No summary available.
ጥር 04 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካቾች፡- 1.አበባ ትራንስፕርት ኃ/የተ/የግል ማህበር ነ/ፈጅ ሰላማዊት ጌታቸው ቀረቡ 2. ባዜን የእርሻና ኢንዱስትሪ ልማት ኃ/የተ/የግል ማህበር ተጠሪዎች፡- አቶ አርጋው አበበ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ የግል የስራ ክርክር ሲሆን ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፋ/የመጀ/ደ/ፍ/ቤት በግራ ቀኙ መካከል የነበረውን ክርክር በመመልከት ተጠሪ በራሱ ፍቃድ ስራ መልቀቁን ተከትል የሚፈጸሙት የስራ ስንብት፣የአመት እረፍት እና ላልች ጥቅሞች ወርሃዊ ደመወዝን መሰረት በማድረግ ስለሚከፈለ እና እንደ ደመወዝ የሚታዩ በመሆናቸው ከተጠሪ ላይ የሚፈለጉ የተለያዩ ዕዲዎች አለ በማለት ለዕዲው ተብል ከስራ ሲሰናበት ሉቀነስበት አይገባም በማለት ውሳኔ በመስጠቱ እና ይግባኝ የቀረበለት የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.337 መሰረት በማጽናቱ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች በማመልከቱ ነው።
አመልካቾች ባቀረቡት አቤቱታ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞባቸዋል ያለዋቸውን ነጥቦች በማመልከት ያቀረቡ ሲሆን በቀን 27-7-2003 ዓ.ም በሁለት ገጽ የተጻፈ የቅሬታቸው ፍሬሃሳብ፡- በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 59(1) በግልጽ እንደሚደነግገው በዕዲ ሉያዝ የማይችለው ደመወዝ ብቻ ነው እንዱባልልን፤ አመልካቾች የተጠሪን ዕዲ የቀነሱት እንደፔሮቪደንት ፈንድ፣ የአገልግልት ክፍያ እና ከመሳሰለት ጥቅማ ጥቅሞች ላይ በመሆኑ ከተጠሪ ላይ ዕዲው መቀነሱ ተገቢ ነው ተብል እንዱወሰንልን የሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ታዞ ግንቦት 22 ቀን 2003 ዓ.ም በአንድ ገጽ በተጻፈ የጽሁፍ መልስ የሰጡ ሲሆን ፍሬ-ሃሳቡ፡- ያልተወራረደ ሂሳብ አለበት የሚለው አመልካች በመሆኑ፣ በዚህ ድርጅት ውስጥ ከአስር አመት በላይ ስሰራ ምንም ዓይነት ዕዲ የላለብኝ እና በየወሩ ሙለ ደመወዜ የሚከፈለኝ በመሆኑ፣ አሁን ስራ በመልቀቄ ምክንያት የአገልግልት ክፍያ ላለመፈጸም ሑሳቡን እንዲሻቸው ሰርተው ያቀረቡት በመሆኑ፣ዕዲው በትክክል ያለብኝ ስለመሆኑ በፍርድ ቤት ሳይረጋገጥብኝ አመልካች እንደፈለገው ቀንሶ እንዱሰጥ መደረግ ስለላለበት በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በአግባቡ እና የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት በመሆኑ እንዱጸናልኝ በማለት ተከራክሯል።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ ከተያዘው ጭብጥ አና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል።
እንደመረመረውም ጉዲዩ ለዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ሲባል ተይዞ የነበረው ጭብጥ ተጠሪ አላወራረደም የተባለውን ሑሳብ አመልካቾች ለተጠሪ ከሚከፍለት ክፍያዎች ላይ መቀነስ አይችለም ተብል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል በመሆኑ ከዚሁ ጭብጥ አኳያ ጉዲዩ ታይቶ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁ መሰረት ጉዲዩን ስንመረምር የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካቾች ተጠሪ ስራውን በገዛ ፍቃደ ሲለቅ ከሚከፈልለት ክፍያ ላይ ዕዲዎች አለበት በማለት ሉቀንስበት አይገባውም ወደ ሚለው መደምደሚያ የደረሰው ከስራ በመሰናበቱ ምክንያት ለተጠሪ የሚፈጸሙለት ክፍያዎች ከደመወዝ ጋር የተያያዙ ናቸው በማለት እና የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 59(1) ን በመጥቀስ ስለመሆኑ ከውሳኔው መገንዘብ ይቻላል። ሆኖም ደመወዝ ማለት ምን እንደሆነ እና የትኞቹ ክፍያዎች እንደ ደመወዝ የሚቆጠሩ ስለመሆኑ በዚሁ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 53(1) ስር ደመወዝ ማለት አንድ ሰራተኛ በስራ ውለ መሰረት ለሚያከናውነው ስራ የሚከፈለው መደበኛ ክፍያ ማለት ስለመሆኑ ተደንግጓል። የትርፍ ሰአት ክፍያ፣አበል፣ከአሰሪ የሚከፈል ጉርሻ(ቦነስ)፣ኮሚሽን፣ላልች የማትጊያ ክፍያዎች እና ከደንበኞች የሚሰበሰብ የአገልግልት ክፍያዎች እንደ ደመወዝ የማይታዩ ስለመሆናቸው በዚሁ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 53(2) ስር ተደንግጓል።
ከዚህ ድንጋጌ አጠቃላይ ንባብ መገንዘብ የሚቻለው ደመወዝ የሚባለው በግራ ቀኙ መካከል ባለው የስራ ውል መሰረት ለተከናወነ ስራ የሚከፈል መደበኛ ክፍያ እንጂ ከዚህ ውጪ ያለውን በተለይም አሁን እያከራከረ ያለውን በስራ ስንብት ምክንያት የሚፈጸሙትን ክፍያዎች የማያጠቃልለ ስለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል። በዚሁ መሰረት የበታች ፍርድ ቤቶች ለተጠሪ በስራ መሰናበቱ ምክንያት የሚፈጸሙለት ክፍያዎች እንደ ደመወዝ ይታያለ በማለት የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 59(1)ን በመጥቀስ የሰጠው ውሳኔ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም። ለዚህ ጉዲይ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ.377/96 ምዕራፍ ሶስት ዘርፍ ሁለት ከአንቀጽ 36 እስከ 38 ድረስ ያለውና የስራ ውል ሲቋረጥ ደመወዝ እና ተያያዥነት ያላቸው ክፍያዎች የሚፈጸምበትን አግባብ የሚደነግገው ክፍል ነው።
አንድ የስራ ውል ሲቋረጥ የሰራተኛው ደመወዝ እና ተያያዥ ክፍያዎች ሁለ በሰባት ቀናት ውስጥ መከፈል ያለባቸው ስለመሆኑ፣ሆኖም የክፍያው ጊዜ ሉራዘም የሚችለው ከአሰሪዉ የተረከበዉን ንብረት የማስረከብ ወይም የሚፈለግበትን ማናቸዉንም ሂሳብ በማወራረድ በራሱ ጥፊት በሆነ ምክንያት ካዘገየዉ ስለመሆኑ በዚሁ አዋጅ በአንቀጽ 36(1) ስር ተደንግጓል።
በተጨማሪም በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 37 ስር በክፍያ መጠኑ ላይ አለመግባባት ሲኖር አከራካሪ ያልሆነዉ ክፍያ ሉፈጸም የሚገባ ስለመሆኑ ተመልክቷል። በዚህ ጉዲይ ላይ ግራቀኙ በተጠሪ ላይ አመልካቾች ያልተወራረደ ሑሳብ አለ በማለት በሚከራከሩበት እና ተጠሪ በበኩለ ምንም ዓይነት ዕዲ የላለበት እና ራሳቸዉ የፈጠሩት ነዉ በማለት በሚከራከርበት ወቅት የእነዚህ ሁለቱ ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ የሚያስገነዝቡት አመልካቾች የተጠሪን ክፍያ ገንዘቡ በእጃቸዉ ስላለ ብቻ ቆርጠዉ ማስቀረት ሳይሆን በፍርድ ቤት አለ የሚለትን ዕዲ በትክክል ያለበት ስለመሆኑ ማስወሰን የሚገባቸዉ ስለመሆኑ ነዉ። አመልካቾች ይሄንን ባልፈጸሙበት ሁኔታ እና ግራቀኙ ያልተማመኑበትን ዕዲ ለተጠሪ ሉፈጸምለት ከሚገባዉ ክፍያ ላይ ቀንሶ ማስቀረቱ ከላይ የተመለከቱትን የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ድንጋጌዎች ያላገናዘበና ተቀባይነት ያለዉ አካሄድ አይደለም ብለናል።
ባጠቃላይ ተጠሪ ከስራ በመሰናበቱ ምክንያት ከሚከፈለት ክፍያዎች ላይ በግራ ቀኙ መካከል አከራካሪ የሆነዉን ሑሳብ መሰረት በማድረግ ቀንሶ ክፍያ መፈጸም አግባብነት የላለዉ ነዉ ብለናል። የበታች ፍርድ ቤቶችም በሰጡት ዉሳኔ በስንብት ወቅት የሚፈጸሙት ክፍያዎች እንደደመወዝ ይቆጠራለ በማለት የሰጡት ምክንያት ተቀባይነት ባይኖረዉም የደረሱበት መደምደሚያ ተቀባይነት ያለዉ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 342 መሰረት ከዉጤት አኳያ ተቀብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተዉን ዉሳኔ ሰጥተናል።
የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝ ቁ.103360መጋቢት 26 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለዉ ችልት እና የፋ/የመጀ/ደ/ፍርድ ቤት በመዝ.ቁ. 70595 በቀን 17-6-2003ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጡት ዉሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.348(1) መሰረት ጸንቷል።
በተጠሪ እና አመልካቾች መካከል አከራካሪ የሆነን ዕዲ በትክክል ዕዲዉ ስለመኖሩ በፍርድ ቤት ሳይወሰንበት በስንብት ወቅት ከስንብቱ ጋር በተያያዘ ለተጠሪ ከሚፈጸሙለት ክፍያዎች ላይ ተቀንሶ የሚከፈልበት አግባብ የለም ብለናል።
በዚህ ችልት በቀን 13-8-2003 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የተሰጠዉ የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰዉ ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.