No summary available.
ጥር 14 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ አምባዬ ወ/ማሪያም- የቀረበ የለም።
ተጠሪዎች፡- የኢትዮጵያ የእህል ንግድ ድርጅት - ነገረፈጅ በየነ ቢቂላ ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ አመልካች የስራ መሪ ሆኖ ሲሰራ በነበረበት ከተጠሪ ድርጅት ጋር ባለው የስራ ውልን መሰረት ያደረገ ክርክር ሲሆን ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የአማራ ብሓ/ክል/መንግስት የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ተጠሪ አመልካችን ከስራ ያሰናበተው ያለበቂ ምክንያት በህገ-ወጥ መንገድ በመሆኑ የስራ ውለ ተቋርጦ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ያልተከፈለው ውዝፍ ደመወዝ ተከፍልት ወደ ስራው ይመለስ በማለት ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በበኩለ ስንብቱ ህገ-ወጥ መሆኑን በማመልከት ክፍያን በተመለከተ ግን ተፈጻሚነት ያለው የፍታሐብሓር ህጉ መሆኑን በመግለጽ የሶስት ወራት ደመወዝ በካሳ መልክ እና የሁለት ወራት ደመወዝ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ብቻ ተፈጽሞለት እንዱሰናበት በማለት በመወሰኑ እና የፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ይሄንኑ ውሳኔ በማጽናቱ የተፈጸመው መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች በማመልከቱ የቀረበ ነው።
አመልካች ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞባቸዋል ያለዋቸውን ነጥቦች ያነሱ ሲሆን ነሐሴ 24 ቀን 2002 ዓ.ም. በሶስት ገጽ በተጻፈ የቀረበ የቅሬታ ፍሬ-ሃሳብ፡የአመልካች የስራ ውል በተጠሪ አነሳሽነት በህገ-ወጥ መንገድ የተቋረጠ ስለመሆኑ በሁለም የበታች ፍርድ ቤቶች በሚገባ የተረጋገጠ በመሆኑ፣ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት እና የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ላይ ያለውን የድርጅቱን የስራ መሪዎች መተዲደሪያ ደንብ በግልጽ በሚቃረን መልኩ ውሳኔ የሰጡ በመሆኑ የተሰጡት ፍርድች ተሽረው የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ፀንቶልኝ በመተዲደሪያ ደንቡ አንቀጽ 59(2) መሰረት ውዝፍ ደመወዝ ተከፍልኝ ወደ ስራ እንድመለስ እንዱወሰንልኝ፣ ይህ አይቻልም የሚባልበት ህጋዊ ምክንያት ቢኖር ግን በስር ፍርድ ቤቶች በማስረጃነት ተያይዞ በቀረበውና በተጠሪ ድርጅት ውስጥ በስራ ላይ ባለው የስራ መሪዎች መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 54(1)(ሀ)፣ 53(3)(ሀ)ና(ለ)፣ እንዱሁም 60(2) መሰረት የስልሳ ቀን ደመወዝ በካሳ መልክ፣ የ12 ወራት ደመወዝ የስራ ስንብት ክፍያ እና የአንድ ወር ደመወዝ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ እንዱከፈለኝ እንዱወሰንልኝ የሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ታዞ ታህሳስ 25 ቀን 2003 ዓ.ም በሁለት ገጽ በተጻፈ መልስ የሰጠ ሲሆን ፍሬ-ሃሳቡ፡- አመልካች ክስ ሲያቀርቡ የሶስት ወራት ውዝፍ ደመወዝ ተከፍል ወደ ስራዬ ልመለስ የሚል እንጂ የስራ ስንብት ክፍያ አላቀረቡም፣ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያላነሱትን ክርክር በማንሳት የተለያዩ ክፍያዎች እንዱፈጸሙለት ሉጠይቅ አይገባውም፣ በተጠሪ እና አመልካች መካከል ያለው ክርክር መታየት ያለበት በፍታሐብሓር ህግ እንጂ በስራ መሪዎች መተዲደሪያ ደንብ መሰረት መሆን የለበትም፣ የበላይ እና ገዥ የሆነው ህግ የፍታሐብሓር ህጉ የስራ መሪ ከስራ ሲሰናበት የሚከፈለው ክፍያ የሶስት ወራት ደመወዝ ብቻ ስለመሆኑ እየደነገገ እና ከዚህ በፉት የሰበር ሰሚው ችልትም የሶስት ወራት ደመወዝ ብቻ የሚገባው ስለመሆኑ አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሰጠበት በመሆኑ የመተዲደሪያ ደንቡ ተፈጻሚነት ሉኖረው አይገባም የሚል ነው።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ ከተያዘው ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሯቸዋል። እንደመረመረውም ጉዲዩ ለዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ሲባል ተይዞ የነበረው ጭብጥ በአመልካች ላይ የተወሰደው የስራ ስንብት እርምጃ ህገ ወጥ ነው ተብል ውጤቱን በተመለከተ ግን ተፈጻሚነት የሚኖረው የፍታሐብሓር ህጉ ነው በማለት የስራ መሪዎች መተዲደሪያ ደንብ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተፈጻሚ ያለመደረጉን አግባብነት ለመመርመር ሲባል በመሆኑ የተያዘው ጉዲይ ከዚሁ ጭብጥ አኳያ እልባት ማግኘት ያለበት ሁኖ ተገኝቷል።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ በተጠሪ ድርጅት ውስጥ በሚሰሩት የስራ መሪዎች ላይ ተፈጻሚነት ያለው መተዲደሪያ ደንብ ስለመኖሩ እና አመልካችም የስራ መሪ ስለመሆኑ ግራ ቀኙን ያከራከረ ነጥብ አይደለም። በግራ ቀኙ መካከል ስራ ላይ ያለው ልዩ ህግ እስካለ ድረስ እና ያለው ደንብ ደግሞ ለሞራል እና ለህግ ተቃራኒ ነው ወይም ተፈጻሚነት ሉኖረው የማይገባበትን ህጋዊ ምክንያት እስካልቀረበ ድረስ ተፈጻሚነት የሚኖረው ይሄው ልዩ ህግ በመሆኑ ወደ አጠቃላይ የፍታሐብሓር ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት ያላቸውን የህግ ማዕቀፍ ፍለጋ የሚኬድበት አግባብ የለም። በልላ በኩል ተጠሪ በግራ ቀኙ መካከል ስራ ላይ ያለው መተዲደሪያ ደንብ ተፈጻሚነት ሉኖረው የማይገባ ስለመሆኑ ያቀረበው ህጋዊ ምክንያት በላለበት፣ ወደ ፍታብሓር ህግ አጠቃላይ ድንጋጌዎች ደግሞ የሚኬደው ለዚህ ጉዲይ የተለየ ህግ በላለበት ሁኔታ በመሆኑ፣ ከዚህ በፉት ይሄ የሰበር ሰሚ ችልት አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል በማለት የተነሳውም ቢሆን ለዚህ ጉዲይ አግባብነት ያለው ባለመሆኑ እና ለደንቡ ተፈጻሚ አለመሆን የቀረበ ህጋዊ ምክንያት ባለመኖሩ በተጠሪ በኩል በደንቡ ተፈጻሚነት ዙሪያ የተነሳው ክርክር ተቀባይነት የላለው ነው ብለናል።
አመልካች ወደ ስራ ለመመለስ ያቀረበውን ቅሬታ በተመለከተ በመተዲደሪያ ደንቡ አንቀጽ 59(2) መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ከስራ የተሰናበተው የስራ መሪ ወደ ስራ ለመመለስ መብት እንዲለው በግልጽ የሚያስቀምጥ ቢሆንም ፍርድ ቤቶች በስራው መልካም አካሄድ ላይ የስራ መሪው ወደ ስራው መመለስ ችግር ያስከትላል በማለት ሲያምንበት ለዚሁ ለህገ-ወጥ ስንብት ተገቢነት ያላቸው ክፍያዎች ተፈጽመውለት እንዱሰናበት መወሰንን የሚከለክል አይደለም። በዚሁ መሰረት የአመልካች ወደ ምድብ ስራው የመመለስ ጥያቄን በተመለከተ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ውድቅ አድርገው ማለፊቸውን በውጤት ደረጃ ይሄም ችልት ተቀብልታል። በመቀጠል የአመልካችን የዲኝነት ጥያቄ በተመለከተ ተጠሪ እንደሚከራከረው ክስ ሲያቀርብ የሶስት ወራት ደመወዝ ተከፍልት ወደ ስራው እንዱመለስ እንጂ የስራ ስንብት ክፍያ አልጠየቀም በሚል ነው።
አመልካች ክስ ሲያቀርብ ከስራ ተሰናብቶ በሶስተኛ ወሩ መሆኑ የተቋረጠው ውዝፍ ደመወዝ ተከፍልት ወደ ስራው እንዱመለስ ቢሆንም ከላይ እንደተመለከተው ፍርድ ቤቱ የአመልካች ወደ ስራው መመለስ ለስራው መልካም አካሄድ ችግር ሉኖረው ይችላል ብል ሲያምን ከዚሁ ከህገወጥ ስንብት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ክፍያዎች ተፈጽመውለት እንዱሰናበት መወሰንን የሚከለክልና ህጉም የመጀመሪያው አማራጭ (ወደ ስራ የመመለስ የዲኝነት ጥያቄ) ተቀባይነት ካጣ ወደ ሁለተኛውና ተያያዥ ክፍያዎች መፈጸም በሚቻል መልኩ የተደነገገ በመሆኑ ተያያዥ ክፍያዎች እንዱፈጸምለት ውሳኔ መስጠት ያልተጠየቀ ዲኝነት ነው የሚባልበት አግባብ የለም።
ተያያዥ ክፍያዎችን በተመለከተ በደርጅቱ ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ በዋለው የስራ መሪዎች መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 54(1)(ሀ)፣ 53(3)(ሀ)(ለ)፣ እና 60(2) መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ከስራ የተሰናበተ የስራ መሪ የካሳ፣ የስራ ስንብት እና የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ሉከፈል የሚገባ ስለመሆኑ የሚደነግግ በመሆኑ በዚሁ ድንጋጌዎች ስር የተመለከቱት ክፍያዎች ለአመልካች ሉፈጸሙለት ይገባል ብለናል። በዚሁ መሰረት የክፍያ መጠኑን ስንመለከት አመልካች በተጠሪ ድርጅት ውስጥ ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰራ የነበረ ስለመሆኑ እና የደመወዝ መጠኑ ደግሞ ብር 1,200 (አንድ ሺህ ሁለት መቶ) ስለመሆኑ ያከራከረ ነጥብ ባለመሆኑ በዚሁ መሰረት ስላቱን ሰርተናል። ከላይ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት ክፍያውን ስናሰላ በደንቡ አንቀጽ 54(1)(ሀ) መሰረት የሁለት(2) ወራት ደመወዝ በካሳ መልክ 1200 x 2= 2,400 ብር (ሁለት ሺህ አራት መቶ ብር)፣ በደንቡ አንቀጽ 53(3)(ሀ)(ለ) መሰረት የስራ ስንብት ክፍያ የ26 ዓመት አገልግልት መሰረት በማድረግ ስናሰላ 1,200 + 1/3 X 1,200(26-1)= 11,200 ብር (አስራ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር) እና በደንቡ አንቀጽ 60(2) መሰረት ለማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ የአንድ ወር ደመወዝ ብር 1,200 (አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር) ይሆናል ማለት ነው። በዚሁ መሰረት ባጠቃላይ ተጠሪ ለአመልካች ብር 14,800 ( አስራ አራት ሺህ ስምንት መቶ ብር) ሉከፍለው ይገባል ብለናል።
ባጠቃላይ የበታች ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች በግራ ቀኙ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ተፈጻሚነት ያለው ህግ በተመለከተ በድርጅቱ ውስጥ በስራ ላይ ያለው የስራ መሪዎች ደንብ ሆኖ እያለ ያለ በቂ ህጋዊ ምክንያት ማለፈ አግባብነት የላለው እና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት የውሳኔ ክፍል በመሆኑ ሉታረም ይገባል ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ. 51756 ሰኔ 21 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የአማራ ብሓ/ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝ.ቁ. 14504 ጥቅምት 12 ቀን 2001 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
በግራ ቀኙ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት መታየት ያለበት በተጠሪ ድርጅት በስራ ላይ ባለው የስራ መሪዎች መተዲደሪያ ደንብ መሰረት ነው ብለናል።
ተጠሪ በህገ-ወጥ መንገድ አመልካችን ከስራ ያሰናበተው በመሆኑ የካሳ፣ የስራ ስንብት እና የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ባጠቃላይ 14,800 ብር (አስራ አራት ሺህ ስምንት መቶ ብር) ለአመልካች እንዱከፍል ብለናል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.