No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዝያ ዐ9 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሪት ሃና አበባው ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አብደ ይመር በላለበት የሚታይ ነው **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ለብድር የተሰጠው ገንዘብ ከብር አምስት መቶ በላይ ሲሆን ለማስረዲት የሚያቀርበውን የማስረጃ አይነት የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በደሴ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የተጠሪ ክስ ይዘትም ለአመልካች ብር 1ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ/አስር ሺህ ብር/ አበድረው አመልካች በብድር ውለ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ገንዘቡን ያልመለሱላቸው መሆኑን ገልፀው የብድር ገንዘቡን ሉመለስ ይገባ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ከመቶ ወለድ ጋር እንዱከፍለ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። ለማስረጃነትም የብድር ውለ በወቅቱ የጠፊ በመሆኑ ለፕሉስ ያመለከቱ መሆኑን የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃና የሰው ምስክሮችን ዘርዝረው አቅርበዋል። አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስም ከተጠሪ የወሰደት የብድር ገንዘብ የላለ መሆኑን፣ ከብር 5ዐዐ.ዐዐ በላይ ለሆነ የብድር ስምምነት ማስረጃነትም የሰው ምስክር ላቀርብ የማይችል መሆኑን ገልፀው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የወረዲው ፍርድ ቤትም ተጠሪ የብድር ሰነደ የጠፊባቸው ስለመሆኑ በሰው ማስረጃ ማረጋገጥ እንደሚችለ ገልፆ ተጠሪ ምስክሮችን አቅርበው ምስክሮቹ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የካቲት ዐ7 ቀን 2ዐዐ2 ዓ/ም የብድር ውል ስምምነት መኖሩን፣ ሰነደ የጠፊበት መሆኑን እንደሚያውቁ ያረጋገጡላቸው መሆኑን እንዱሁም በአመልካች በኩል የተሰሙት ምስክሮች ግን የብድር ውለ ስለመኖሩ አናውቅም ከማለት ውጪ የተጠሪን ማስረጃ ለማስተባብል የሚችል የምስክርነት ቃል ያልሰጡ መሆኑን ገልፆ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የብድር ውል ስምምነት መኖሩ ተረጋግጧል ወደሚለው ድምዲሜ ደርሶ አመልካች ለተጠሪ ብር 1ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ ከእነ ሕጋዊ ወለደ ሉከፍለ ይገባል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቀጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። ከዚህም በኋላ አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን መርምሮ ተጠሪ ባለበት የሚጣራ የሕግ ነጥብ አለ በማለት ነጥቡን ለይቶ ለተጠሪ ጥሪ አድርጎላቸው የግራ ቀኙን ክርክር ለመስማት ለመስከረም 22 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም ቀነ ቀጠሮ ይዞ ተጠሪ ሲቀርቡ አመልካች አልቀረቡም፣ የቀረቡት ተጠሪም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ክደው ተከራክረዋል በማለት የጉዲዩ ክርክር ሉሰማ በተያዘው ቀነ ቀጠሮ አመልካች ስላልቀረቡና ተጠሪም ክደው ስለተከራከሩ መዝገቡ ሉዘጋ የሚገባው ነው በማለትና በዋቢነትም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 ድንጋጌን በመስማት መዝገቡን ዘግቶታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ትዕዛዝ በመቃወም ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ የቀረበበትን መዝገብ የዘጋው አመልካች ቀርበው እያለና ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ መሆኑን፣ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔም ስለብድር ማስረጃ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2472 ስር የተደነገገውን ደንጋጌ ይዘት ያላገናዘበና የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2003 ድንጋጌን ያለቦታው በመጠቀም የተሰጠ መሆኑን ገልፀው ውሣኔው ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልት ላታይ የሚገባው ነጥብ በመኖር ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪም ጥሪ ተደርጎላቸው በስርዓቱ መሰረት ጥሪ ተደረጎላቸው ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ለዚህ ሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ትዕዛዝና አግባብነት ከአላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ ሁኖ የተገኘው የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩ የቀረበበትን መዝገብ የዘጋበት ሥነ-ሥርዓት ሕጉን የተከተለ መሆን ያለመሆኑን ነው።
አመልካች ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በሰበር ችልት ላታይ የሚገባው የሕግ ነጥብ መኖሩ ታምኖበት የአሁኑ ተጠሪ በተጠሪነት የተመዘገቡበት በመሆኑ ክርክሩን ተጠሪ ባለበት ለመስማት ተብል ቀነ ቀጠሮ ተይዞ መስከረም 22 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም በተያዘው ቀነ ቀጠሮ ተጠሪ ሲቀርቡ አመልካች ያለመቅረባቸው ስለመረጋገጡና ተጠሪም ክደው መከራከራቸውን የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት መስከረም 22 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም. በዋለው ችልት ከመዝገቡ ከአሰፈረው መረዲት የሚቻል ሲሆን ይህንኑ ምክንያት በማድረግም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩ ሉሰማ በተቀጠረበት ቀነ ቀጠሮ አመልካች ስላልቀረቡና ተጠሪም ጉዲዩን ክደው ስለተከራከሩ መዝገቡን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 ድንጋጌን በመጥቀስ ሶስት ዳኞች በተሰየሙበት ችልት ዘግቶታል። ከዚህ በቀላለ መረዲት የሚቻለው የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን ለመስማት በያዘው ቀነ ቀጠሮ ተጠሪ ቀርበው አመልካች ያለመቅረባቸውን ፣ ችልቱ ላይ የተሰየሙት ዳኞች ቁጥር ሶስት ከመሆናቸውም በተጨማሪ መዘገቡን ሲዘጋውም በሶስት ዳኞች ብቻ መሆኑና መዝገቡ ሲዘጋ የተጠቀሰው የሥነ ሥርዓት ድንጋጌም መልስ ሰጪን ሳይጠራ ይግባኙን ለመሰረዝ ስለሚቻልበት ሁኔታ የሚደነግገው ቁጥር 337 መሆኑን ነው።
No topics extracted.
በመሰረቱ ማንኛውም የፍርድ ቤት ክርክር በሕጉ አግባብ በተደነገገው የሥነ ሥርአት ሕግ መሰረት መመራት አለበት። በየትኛውም እርከን የሚገኝ ችልትም በሕጉ ተለይቶ የተቀመጠለት ሥርዓት እስከላለ ድረስ ተፈፃሚነት ባለው የስነ ስርዓት ሕግ መሰረት ከተዘረጋው ሥርዓት አንፃር ጉዲዮችን መምራት አለበት። ጉዲዮች በሥነ ሥርዓት ሕጉ መሰረት የሚመሩትም አይነተኛ አላማም ክርክሮችን ፍትሃዊ በሆነ እና ሥርዓት ባለው መንገድ በመምራት በአጭር ጊዜ እና በአነስተኛ ወጭ እንዱቋጩ ማድረግ ስለመሆኑም ይታመናል። ይህንኑ የሥነ ሥርዓት ሕጉን አላማ ለማሳካት ደግሞ በሕጉ የተመለከቱትን የስነ ሥርዓት ድንጋጌዎችን እንደየአግባብነታቸው መከተልን የግድ ይላል። በስነ ሥርዓት ሕጉ የተመለከቱት ድንጋጌዎችን እንደየአግባብነታቸው ያለመከተል በተከራካሪ ወገኖች መሰረታዊ መብት ላይ አለታዊ ውጤት ማስከተለ አይቀሬ ነው። ስለሆነም በስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት ሉኖራቸው የሚገባው ለጉዲዩ አግባብነት ሲኖራቸው እንጂ በዘፈቀደ ላሆን አይገባም።
ድንጋጌዎቹ አግባብነት ያላቸው ስለመሆኑ ከመለየቱ በተጨማሪ በጉዲዩ ላይ ተገቢነት አለው የሚለውን ትዕዛዝ ወይም ውሣኔ የሚሰጠው ችልትም በሕጉ አግባብ የተመለከተው የዳኞች ቁጥር የተሟላ ላሆን ይገባል። በሕጉ አግባብ ሉሟላ የሚገባው የዳኞች ቁጥር ሳይሟላ የሚሰጠው ትእዛዝ ወይም ውሣኔ ደግሞ እንደተሰጠ የማይቆጠርና ሕጋዊ ውጤት ሉኖረው የሚገባ አይደለም።
ወደተያዘው ጉዲዩ ስንመለስ በክልለ የሰበር ችልት በክልለ አዋጅ ቁጥር 153/2000 እና ይህንኑ አዋጅ በአሻሻለው አዋጅ ቁጥር 169/2002 ተደራጅቷል። በእነዚህ አዋጆች መሰረት የአመልካች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ቀደም ብለው ሶስት ዳኞች ተሰይመውበት አምስት ዳኞች በሚሰየሙበት ችልት ላታይ ይገባል ተብል ትእዛዝ ተሰጥቶበት አመልካችንና ተጠሪን ለመስማት ቀነ ቀጠሮ መያዙ ተረጋግጦ እያለ ጉዲዩ አምስት ዳኞች በተሰየሙበት ችልት አይደለም። ጉዲዩ አምስት ዳኞች በተሰየሙበት ችልት እንዱቀርብ ከተደረገ በሁዋላ የቃል ክርክርን ለመስማት ሶስቱ ዳኞች በእለቱ ተሰይመው ላሆን እንደሚችል የሚገመት ቢሆንም መዘገቡን ለመዝጋት ግን በዚህ የዳኞች ቁጥር የሚቻል ስለመሆኑ የክልለን ሰበር ሰሚ ችልት ያደራጀው የክልለ ሕግም ሆነ ላልች አግባብነት ያላቸው የሥነ ሥርዓት ሕጎች አያሳዩም።
ስለሆነም የአመልካች የሰበር አቤቱታ የተዘጋው በሕጉ አግባብ የተመለከተውን የዳኞችን ቁጥር ባሟላ ችልት በአለመሆኑ ትዕዛዙ እንደተሰጠ የማይቆጠርና ሕጋዊ ውጤት ሉኖረው የሚገባው አይደለም።
ላላው የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን ሲዘጋ መሰረት ያደረገው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 ድንጋጌን ነው። እኛም ጉዲዩን እንደተመለከትነው የሥር ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ አቅራቢን ክርክር ለመስማት ቀጠሮ ይዞ እንደነበርና የመስማቱ ዓላማም የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል አልተፈፀመበትም የሚለውን ለይቶ በተሟላ ችልት የሚታይ መሆኑንና አለመሆን ለማዘዝ ስለመሆኑን ከመዝገቡ ግልባጭ ተረድተናል። የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የቀረበለትን ጉዲይ አይቶ ለመወሰን ክርክሩን የሚመራበት የእራሱ የሆነ የጉዲይ አካሄድ ሥርዓት የለውም።
የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሚመራው መደበኛ ችልቶች በሚመሩበት በ1958 ዓ.ም በወጣው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ መሰረት ነው።
ይህንን መነሻ አድርገን ጉዲዩን ስናየው መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል የሚለውን የፅሐፍ ቅሬታ በማብራራት ረገድ የሰበር አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ እንዱያሰማ ችልቱ ቀጠሮ ከያዘ ይህን ሥርዓት ለመፈፀም የሚያዘው ቀጠሮ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ለመፈፀም የሰበር አቤቱታ አቅራቢ የግድ እንዱቀርብ የሚጠበቅበት አይደለም። አመልካቹ ጉዲዩን የበለጠ ለማብራት የሚጠቀምበት መብት ቀሪ ከሚሆንበት በስተቀር ችልቱ የቀረበለትን አቤቱታ መርምሮ ተጠሪን ያስቀርባል ወይም አያስቀርም የሚል ትዕዛዝ ከመስጠት የማያግደው ሲሆን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 73 ድንጋጌም ተፈፃሚነት ሉኖረው የሚችለው የክርክር ደረጃ አይሆንም። ጉዲዩ የሕግ ስህተት አለበት ተብል ወደ አምስቱ የሰበር ችልት ከቀረበ እና ክርክሩን ለመስማት ቀነ ቀጠሮ ከተያዘ ደግሞ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 ድንጋጌ ተፈፃሚነት የሚኖርበት ሥርዓት የለም። በመሆኑም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ እንዱያሰሙ በችልቱ ቀጠሮ ከተያዘ በኋላ ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 ድንጋጌን በመጥቀስ መዝገቡን መዝጋቱም ሕጋዊ አካሄደን የተከተለ አይደለም። በአጠቃላይ አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ እንዱያሰሙ ችልቱ ቀጠሮ ከያዘ ይህን ሥርዓት ለመፈፀም የሚያዘው ቀጠሮ ሉሟላ የሚገባው የዳኞች ቁጥር አምስት ሁኖ እያለ መዝገቡን በሶስት ዳኞች መዝጋቱና መዝገቡን ለመዝጋት የተጠቀሰው የስነ ስርአት ሕጉ ድንጋጌም አምስት ዳኞች በተሰየሙት ችልት ባለው የክርክር ደረጃ ተፈፃሚነት የላለው በመሆኑ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በጉዲዩ ላይ የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ መስከረም 22 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም በመዝገብ መዝጋት ረገድ የሰጠው ትእዛዝ ተሽሯል።
አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ቀድሞ ያስቀርባል በተባለው መሰረት ተጠሪ ባለበት ግራ ቀኙ በተሟላ ችልት እንዱሰሙ እንዱደረግና ተገቢ ስርዓት መሰረት ተደርጎም ክርክሩ ተካሂድ ተገቢው ዲኝነት እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 341 መሰረት ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አምስቱ ዳኞች ወደሚሰየሙበት ችልት መልሰናል።