No summary available.
ጥቅምት 21 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አመልካች፡
መዝገቡን ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል ጋር ተያያዥነት ያለው ክርክር ሲሆን የተጀመረው በፋ/የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ባቀረበው ክስ ነው። ቀርቦ የነበረውም ክስ በግራ ቀኙ መካከል የነበረው ጋብቻ በሸሪዓ ፍርድ ቤት ውሳኔ በፍቺ የፈረሰ መሆኑን በማመልከት በጋራ ያፈራናቸዉን ንብረት ተጠሪ ታካፍለኝ በማለት ተንቀሳቃሽ ንብረቶቹን ከተራ ቁጥር 1-13 ከነ ግምታቸው የዘረዘሩ ሲሆን ስፊቱ 4ዐዐ ካ.ሜ የሆነ ቦታና ቤት ታካፍለኝ የሚል ነው። ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፋ/የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት ተከሣሽን በተመለከተ መልስ እንዱሰጡበት ተጠርተው ስላልቀረቡ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፍአል በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል።
በመቀጠል በተሰጠው ውሳኔ በድሬዲዋ ከተማ ቀበላ 02 ክልል የሚገኘው ቤት እንዱሁም አንድ ቴላቪዥን ባለ 14 ኢንች እና አንድ ቴኘ የአመልካችና የተጠሪ የጋራ ሀብት ናቸው በማለት ከተቻለ በዓይነት እኩል ይካፈለ፣ካልተቻለ በስምምነት ተገምቶ አንደ ለላላው ግምቱን ከፍል ያስቀር፣በዚህ ካልተስማሙ በራሣቸው ወይም በጨረታ ተሸጠው ገንዘቡን እኩል እንዱካፈለ ፍርድ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝዋን ለፋ/የከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበች ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት የፋ/የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትን ውሳኔ አፅንቷል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚሁ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምተናል። ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። በዚሁ መሰረት አመልካች አጥብቃ የምትከራከረው ከዚህ በፉት በሸሪዓ ፍ/ቤት የፍቺ ውሳኔም ሆነ የንብረት ክፍፍል ጉዲይ የተቋጨ ሆኖ እያለ ላላ ክስ መቅረቡ ያለአግባብ ነው፣ በሸሪዓ ፍ/ቤት በተሰጠው ውሳኔ የቤት ቁሣቁስ በተመለከተ በሰፈር ሽማግላ ይካፈለ ላላ ንብረት ካለ ደግሞ በመደበኛ ፍ/ቤት ይጠያየቁ በማለት የድሬዲዋ የመጀመሪያ ደረጃ የሸሪአ ፍ/ቤት ውሣኔ የሰጠ ሲሆን ይሄንን ውሣኔ በመቃወም ለከፍተኛ ሸሪዓ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ ከአንድ ሻንጣ ልብስ በስተቀር ላላ ንብረት የላለው መሆኑ ተረጋግጦ ውሣኔ የተሰጠበት ከመሆኑም በላይ ተጠሪም የተስማማበት ስለመሆኑ በሽማግላዎች ፉት የፈረመ በመሆኑ የቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም የሚል ነው። ተጠሪ በበኩለ ባቀረበው ክርክር አመልካች በቀረበባት ክስ መጥሪያ ደርሷት ቀርባ ያልተከራከረች በመሆኑ፣የጋራ ንብረት ደግሞ ለመካፈል ህጉ መብት የሚሰጠኝ በመሆኑ እና የሸሪዓ ፍ/ቤት ደግሞ በመደበኛ ፍ/ቤት የመጠየቅ መብት የሰጠኝ በመሆኑ የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት የለውም የሚል ነው።
በዚህ የክርክር ሂደት በእርግጥም ተጠሪ እንደሚከራከረው የሸሪዓ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን በአካባቢ ሽማግላዎች እንዱከፊፈለ እና ላልች ንብረቶችን በመደበኛ ፍ/ቤት የመክሰስ መብቱ እንደጠበቀ ግራ ቀኙን አላከራከረም። አመልካች የምትከራከረው በሸሪዓ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ ይግባኝ በመውሰድ በከፍተኛው የሸሪዓ ፍ/ቤት ተሽሯል። በዚሁ በከፍተኛ ሸሪዓ ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረት ተጠሪ ከአንድ ሻንጣ ልብስ በስተቀር የሚደርሰው ንብረት የላለ መሆኑ ውሣኔ ተሰጥቶበታል በሚል ነው። ይሄንን አመልካች በግልፅ ያነሣቸውን የክርክር ነጥብ ተጠሪ ያላስተባበለና የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ ላይ ብቻ በመንጠልጠል መልስ የሰጠ በመሆኑ በግልፅ እና በዝርዝር ያልተስተባበለ ነጥብ ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 234/መ/ እና 235 መሰረት እንደታመነ የሚቆጠር በመሆኑ ቀድሞ በሸሪዓ ፍ/ቤት ፍርድ ያረፈበትን የንብረት ክፍፍል ጉዲይ በተመለከተ እንደ አዱስ ለመደበኛ ፍ/ቤት ማቅረብ አግባብነት አለው? ወይስ የለውም የሚለውን መመልከት ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል።
የሸሪዓ ፍ/ቤቶች በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 78/5/ እና 188/92 መሰረት በማድረግ የተቋቋሙና እውቅና የተሰጣቸው መሆኑን ስለሚያመለክት፣በዚሁ ህገ-መንግስት አንቀጽ 34/5/ መሰረት በተከራካሪዎች ፍቃድ መሰረት የግል ወይም የቤተሰብ ሕግን በተመለከተ በሃይማኖት ህጎች የመዲኘት መብት የተጠበቀ በመሆኑና በዚሁ ሂደትም የተሰጡት ፍርድች ተቀባይነት ያላቸው ስለመሆኑ ከነዚህ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ህገ-መንግስት ድንጋጌዎች ይዘት፣ዓላማና መንፈስ መገንዘብ ይቻላል።
No topics extracted.
በዚሁ መሰረት በህግ ስልጣን በተሰጠው የሸሪዓ ፍ/ቤት ግራ ቀኙ ተከራክረውበት በፍርድ ያለቀን ጉዲይ ተጠሪ በውሣኔው ቅሬታ እንኳ ቢኖረው በዚያው በሸሪዓ ፍ/ቤት መዋቅር መሰረት ቅሬታውን ለሚመለከተው የይግባኝ ወይም የቅሬታ ሰሚ ክፍል ማቅረብ ሲገባው እንደ አዱስ ጉዲይ በመደበኛ ፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 5/1/ መሰረት ተቀባይነት ያለው አይደለም። የበታች ፍርድ ቤቶችም የአሁን ተጠሪ ያቀረበው ክስ በላለበት የተሰማ ቢሆንም በሂደት ግን ጉዲዩ ቀድሞ በውሣኔ ያለቀ መሆኑን እንደተረደ የቀረበውን ክስ ወድቅ ማድረግ ሲገባቸው በቀረበው ክስ መሰረት ውሣኔ መስጠታቸው አግባብነት የላውና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ. 05327 ግንቦት 26 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የፋ/የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ. 27905 በቀን 26-12-2002 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ቀድሞ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት በፍርድ የተቋጨን ጉዲይ ሁለተኛ ክስ ወይም ማንኛውም ዓይነት ላላ ክርክር ለማቅረብ አይቻልም ብለናል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።