No summary available.
ጥቅምት 20 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ቴላኮሙኒኬሽን ኮፔሬሽን ደቡብ ሪጅን - ነገረ ፈጅ አየነው ዱለላቻ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ጥበቡ ተሰማ - ጠበቃ ወርቀአገኘሁ ኃይላ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ክርክር ሲሆን የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ በፍርድ ባለመብትነት ባቀረበው የአፈፃፀም አቤቱታ በማቅረቡ በደቡብ ብሓ/ብሓ/ህዝቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት በአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተጀመረ ነው። ቀረቦ የነበረው የአፈፃፀም አቤቱታ በተመደብኩበት የሥራ መድብና ደሞዝ ቀድሞ በተሰጠው ፍርድ መሰረት እንዱፈፀምልኝ የሚል ነው። አመልካች ለቀረበው የአፈፃፀም አቤቱታ መልስ ሲሰጥ ቀድሞ የነበረው መዋቅር በመንግሥት መመሪያ የተሰረዘ በመሆኑ እንደውሣኔው መፈፀም ያልቻለ መሆኑና አዱስ በወጣው መዋቅር መሰረት ደግሞ የሚመደብበትን ቦታ እንዱጠባበቅ በማለት ተከራክሯል።
የአፈፃፀም መዝገቡን የያዘው ፍርድ ቤት በአፈፃፀሙ ዙሪያ በዚሁ መልኩ ካከራከረ በኋላ የፍርድ ባለመብት (የአሁኑ ተጠሪ) ፍርድ ያገኘው የቀድሞ መዋቅር ሥራ ላይ በነበረበት ወቅትና አዱሱ መዋቅር ባልነበረበት ወቅት በመሆኑ በፍርደ መሰረት ሉፈፀም ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ የቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 337 መሰረት የከፍተኛውን ፍ/ቤት ውሣኔ በማጽናት ውሣኔ ሰጥቷል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምተናል። ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች ከታያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመረው ለአሁኑ ተጠሪ ተሰጥቶት የነበረው ፍርድ ሉፈፅም የሚችል ፍርድ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ ተይዞ ይሄ ጉዲይ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁ መሰረት አመልካች አጥብቆ እየተከራከረ ያለው ለተጠሪ በፍርድ ቤት የተሰጠ ፍርድ መኖሩን ሳይክድ ቀድሞ የነበረው የድርጅት መዋቅር አደረጃጀቱን ለማሻሻል በተወሰደ እርምጃ በሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁ. 197/2003 መሰረት የፈረሰ በመሆኑ እንደፍርደ ለመፈፀም ያልተቻለ መሆኑን ነው። በልላ በኩል የተጠሪ ክርክር ቀድሞ የነበረው የድርጅቱ መዋቅር የፈረሰ ስለመሆኑ ሳያስተባብል ውሣኔውን ከመፈፀም የሚከለክል ባለመሆኑ እንደፍርደ ሉፈፀምልኝ ይገባል የሚል ነው።
በግራ ቀኙ መካከል በነበረው የክርክር ሂደት አመልካች ድርጅትን በተመለከተ መንግሥት ባወጣው ደንብ መሰረት ቀድሞ የነበረው መዋቅር የፈረሰ መሆኑ አላከራከረም። በተጨማሪም የመዋቅር ለውጡ ከመምጣቱ በፉት ተጠሪ በፍርድ ቤት ውሣኔ የፍርድ ባለመብት ስለመሆኑ እና ይሄው የተሰጠው የፍርድ ቤት ውሣኔ ሣይፈፀም የድርጅቱ አደረጃጀት በመንግስት መለወጡ በተመሳሳይ መልኩ ግራ ቀኙን ያከራከረ ጉዲይ አይደለም። ይሄ ከሆነ ደግሞ የቀድሞውን የድርጅቱን አደረጃጀት መሰረት በማድረግ በፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ ከመፈፀሙ በፉት መንግሥት በሚያወጠው ደንብ መሰረት አደረጃጀቱ ቢለውጥ ፍርደ ሉፈፀም የሚችልበት አግባብ ስለመኖሩ ወይም አለመኖሩ መመልከት ተገቢ ነው።
በክርክሩ ሂደት የታወቁትን ፍሬ ነገሮች ይዘን ወደ ህጉ ስንመለስ ቀድሞ በሥራ ላይ የነበረው የአመልካች ድርጅት አደረጃጀትና በፍርድ ቤት ለተሰጠው ፍርድና ተጠሪን የፍርድ ባለመብት ያደረገው ውሣኔ መሰረት ያደረገው መዋቅር በአሁኑ ጊዜ በሥራ ላይ የላለ መሆኑ ግልጽ ነው።
በሥራ ላይ በላለ መዋቅር መሰረት የተሰጠው ፍርድ ለተጠሪ ይፈፀም ማለት ደግሞ የማይቻል ነው። በመሰረቱ በመርህ ደረጃ የተሰጡት የፍርድ ቤት ውሣኔዎች ተፈፃሚነት የሚያገኙ ሲሆን አልፍ አልፍ ሉፈፀም የማይቻል ፍርድ ሉኖር እንደሚቻል ከፍታሐብሓር ሥነ ሥርዓት ህጋችን መገንዘብ ይቻላል። እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 392(1) መሰረት አፈፃፀሙን የያዘው ፍርድ ቤት ሉፈፀም የሚቻል ውሣኔ ስለመሆኑ ወይም ስላለመሆኑ ማረጋገጥ እንዲለበት ያመለክታል። የማይፈፀምበት አግባብ ካለ ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.
392(2) መሰረት ይሄንኑ በማመልከት ሉፈፀም የማይቻል ስለመሆኑ ትዕዛዝ መስጠት እንደሚቻል ያመለክታል።
በዚህ ጉዲይ ላይም በላለ አደረጃጀት ላይ ውሣኔ ማስፈፀም የማይቻል መሆኑ ግልጽ ሆኖ እያለ የበታች ፍ/ቤቶች በፍርድ መሰረት ይፈፀም በማለት ትዕዛዝ መስጠታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
53298 በቀን 26-9-2003 ዓ.ም እና የሀዋሣ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝ. በቀን 22-9-2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በህግ አግባብ ቀሪ በሆነ አደረጃጀትን መሰረት በማድረግ ፍርድ እንዱፈፀም የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ትዕዛዝ አግባብነት የለውም ብለናል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰ ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.