No summary available.
የሰ/መ/ ታህሣሥ 2 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሪት ሰላም ተስፊዬ ጠበቃ ዲንኤል ግርማ ቀረቡ ተጠሪ፡- አልካን ሃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሙለጌታ ሀመነ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪ የሥራ ውል ከህግ ውጭ ያቋረጠ በመሆኑ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ መሰረት መብቴ እንዱጠበቅልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ አመልካች የተቀጠሩት በዱኘልማ ደረጃ ላለ ተማሪዎች የእንግሉዝኛ ቋንቋ ለማስተማር ነበር። በዱኘልማ ኮርስ እንግሉዝኛ ቋንቋ እንዲይሰጥ ከመንግሥት ትዕዛዝ የተሰጠ በመሆኑ ከሥራ የተሰናበቱ ስለሆነ ስንብቱ ህጋዊ ነው በአዋጁ መሰረት የካሣና ላልች ክፍያዎች ልንጠየቅ አይገባም በማለት ተከራክሯል። የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከአመልካች ጋር ያለውን የሥራ ውል ያቋረጠው በህግ በተደነገገው መሰረት ነው በማለት ከወሰነ በኋላ ተጠሪ ለአመልካች የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያና የሥራ ስንብት ክፍያ ይክፈል በማለት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ ላይ ተጠሪ ይግባኝ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ አመልካችን ያሰናበተው በህጉ በተደነገገው መሰረት ስለሆነ የማስጠንቀቂያ ክፍያና የሥራ ስንብት ክፍያ ክፈል መባለ ተገቢ አይደለም በማለት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል።
አመልካች በመንግስት ትዕዛዝ የእንግሉዝኛ ቋንቋ ለዱኘልማ ተማሪዎች እንዲይሰጥ መከልከለና በዚህ ምክንያት ተጠሪ የሥራ ውለን ማቋረጡ ተጠሪን የማስጠንቀቂያ ክፍያና የሥራ ስንብት ክፍያ ከመክፈል ነፃ አያደርገውም በማለት የሰበር አቤቱታ አቅርባለች። ተጠሪ በበኩለ እኔ የሥራ መደቡን አልሰረዝኩም። የሥራ መደቡ ለዱኘልማ ትምህርት እንደማያስፈልግ ትዕዛዝ የተሰጠው በመንግስት ነው። ስለዚህ በመንግስት ትዕዛዝ የሥራ መደቡ አላስፈላጊ የሆነ በመሆኑ የማስጠንቀቂያና የሥራ ስንብት ክፍያ የምከፍልበት ምክንያት የለም በማለት መልስ ሰጥቷል።
አመልካች የመልስ መልስ አቅርባለች።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪ ለአመልካች የሥራ ስንብት ክፍያና የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ የመክፈል ሀላፉነት የለበትም በማለት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካች በተጠሪ ድርጅት የተቀጠሩት ድርጅቱ በዱኘልማ ትምህርት ለሚያስተምራቸው ተማሪዎች የእንግሉዝኛ ቋንቋ ለማስተማር እንደነበር በፍሬ ጉዲይ ደረጃ ተረጋግጧል። ተጠሪ በዱኘልማ ደረጃ ትምህርታቸውን ለሚከታተለ ተማሪዎች የእንግሉዝኛ ቋንቋ እያስተማሩ በነበሩበት ጊዜ መንግስት በዱኘልማ ደረጃ ለሚሰጥ ትምህርት የእንግሉዝኛ ቋንቋ መሰጠት የላለበት መሆኑን የሚገልፅ መመሪያ ማውጣቱ የሚያከራክር አይደለም።
አመልካች የተቀጠሩበት የሥራ መደብ በዱኘልማ ደረጃ ትምህርት ለሚሰጡ ተቋማት እንደማያስፈልግና አመልካች ያስተምሩት የነበረው ትምህርት ላሰጥ እንደማይችል መንግስት መመሪያ ያወጣበት ጉዲይ ነው። ተጠሪ አመልካችን ያሰናበታቸው ከዚህ በኋላ በተቋሙ የሚሰሩት ሥራ የለም በማለት ነው። ተጠሪ አመልካችን ያሰናበታቸው በራሱ አነሳሽነት አይደለም። ተጠሪ አመልካችን ያሰናበታቸው በህግ ሥልጣን በተሰጠው የመንግስት አካል በተላለፈው መመሪያ መሰረት አመልካች የሚያስተምሩት የእንግሉዝኛ ቋንቋ በዱኘልማ ደረጃ መሰጠት የላለበት መሆኑን የሚያረጋግጥ አስገዲጅ ትዕዛዝ ስለደረሰው ነው። ስለሆነም ተጠሪ ከአቅሙ በላይ በሆነ ሁኔታ ሥልጣን ባለው አካል በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት በመሆኑ በጉዲዩ የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 28 ድንጋጌዎችን በመጥቀስ የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለአመልካች የሥራ ስንብት ክፍያና የማስጠንቀቂያ ክፍያ እንዱከፍል የሰጠው ውሣኔ ተገቢነት የላለው በመሆኑ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንን ውሣኔ መሻሩ በአግባቡ ሆኖ አግኝተነዋል። ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 12 ንዐስ አንቀፅ 1/ሀ/ መሰረት ለአመልካች ተሰጥቷት የነበረው ሥራ ሥልጣን ያለው የመንግስት አካል ባወጣው መመሪያ መሰረት አመልካች እየሰራች ለመቀጠል የማትችል መሆኑ ተረጋግጧል። ተጠሪ ለአመልካች የሚሰጠው ሥራ በላለበት ሁኔታ የሥራ ውለ እንዱቀጥል የማድረግ ህጋዊ ግዳታ የለበትም። የሥራ ውለ በመንግስት በወጣ መመሪያ ተፈፃሚነት ምክንያት የተቋረጠ በመሆኑ አመልካች ማስጠንቀቂያም ሆነ የሥራ ስንብት ክፍያ የሚከፍልበት ምክንያት የለም። ስለሆነም የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ክርክር ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.