No summary available.
ሐምል 17 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡
ይህ የሰበር ጉዲይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 41 የተመለከተውን የጣልቃ ገብነት ሥርዓት አፈፃፀም የሚመለከት ነው።
የአሁን 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ ሆነው ግንቦት 19 ቀን 1996 ዓ.ም በተደረገ ውል ከአቶ ገረመው ጥላሁን እና ከወ/ሮ ልባዊት ዓለሙ ቁጥሩ 154 የሆነውንና በ800 ካ.ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውን ቤት ገዝቻለሁ ሆኖም የአሁን 2ኛ ተጠሪ በውል ላገኘሁት ቤት ካርታና ፔላን በስሜ ሰርቶ ሉሰጠኝ ሲጠየቅ እምቢተኛ ስለሆነ ካርታና ፔላን በስሜ ሰርቶ እንዱሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት በአሁን 2ኛ ተጠሪ ላይ ክስ አቅርባለች።
2ኛ ተጠሪም በቃል ክርክር ወቅት ቀርቦ ይህ ካርታና ፔላን ይሰራለት የተባለው ንብረት በቅደስ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን አካባቢ ስለሚገኝ እና ህዝብና መንግስት እንዲይጋጭ ብለን ላላ ተለዋጭ ቦታ ለመስጠት እየተዘጋጀን በመሆናችን እንጂ እምቢተኛ ሆነን አይደለንም የሚለውን አስመዝግቦ ጉዲዩ በክርክር ላይ እንዲለ የአሁን አመልካች በፍ/ብሥ/ሥ/ሕ/ቁ 41 መሰረት ጣልቃ ገብቼ እንድከራከር ይፈቀድልኝ፣ በማለት ጣልቃ ሉገባ የሚችልበትን አቤቱታ ከእነማስረጃው አቅርቧል።
በማስረጃነትም ክርክር ባስነሳው ንብረት ላይ የይገባኛል መብት ያለው መሆኑን የሚያመለክት የከተማ ቦታ ባለቤትነት ማስረጃ ወረቀት አያይዞ እንደቀረበ የስር የአደአ ወረዲ ፍ/ቤት በሰጠው ትዕዛዝ ላይ ተመልክቷል።
ሆኖም የአሁን አመልካች ጣልቃ ልገባ ይገባል በማለት ላቀረበው አቤቱታ በማስረጃነት ይህንኑ ሰነድ ያቀረበ ለመሆኑ በትዕዛዙ መግቢያ ላይ ፍ/ቤቱ መግለፁ እየታወቀ እንደገና ወረድ ብል ጣልቃ ልግባ ባዩ ጣልቃ እገባለሁ በማለት ለቤተክርስቲያን ህጋዊ ሰውነት ሰጭ የሆነውን የፍ/ብ/ሕ/ቁ 398 እና ለአስተዲደሩ የተሰጠውን ሥልጣን ከመጥቀሱ በቀር ያቀረበው ክርክርና ማስረጃ የለም የሚለውን ምክንያት በመያዝ፤ እንዱሁም ከሳሽ የአሁን 1ኛ ተጠሪ የሆነችው በውል ምክንያት ባገኘችው ካርታና ፔላን ላይ ጣልቃ ለመግባት የሚያስችል መብትም የለውም የሚለውን በመጥቀስና ጣልቃ ገብ ራሱን የቻለ ካርታና ፔላን አለው በአሁን 1ኛ ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት ከሳሽ በነበሩትና በአሁን 2ኛ ተጠሪ ተከሳሽ በነበሩት መካከል የተነሳው ክርክር በጣልቃ ገብ ካርታና ፔላን ላይ አይደለም። ከድሮ ጀምሮ ለላላ አካል በተሰጠ ካርታና ፔላን ላይ መብት ያለው አይደለም፤ ከፈለገም በልላ በኩል መብቱን ያስከብር እንጂ የሚለውን በማከል ጣልቃ ሉገባ አይገባም በሚል አሰናብቶታል።
የአሁን አመልካች ደረጃውን ጠብቆ እስከ ክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ጣልቃ ሉገባ እንደሚገባ በመግለፅ ይኸው ትዕዛዝ በይግባኝና በሰበር ሥርዓት እንዱታረምለት ዲኝነት ቢጠይቅም የወረዲው ፍ/ቤት ከሰጠው ዲኝነት ጋር ተመሳሳይ በሆነ ምክንያት ጥያቄው ተቀባይነትን አላገኘም። በዚህም የተነሳ የአሁን አመልካች ለዚህ የሰበር ጉዲይ መነሻ የሆነውን የሰበር አቤቱታ አቅርቧል።
1ኛ ተጠሪም የጣልቃ ልግባ ባዩን አቤቱታ የሥር ፍ/ቤቶች ውድቅ ማድረጋቸው በአግባቡ ዲኝነት መስጠታቸውን እንጂ የህግ ስህተት የፈፀሙ መሆኑን አያመለክትም የሚልበትን ምክንያት በመጥቀስ ሲከራከር፤ 2ኛ ተጠሪ በበኩለ በአንድ በኩል ክርክር ያስነሳውን ንብረት ከአሁን አመልካች በፉት 1ኛ ተጠሪ በግዥ ያገኙት ነው የሚል፤ በልላ በኩል የዚህ ንብረት ህጋዊ ባለይዞታ አመልካች ናት የሚል እንድመታ ያለው እርስ በእርሱ የተምታታ ሐሳብ ከሰጠ በኋላ በሁለት ግለሰቦች መካከል ባለ ክርክር 2ኛ ተጠሪ በሰበር ደረጃ ተጣርቶ ለመከራከር የሚያስችለው የህግ ምክንያት የላለ መሆኑን በመግለፅ መልስ ሰጥቷል።
እንግዱህ የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን፤ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል። እንደመረመርነውም ዲኝነት ሰጭ የሆነ አካል በሥራው የሚሰጠው ማናቸውም ዲኝነት በተከራካሪ ወገኖች በማስረጃ ተረጋግጦ የቀረበ ጉዲይ ከህግ ጋር በማገናዘብ ክርክርን፤
ማስረጃንና አግባብነት ያለውን ህግ መሰረት ያደረገ ላሆን ይገባል። ከዚህ አንፃር የአሁን አመልካች በሥር የአደአ ወረዲ ፍ/ቤት በነበረው ክርክር ጣልቃ ገብቼ ለመከራከር ያስችለኛል የሚለውን ምክንያት ለዚሁ ምክንያቱ ደጋፉ የሆነ የከተማ ቦታ ባለቤትነት ማስረጃ ማቅረቡ እየተገለፀ፤ የወረዲው ፍ/ቤት ጣልቃ ገብ ህጋዊ ሰውነት ያገኘበትን ህግና በአስተዲደሩ የተሰጠውን ሥልጣን ከመጥቀሱ በቀር ያቀረበው ክርክርና ማስረጃ የለም በሚል የተሰጠው ትንታኔ/ዲኝነት ከላይ ከዲኝነት ሰጭ አካል የሚጠበቀውን መሰረታዊ የስራ ግዳታ ምርኩዝ ያደረገ ሆኖ አላገኘነውም። በልላ በኩል በሥር ፍ/ቤት ከሳሽ የነበሩት የአሁን 1ኛ ተጠሪ በአደአ ወረዲ ፍ/ቤት በአሁን 2ኛ ተጠሪ ላይ ላቀረቡት የክስ አቤቱታ በማስረጃነት ያቀረቡት ቤቱን በግዥ አግኝቻለሁ ያለበትን ውል በማያያዝ መሆኑ ቢታወቅም ይህ ውል በህግ ፉት ሉፀና የሚችል ሆኖ ተገኝቷል ከተባለ የዚህ ውል የአስገዲጅነት ባህሪይ በተዋዋይ ወገኖች መካከል የተወሰነ ለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1731 የተመለከተ በመሆኑ የውለታው ጉዲይ በሆነው ንብረት ላይ መብት አለን የሚለትን ላልች ሦስተኛ ወገኖችን በንብረቱ ላይ ያላቸውን መብት ለማስከበር ሲለ ሉያቀርቡ የሚችለትን ክርክር ከጅምሩ ሉገደብ የሚችል አይደለም ይልቁንም ተዋዋዩ ወገን ሆነ ከነዚህ ሦስተኛ ወገኖች በየፉናቸው በሚያቀረቧቸው ክርክር እና ማስረጃ እየታየ የህግ መሰረት ያለው መሆኑንና አለመሆኑ እየተለየ ሉወሰን ከሚችል በቀር ከዚህም በቀር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 41 የተዘረጋው ሥርዓት በከሳሽና በተከሳሽ ተሰይመው በሚከራከሩበት ጉዲይ የመጨረሻ ውጤት የተነሣ በማጣት ሆነ በማግኘት ረገድ ጥቅሙ/መብቱ የሚነካበት፤ ማናቸውም ወገን ላላ ክስ ማቅረብ ሳያስፈልገው በጉዲዩ ገብቶ የክርክር ተካፊይ እንዱሆን በማድረግ ከአንድ ጉዲይ ሉመነጭ የሚችልን ክርክር በአንድ ፍ/ቤት በአንድ መዝገብ አጣምሮ በአጭር ጊዜ እና በአንስተኛ ወጭ እንዱቋጭ ለማድረግ እንዱረዲ ታስቦ የተደነገገ መሆኑ እየታወቀ የአሁን አመልካች ከፈለገ በልላ መንገድ መብቱን ያስከብር እንጂ በጉዲዩ ላይ ጣልቃ ሉገባ አይገባም በሚል የተሰጠው ትርጉም የህጉን ይዘት ግብና ዓላማ መሰረት ያደረገ ሆኖ አልተገኘም።
No topics extracted.
ከዚህም በቀር የአሁን አመልካች ያቀረበው ክርክር እና ማስረጃ በጉዲዩ ላይ ጣልቃ ገብቶ ለመከራከር የሚያስችለው አመልካች የሆነ ክርክርና ማስረጃ ማቅረቡ አስከተረጋገጠ ድረስ የክርክር ተካፊይ በማድረግ ጉዲዩን መምራት ሲቻል የአሁን አመልካች የክርክር ተካፊይ ሆኖ በዋናው ክርክርና ሙግት ጊዜ ክርክሩን ለማስረዲት ማቅረብ በሚገባው የክርክር ጥንካሬ እና የማስረጃ ሚዛን ዓይን በመለካት የተሟላ የክርክር አመራር ሥርዓት ሳይጠበቅ ለፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 41 በተሰጠው የተዛባ ትርጉም የተነሣ የአሁን አመልካች በጣልቃ ገብነት የክርክር ተካፊይ ላሆን አይገባም በሚል ከታች ወረዲ ፍ/ቤት ጀምሮ እስከ ክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚው ችልት የተሰጠው ትርጉም መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
የአደአ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ በ01/11/2002 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ፤ በማስከተልም በ22/11/2002 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ፤ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ09/3/2003 ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መ/ በ05/6/2004 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ሁለ ተሸሯል።
የአሁን 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ፤ 2ኛ ተጠሪ ተከሳሽ ሆኖ ክርክር በጀመሩበት በመ/ በ22/11/2002 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ የተሻረ በመሆኑ በዚሁ መዝገብ ላይ የአሁን አመልካችን በጣልቃ ገብነት በመሰየም ክርክሩን እንደ አዱስ ከጅምሩ በመምራት በጉዲዩ ላይ ተገቢው ዲኝነት ይሰጥበት ዘንድ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 341 መሰረት ጉዲዩን ለአደአ ወረዲ ፍ/ቤት መልሰናል።
የዚህ ሰበር ክርክር ላስከተለው ወጭና ኪሳራ ሁለም ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።