No summary available.
ሕዲር 04 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ጨረር መካላከያ ባለስልጣን - ነ/ፈጅ ኃይለ ታደሰ ቀረበ ተጠሪ፡- አቶ ታሪኩ ጫኔ - ጠበቃ ካሣኝ ይበልጣል ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በስራ ምክንያት የወጣ ንብረት ባለመመለሱ የተነሳ የንብረቱ ጉድለት በገንዘብ ይተካልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡-ተጠሪ ለስራ የተረከቡትን ግምቱ ብር 23,423.39 (ሃያ ሶስት ሺህ አራት መቶ ሃያ ሶስት ብር ከሰላሳ ዘጠኝ ሳንቲም) የሆነ የጨረር መጠን መለኪያ(Universal survey meter- model RDS-200) እና ግምቱ ብር 53,443.85 (ሃምሳ ሶስት ሺህ አራት መቶ አርባ ሶስት ብር ከሰማኒያ አምስት ሳንቲም) የሆነ የራጅ ጥራት መለኪያ (Digital quality control sit- 1 set) መጠበቅ ሲገባቸው በቸልተኝነትና በጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት ለተገዛበት ጉዲይ ሳይውል ያጠፊ መሆኑን ገልፆ የመሳሪያዎቹን ጠቅላላ ድምር ብር 76,867.34 (ሰባ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ስልሳ ሰባት ብር ከሰላሳ አራት ሳንቲም) እንዱከፍለ፣ የንብረቶቹ ዋጋ ከገበያ ውስጥ ከጨመረ ይኸው ታክልበት ገንዘቡን እንዱከፍለ ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስም በአመልካች መስሪያ ቤት ተቀጥረው በሚሰሩበት ጊዜ ንብረቶቹን ለስራ መረከባቸውን ሳይክደ ንብረቶቹን ለስራ ይዘው ከሄደበት ቦታ ላይ በመኪና ውስጥ በጥንቃቄ አስቀምጠው እያለ በስራ ቦታ ላይ በሥርቆት ምክንያት የጠፈባቸው መሆኑን ገልፀው ከአቅም በላይ ለተከሰተው የንብረት መጥፊት በአዋጅ ቁጥር 515/1999 አንቀጽ 65 እና አግባብነት ባለው የመንግስት ንብረት አስተዲደር ሕግ መሰረት ሃላፉነት የለብኝም ሲለ ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በሁዋላ ለክርክሩ መሰረት የሆኑት ንብረቶች ተጠሪ በስራ ላይ እያለ በጥንቃቄ ካስቀመጡበት ቦታ በስርቆት የጠፈ መሆኑ መረጋገጡን በምክንያትነት በመያዝና የአዋጅ ቁጥር 515/1999 አንቀጽ 65 ድንጋጌን በዋቢነት በመጥቀስ ተጠሪ ለክሱ ኃላፉ ሉሆኑ አይችለም ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪ ለስራ የተረከቡትን ንብረት ያላስረከቡ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ ለንብረቱ መጥፊት ኃላፉነት የለባቸውም ተብል መወሰኑ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ተጠሪ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ለደረሰ የንብረት መጥፊት ኃላፉ አይሆኑም የመባለን አግባብነት ለመመርመር ተብል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን ሕጎች መሰረት ያደረገ በመሆኑ ሉጸና ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። አመልካች በበኩለ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም ምላሽ የሚያስፈልገው የጉዲዩ ጭብጥ ተጠሪ ከአመልካች የተረከቧቸውን እቃዎች የዋጋ ግምታቸውን ለመክፈል ይገደዲለ? ወይስ ይገደደም? የሚለው ሆኖ ተገኝቷል። ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን እቃዎች ከአመልካች ላይ የተረከቡ መሆኑን ሳይክደ ኃላፉነት የለብኝም በማለት የሚከራከሩት ለመስሪያ ቤቱ ስራ በሄደበት ቦታ በስራው ቦታ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሁኖ ፣ በመስሪያ ቤቱ መኪና ውስጥ አስቀምጠው እና መኪናውን በመቆለፍ የአበል ክፍያ ለመቀበል ወደ መ/ቤቱ ሂሳብ ክፍል በሄደበት ጊዜ እቃዎቹ ሉሰረቁ ወይም ሉጠፈ ችለዋል በማለት ነው። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ በክስ የተጠየቀውን ገንዘብ ሉከፍለ አይገባም ወደሚል ድምዲሜ መድረስ የቻለው የተረከቧቸው እቃዎች በስርቆት ምክንያት የጠፈ መሆኑ ተረጋገጧል ፣ ይህም ከተጠሪ አቅም በላይ በሆነ ምክንያት ንብረቶቹ የጠፈ መሆኑን ስለሚያሳይና በተጠሪ በኩል ቸልተኝነት የነበረ መሆኑ አልተረጋገጠም በማለት ፍሬ ነገርን አጣርቶና የግራ ቀኙን ማስረጃዎችን መዝኖ እንዱሁም የአዋጅ ቁጥር 515/1999 አንቀፅ 65 ድንጋጌን በዋቢነት በመጥቀስ ነው። በተጠሪ በኩል ቸልተኝነት ያልነበረ፣ እቃዎቹ በስርቆት ምክንያት የጠፈ ስለመሆኑ የስር ፍርድ ቤት በማስረጃ ያረጋገጠው ፍሬ ነገር ጉዲዩን በይግባኝ በተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተቀባይነት አግኝቷል።
አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው ደግሞ ተጠሪ ኃላፉነት አለባቸው በማለት ነው። ይሁንና ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ከአመልካች ጋር በፈጠረው የሥራ ውል መነሻነት ለክሱ መነሻ የሆኑትን እቃዎችን ስለመረከቡ በአመልካች ማስረጃ የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ በተጠሪም ያልተካደም ቢሆንም ተጠሪ እነዚህን ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን እቃዎች ከአመልካች ከተረከቡ በኋላ በአሰሪው መስሪያ ቤት ወደ ታዘዙበት የስራ ቦታ ይዘው ሄደው በተገቢው ቦታና ጥንቃቄ መሰረት አስቀምጠው በነበሩበት ሁኔታ ንብረቶቹ መሰረቃቸው ወይም መጥፊታቸው በፍሬ ነገር ደረጃ በሚገባ የተረጋገጠ ስለመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በግልጽ ያሳያል። ይህንኑ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር ደረጃ የደረሱበትን ድምዲሜ ይህ ችልት እንዲለ ከመቀበል ውጪ የማስረጃ ምዘናን መሰረት በማድረግ ሉመረምረው የማይገባው መሆኑን ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። በልላ አገላለጽ ይህ ችልት በሕጉ ተለይቶ የተሰጠው ስልጣን በማናቸውም የመጨረሻ ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መፈጸሙ ሲረጋገጥ ማረም ነው። በመሆኑም ንብረቶቹ የጠፈት በስርቆት መሆኑና ስርቆቱ ደግሞ የተፈፀመው ተጠሪ ተገቢውን ጥንቃቄ አድርገው በነበሩበት ጊዜ ስለመሆኑ በፍሬ ነገር መረጋገጡን ይዘን በሕጉ አተረጓጎም ረገድ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር ያለመኖሩን እንመለከታለን። ተጠሪ አከራካሪ እቃዎቹን ለአመልካች መስሪያ ቤት እስከሚያስረክቡ ጊዜ ድረስ በንብረቶቹ ላይ ለሚደርስ ማናቸውም ጉዲት ፣ ብልሽት ወይንም መጥፊት በኃላፉነት ተጠያቂ ሉሆኑ ስለሚችለ ይህ ችግር እንዲይከሰት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ይታመናል። አንድ ሰራተኛ ከአሰሪው መስሪያ ቤት ለስራ እቃዎቹን ሲረከብ የሚፈርመበት ዋናው ምክንያትም ይህንኑ ግዳታውን ካልተወጣ ኃላፉነት ሉከተልበት ስለሚገባው እንደሆነ ይታመናል። በልላ በኩልም ተጠሪ ፈርሞ የተከረባቸውን እነዚህን እቃዎች እንዲይጠፈ፣ እንዲይሰረቁም ሆነ ላላ ጉዲት እንዲይደርስባቸው ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ የሚጠበቅበት በሥራ ሰዓት ሲሆን ንብረቶቹ በሥራ ሰዓት ከራሱ ጥንቃቄ ጉድለት ውጪ በሆነ ምክንያት ወይም ከሥራ ሰዓት ውጭና በራሱ እጅ ባልነበሩበት ጊዜ የጠፈ ስለመሆኑ የማስረዲቱ ሸክም አለባቸው። ይህንኑ ግዳታውን የተወጡ ስለመሆኑ ደግሞ ከላይ እንደተገለጸው የበታች ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር ደረጃ ማስረጃን መዝነው አረጋግጠዋል።
አመልካች ከላይ በተመለከተው ሁኔታ ተጠሪ ያረጋገጡትን ፍሬ ነገር ያለመስተባበለም በበታች ፍርድ ቤቶች ድምዲሜ ላይ ተደርሷል። ተጠሪ ይህንን የማስረዲት ሸክማቸውን ከተወጡ ወይም እቃዎቹ በስራ ላይ ቆይተው በጥንቃቄ ከተቀመጡበት ቦታ በስርቆት መጥፊታቸውን በማስረጃ ከአረጋገጡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 2027 ድንጋጌ መሰረት በቸልተኝነት ጥፊት መፈጸማቸውን የማያረጋግጥ ነው። ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት ባለው በአዋጅ ቁጥር 515/1999 አንቀጽ 65 ስር ደግሞ አንድ የመንግስት ሰራተኛ ፈርሞ ላወጣው ንብረት መጥፊት በእዲ ተጠያቂ ላሆን የሚችለው ፈርሞ ላወጣው ንብረት መጥፊት የሰራተኛው ቸልተኝነት የታየ ወይም በሰራተኛው በኩል ሆነ ተብል የተፈፀመ ድርጊት ያለ እንደሆነ ስለመሆኑ ተደንግጓል። በልላ በኩል አመልካች በሰ/መ/ በኪራይ ቤቶች ኤጄንሲና በአቶ ካሳ ግዛው መካከል በነበረው ክርክር ህዲር 24 ቀን 2000 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ ለዚህ ጉዲይም አግባብነት ያለው መሆኑን ጠቅሶ የተከራከረ ሲሆን ይህ ችልት ይህንኑ መዝገብ ሲመለከተው በመዝገቡ የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮችና ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ሕግ አሁን ከታያዘው መዝገብ ጉዲይ ጋር ሙለ በሙለ ተመሳሳይ ነው ለማለት የማይቻል ሁኖ አግኝቶታል። ስለሆነም የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ተጠሪ ንብረቶቹ በሥራ ሰዓት በጥንቃቄ አስቀምጠው ባለበት ሁኔታ በስርቆት የጠፈ ስለመሆኑ በማረጋገጥና የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር ከላይ ከተጠቀሰው አዋጅ ጋር በማዛመድ ተመልክቶ ተጠሪ ጥፊት መፈጸማቸውን አመልካች አላረጋገጠም በማለት ክሱን ሳይቀበል መቅረቱ እንዱሁም ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንኑ መቀበለ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት አልተቻለም።
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሳስ 04 ቀን 2003 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሚያዚያ 20 ቀን 2003 ዓ.ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዚኅ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.