስብ ወይም ምክንያት ሲሆን በሕጉ እንደተመለከተው ሰራተኛው የፔሮቪደንት ፈንድ ሽፊን ወይም የጡረታ መብት ካለው ግን የስራ ውለ ቢቋረጥም፤ ገንዘብ ማግኘቱን ስለሚቀጥል (ስለቀጠለ) የስራ ስንብት ክፍያው አይከፈለውም።የጡረታ አበል ወይም የፔሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚነት ካለ የስራ ስንብት የማይከፈለው ከአንድ ምንጭ(አሰሪ) ሁለት ጊዜ ገንዘብ እንዲይከፈል ለመከልከል ታስቦ ነው።
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስ አመልካቾች የስራ ውለን ያቋረጡት በተጠሪ ድርጅት ውስጥ ከአምስት አመታት በላይ ካገለገለ በኋላ ነው ቢባልም፤በጡረታ ሕጉ መሰረት የጡረታ እድሜና አገልግልት ዘመን ላይ ስለመድረሳቸውና የጡረታ አበል የሚያገኙ ለመሆኑ ተጠሪ አላስረዲም።
አመልካቾች የስራ ውለን እንዲቋረጠ የጡረታ አበል ማግኘታቸውን ይቀጥላለ የሚል ክርክርም ሆነ ማስረጃ ከላለ ደግሞ ለስራ ስንብት መከፈል መሰረት የሆነውን በሕጉ በስተጀርባ ያለውን ምክንያት መሰረት በማድረግ የስራ ስንብቱን ክፍያ ማስከፈል የግድ ይሆናል። ሕጉ በዚህ መልክ ካልተተረጏመም ሰራተኛውን ለድንገተኛ የገንዘብ ችግር ማጋለጥ ይሆናል።ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 345/1995 አንቀጽ 2 ንኡስ አንቀጽ 13 እና 14 ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች መሰረት አድርጎ የሚከራከረው አመልካቾች ለጡረታ ያዋጡትን የራሳቸውን 4% ገንዘብ ወስደዋል በማለት ሲሆን አመልካቾችም ይህንኑ አይክደም። ስለሆነም የጡረታ መዋጮ ተመላሽ መሆን በሕጉ አነጋገር የጡረታ መብት ተጠቃሚነትን ያሳያል ወይ? የሚለው ጥያቄ መመለስ ያለበት ነው።
በዚህም መሰረት አመልካቾች ክሱን ሲመሰርቱ በስራ ላይ በነበረው በአዋጅ ቁጥር 345/1995 አንቀጽ 2(13) ስር አበል የሚለው ቃል የጡረታ መዋጮ ተመላሽንም የሚጨመር መሆኑን፣በአዋጁ አንቀፅ 21 ደግሞ ተመላሽ መዋጮ የሚሰጠው ከአስር አመት ያላነሰ፣ሃያ አመት ያልሞላ አገልግልት ፈጽሞ በራሱ ፈቃድ ስራውን ከለቀቀ ወይም ከሃያ አመት ያነሰ አገልገልት ፈጽሞ በአዋጁ ከተጠቀሱት ውጪ በሆነ ምክንያት ከስራ ከተሰናበተ ሰራተኛው የከፈለው አራት በመቶ 4% የጡረታ መዋጮ የሚመለስ መሆኑና በአዋጁ አንቀጽ 2(14) ደግሞ ባለመብት ማለት በአዋጁ መሰረት አበል የሚቀበል ወይም አበል ለመቀበል የሚያስፈልጉትን ሁኔታዎች የሚያሟላ ሰራተኛ ወይም ተተኪ መሆኑ ተመልክቷል።ይህ ድንጋጌ መታየት ያለበት ከአዋጅ ቁጥር 377/1996 ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 494/1998 አንቀፅ 2(1(ሸ)) ይዘት፣መንፈስ እና ዓላማ ጋር ተጣጥሞ ነው። በመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 345/1995 አንቀጽ 2(13 እና 14) እና 21 ድንጋጌዎች የተቀመጠውን ድንጋጌ አንድ ላይ ስንመለከተው የጡረታ መዋጮ የሚመለሰው የሰራተኛው ድርሻ ብቻ ነው።የአሰሪው መዋጮ የማይከፈል መሆኑን ድንጋጌዎቹ በግልፅ ያሳያለ። እንዱህ ከሆነ ሁለት ጊዜ ከአሰሪው ኪስ ገንዘብ ወጥቷል ልባል የሚችልበት አግባብ የለም። እንዱሁም ሰራተኛው ለአሰሪው ባበረከተው አስተዋጽኦ ምክንያትና የስራ ስንብት የማህበራዊ ዋስትና ሽፊን (Social Security Scheme) ተብል ከሚታሰብበት አግባብ አንፃር ሲታይ አመልካቾች ከተጠሪ የስራ ስንብት ክፍያ የማያገኙበት ምክንያት የለም።
ስለሆነም የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጡረታ አበል ተጠቃሚነት የሚለውን ሐረግ ብቻ ይዞ የአዋጁን ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ እንዱሁም ዓላማ ጋር ባግባቡ ሳይመረምር አመልካቾች የስራ ስንብት ክፍያ አይገባቸውም በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ መስከረም 5 ቀን 2004 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሸሯል።
በአሰሪ ዘንድ ከአምስት አመታት በላይ አገልግል በራሱ ፈቃድ ስራውን የለቀቀ ሰራተኛ እድሜውና የአገልገልት ዘመኑ የጡረታ መብት ተጠቃሚ የማያደርገው እስከሆነ ድረስ ራሱ ያዋጣውን መዋጮ ተመላሽ ሁኖለታል በሚል ምክንያት የስራ ስንብት አይከፈልም ለማለት የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት የለም ብለናል።
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሰኔ 28 ቀን 2003 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር በግራ ቀኙ የወጣውን ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ። መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.