No summary available.
የሰ/መ/ ህዲር 6 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኦሮሚያ መንገድች ቦለሥልጣን - አልቀረቡም ተጠሪ፡- ወ/ሮ ብርቄሣ አብራሂም - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የሰበታ ሐዋሳ ወረዲ ፍርድ ቤት የፉንፉኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አመልካች የገቢ ግብር ሣይቀንስ ለተጠሪ የሥራ ስንብትና ላልች ክፍያዎችን እንድንከፍል የሰጡት ውሣኔ መሰታዊ የሕግ ስህተትና ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። የወረዲው ፍርድ ቤት ተጠሪ ከአመልካች ጋር በነበራት የሥራ ክርክር እንዱከፈላት የተወሰነላት የስራ ስንብት የካሣና ላልች ክፍያዎች ግብር ተቀናሽ ሣያደረግ በደመወዟ በጥቅለ አስቦ እንዱከፍል ትእዛዝ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች የተጠሪን የአገልግልት ካሣና ግብር ሣይቀንስ በሙለ ደመወዝ (gross income) ታስቦ ይከፈላት በማለት ወስኗል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አቅርቦ አቤቱታው ተቀባይነት አላገኘም።
አመልካች ተጠሪ የሥራ ስንብት ክፍያና የአገልግልት ካሣ ክፍያ ግብር ሣይቀነስ በሙለ ደመወዟ አስበን እንድንከፍል የተሰጠው ውሣኔ በአዋጅ ቁጥር 286/94 እና ደንብ ቁጥር 78/1994 የሚጥስ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት አመልክቷል። ተጠሪ የአመልካች ክርክር የህግ መሰረት የለውም የሚል መስከረም 29 ቀን 2004 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርባለች።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ለተጠሪ የገቢ ግብር ሣይቀናነስ በሙለ ደመወዙ በማስላት የስራ ስንብት ክፍያና የአገልግልት ካሣ ክፍያ እንዱከፈል የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ውሣኔ ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን በአዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 10 ገቢ ማለት ማናቸውም የኢኮኖሚ ጥቅም ሲሆን በመደበኛነት የተገኘ ባይሆንም ከማናቸውም ምንጭ በጥሬ ገንዘብ ወይም በአይነት በማናቸውም መልክ ለግብር ከፍዩ የተከፈለው በስሙ የተያዘለትን ወይም የተቀበለውን ሁለ ጥቅም ይጨምራል በማለት ሰፉ ትርጉም ተሰጥቶታል።
ከላይ በተገለፀው አዋጅ አንቀጽ 10 ማናቸውም ሰው በመቀጠር ከሚያገኘው ገቢ ግብር የመክፈል ሃላፉነት እንዲለበት ማናቸውም ቀጣሪ በሚከፍለው እያንዲንደ ክፍያ ግብሩን የመቀነስና ለመንግስት ገቢ የማድረግ ግዳታ እንዲለበት የተደነገገውን መመልከት አስፈላጊ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በአዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 13 ከግብር ነፃ የሚሆኑ ክፍያዎች የተዘረዘሩ ሲሆን በደንብ ቁጥር 78/1994 አንቀጽ 3 ግብር የማይከፈልባቸው ገቢዎች በዝርዝር ተደንግገዋል ስለሆነም የስራ ስንብት ክፍያንና ካሣ ክፍያ በአዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 13 እና በደንብ ቁጥር 78/1994 ግብር የማይከፈልባቸው ስለመሆኑ በግልጽ አልተደነገገም። ስለሆነም አመልካች በአዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 10 ንዐስ አንቀጽ 2 በተጣለበት ሃላፉነት መሰረት ለተጠሪ ከሚከፈለው ክፍያ የገቢ ግብር በመቀነስ ለመንግስት ገቢ ለማድረግ ያቀረበውን ክርክር ውድቅ በማድረግ ለተጠሪ በሙለ ደመወዝ አስልቶ የሥራ ስንበት የካሣ ክፍያ እንዱከፍል የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የሰበታ ሐዋሳ ወረዲ ፍርድ ቤት፤ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሻሽሎል።
አመልካች የገቢ ግብር በመቀነሰ ለተጠሪ በፍርድ የተወሰነለትን የሥራ ስንብት ክፍያና የካሣ ክፍያ ይክፈላት በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
የማይነብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.