No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 8 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ቴላኮሙኒሽን ኮ/ን ተጠሪዎች፡-
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ በአሰሪና ሰራተኞች መካከል የተነሣውን የሥራ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በአዋሣ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መደበኛ ችልት ሲጀመር ከሣሾች የነበሩት ተጠሪዎች ናቸው። በአመልካች ላይ ክስ የመሰረቱት የሥራ ውላችንን ከሕግ ውጪ አቋርጦብናል በማለት ነው። በዚህ መሰረትም ወደ ሥራቸው እንዱመልሳቸው፤ ይህ ካልተቻለ ደግሞ ልዩ ልዩ ክፍያዎችን ይከፈላቸው ዘንድ እንዱወሰንላቸው ጠይቀዋል። አመልካች በበኩለ ለክሱ በሰጠው መልስ ተጠሪዎች የተቀጠሩት ለተወሰነ ጊዜ የተወሰነ ሥራ ለመሥራት ነው። የተሰናበቱትም በውለ መሰረት ነው በማለት ተከራክሮአል። ፍ/ቤቱም የሁለቱን ወገኖች ክርክር ከመረመረ በኋላ፣ የሥራ ውለ የተቋረጠው በውለ እና በሕጉ መሰረት ነው እሚል መደምደሚያ ላይ ደርሶአል። በዚህ መሰረትም በሕጉ መሰረት መከፈል አለበት ያለውን ክፍያ ብቻ ተከፍልአቸው ይሰናበቱ በማለት ወስኖአል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪዎች ውሣኔውን በመቃወም ለአዋሣ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት መደበኛ ጉዲይ ችልት ይግባኝ በማቅረባቸው ክርክሩ በድጋሚ የተሰማ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የተጠሪዎችን ክርክር በመቀበል ይግባኝ የተባለበትን ውሣኔ ሽሮአል። ተጠሪዎች ወደ ሥራቸው ይመለሱ በማለትም ወስኖአል። በመጨረሻም አመልካች ለደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት አቤቱታ አቅርቦ የነበረ ሲሆን፣ የሰበር ችልቱ አቤቱታ በቀረበበት ውሣኔ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም በማለት አቤቱታውን ሰርዞአል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች ሚያዝያ 6 ቀን 2003 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል የሚልበትን ምክንያት በመግለጽ አቤቱታውን አቅርቦአል። እኛም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልቱ እንዱታይ የተደረገው በአመልካች እና በተጠሪዎች መካከል ተደርጎ የነበረው የሥራ ውል የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው የመባለን አግባብነት ሉመረመር ይገባል በመባለ ነው።
በመሆኑም በዚህ ረገድ አመልካች እና ተጠሪዎች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከሥር ጀምሮ የተደረገው ክርክር እና የተሰጡት ውሣኔዎች ይዘት እንዲየነው በአመልካች እና በተጠሪዎች መካከል የተደረገው የሥራ ውል በሚሰራው ሥራ ዓይነት እና በጊዜ የተወሰነ ነው።
ተጠሪዎች የተቀጠሩት ሳይሰበሰብ የቆየውን የስልክ አገልግልት ክፍያ ለመሰብሰብ ይቻል ዘንድ በፍ/ቤት እየቀረቡ ለመከራከር ወይም የነገረ ፈጅነት አገልግልት ለመስጠት ነው። ውለ ይህ ለመሆኑ በፍሬ ነገር ረገድ አለማከራከሩ የሥር ፍ/ቤቶች በሰጡአቸው ውሣኔዎች ተመልክቷል።
በእርግጥ አመልካች ውለን ለአንድ ጊዜ አራዝሞት እንደነበር በክርክሩ ተገልጾአል። ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ የሰማው ፍ/ቤት የተጠሪዎችን ክስ ውድቅ ያደረገው /ውለ በሕጉ አግባብ ነው የተቋረጠው ያለው/ የውለን ይዘት እና የሥራው ማለቅ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው።
ይግባኙን የሰማው ፍ/ቤትም ቢሆን በውለ ይዘት ላይ የተለየ ግንዛቤ እንዲለው አልገለጸም።
ተጠሪዎች የተቀጠሩበት ሥራ አላለቀም እሚል መደምደሚያ ላይ አልደረሰም። ውለ ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ ነው ለማለት የበቃው አመልካችን እንደተቋም በመውሰድ ብቻ ነው። ተጠሪዎች የተቀጠሩበት መለስተኛ የሕግ ባለሙያ የሚል ነው። ይህ የሥራ መደብ ደግሞ ተቋሙ እስካለ ድረስ ያለ ነው የሚል ምክንያት ነው የሰጠው።
በእርግጥ አመልካች እንደተቋም አሁንም አለ፣ መኖሩም ይቀጥላል። ለክርክሩ አወሳሰን መያዝ ያለበት ጭብጥ ተጠሪዎች የተቀጠሩት በአሰሪና በሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 10 መሰረት ነው ወይስ አይደለም የሚል ነው። ይህ ጭብጥ መፈታት ያለበትም የአመልካችን ድርጅታዊ አቋም መሰረት በማድረግ ሳይሆን፣ በሥራው አይነትም የተወሰነ ነው። በውለ መሰረት ተጠሪዎች የተቀጠሩበት ሥራ የሚያልቅ አይደለም ወይም አላለቀም አልተባለም።
በመሆኑም አመልካች ተጠሪዎችን በሰራተኛነት ይዞ የሚቀጥልበት የሕግ ምክንያት የለም።
ውለ ለተወሰነ ሥራ የተደረገ በመሆኑ አመልካች ተጠሪዎችን ያሰናበተው በአንቀጽ 10/1 እና 24/1/ መሰረት ነው። ይግባኙን የሰማው ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ከዚህ አንፃር ሲታይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል። ስለዚህም ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
52288 ሚያዝያ 4 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
በአመልካች እና በተጠሪዎች መካከል ተደርጎ የነበረው የሥራ ውል የተቋረጠው በሕግ አግባብ ነው ብለናል።
ግራ ቀኙ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።