No summary available.
ሐምል 03 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ አልዩ ተክለ - አልቀረበም ተጠሪ፡- አቶ መስፍን ስለሺ - አልቀረበም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ ክስ ያቀረበ ወገን ክሱን ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት ማቅረብ ይችል ዘንድ መጥሪያውን ለተከሳሽ ለማድረስ በፉት ክሱ እንዱዘጋለት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ክሱ በተዘጋ ጊዜ ሙለ የዲኝነት አገልግልት አገኛለሁ በሚል በሰበር ከከፈለው የዲኝነት ገንዘብ ተገቢው ተቀንሶ እንዱመለስለት የመጠየቅ መብት አለው ወይስ የለውም? የሚለውን ተመልክቶ ተገቢውን ትርጉም ለመስጠት በሚል ነው።
ከላይ የተመለከተውን ጉዲይ አስመልክቶ በቅድሚያ ጉዲዩን የተመለከተውን የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሳሽ ክሱን በተከሳሽ አድራሻ ማቅረቡ ለአፈፃፀም የተሻለ ሆኖ ስላገኙት ወጭ አድርገው የወሰደትን መጥሪያ እና የእግድ ትዕዛዙን በመመለስ መዝገቡ እንዱዘጋላቸው እና የከፈለትም የዲኝነት ገንዘብ እንዱመለስላቸው ጠይቀዋል። በዚህም መሰረት ፍ/ቤቱ መዝገቡን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 278/1/ መሰረት መዝገቡን ዘግቶታል።
ይሁን እንጂ ከሳሽ ከከፈለው የዲኝነት ገንዘብ ተገቢው ተቀንሶ የሚመለስበትን አግባብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 232 እና 245 ከመደንገጉ በቀር ከሳሽ በእራሱ አነሳሽነት መዝገብ እንዱዘጋ ባደረገ ጊዜ ከከፈለው የዲኝነት ገንዘብ ሉመለስ የሚችልበትን ሁኔታ የደነገገ ሕግ አልተገኘም።
ስለሆነም ጥያቄው ተቀባይነት የለውም በማለት ዲኝነት ሰጥቷል።
ይህንኑ ትዕዛዝ በይግባኝ የተመለከተው ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በበኩለ ክስ የቀረበለት ፍ/ቤት የከሳሹን ክስ ሕጋዊ ብቃት መርምሯል። የእግድ ትዕዛዝም ሰጥቷል። ተከሳሽም ስለጉዲዩ መከላከል እንዱፈቀደለት የሚጠይቅ ከሆነ ፈቃድ እንዱጠይቅ መጥሪያ እና የክስ ማመልከቻ ግልባጭ ተልኮለታል። በዚህ ሁለ ምክንያት የፍ/ቤቱን የፅሕፈት መሣሪያ ከሳሽ የተጠቀመ ከመሆኑም በላይ ተገቢውን የዲኝነት አገልግልት አግኝቷል። ይህን አገልግልት ማግኘቱ ከተረጋገጠ የፍ/ቤት ዲኝነት አገልግልት ተሰጥቷል ማለት የሚቻለው ክሱ ከተሰማ በኋላ እንጂ ክሱ ከመሰማቱ በፉት ነው የሚለው ክርክር ከግንዛቤ እጥረት የመነጨ ነው የሚለውን ለጉዲዩ ምክንያት በመስጠት እና የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 177/45 ለጉዲዩ ተፈፃሚነት የላለው መሆኑን ሁለ ጠቅሶ ውሣኔውን አፅንቶታል።
አመልካች በዚህ ዲኝነት ላይ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን፤ ተጠሪ በጥሪው መሰረት ቀርቦ ለመከራከር ካለመፈቀደም በላይ በጉዲዩ ላይ ሉከራከር የሚችልበት ምክንያት ላይኖርም የሚችል መሆኑ ተጠቅሶ ክርክሩ ከአመልካች የሰበር አቤቱታ ጋር ተገናዝቦ እንዱታይ ተደርጓል። እኛም አመልካች ያቀረቡትን የሰበር መከራከሪያ ነጥብ ከላይ ከፍ ሲል ከተጠቀሰው የሥር ፍ/ቤቶች ዲኝነት ጋር በማገናዘብ ተመልክተናል።
እንደተመለከትነውም የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰጠው ትዕዛዝ እንደገለፀው ከሳሹ ክሴን ትቼዋለሁ በማለት ተከሳሹ ቀርቦ መልስ ከመስጠቱ በፉት ወይም የጉዲዩ መሰማት ከመጀመሩ በፉት በማመልከቱ የተነሣ መዝገብ በተዘጋ ጊዜ ፍ/ቤቱ ለሚሰጠው የዲኝነት አገልግልት ሲባል ከከፈለው የዲኝነት ገንዘብ ውስጥ የሚቀንሰው ተቀንሶ ቀሪው የሚመለስለት ስለመሆኑ ወይም ስላለመሆኑ በ1958 ዓ.ም በወጣው የፍ/ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ አልተደነገገም። በዚህ ሕግ ይህ ነጥብ በዝምታ ታልፎል። የሕግ ሽፊን አላገኘም።
ይሁን እንጂ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ የመሸጋገሪያ ድንጋጌ ክፍል በሆነው በአንቀጽ 3 ላይ የፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ሕጉ በግልፅ ለሸፈናቸው ጉዲዮች ሕጉ ከመውጣቱ በፉት ተፅፈው ሥራ ላይ የነበሩ ሕጏችና ደንቦች የተሻሩ መሆኑን ከመግለፅ በቀር ሕጉ ሳይሸፍናቸው ለታለፈ ጉዲዮች የፍ/ብሓር ሕጉ ከመውጣቱ በፉት ተፅፈው በሥራ ላይ የነበሩ አግባብነት ያላቸው ሕጎች እንደ አግባብነቱ ሥራ ላይ ሉውለ የሚችለ መሆኑን የሚያመለክት ነው።
በዚህም መሰረት በ1945 ዓ.ም በወጣው የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 177 አንቀጽ 11 ላይ ከሳሹ ክሱን ካቀረበ በኋላ በእራሱ ጠያቂነት ክሱን የተወው እንደሆነ አስቀድሞ ከከፈለው የዲኝነት ገንዘብ ምን ያህል ተቀንሶ ምን ያህል እንደሚመለስለት በዝርዝር የተደነገገ በመሆኑ ከላይ በተሰጠው ትርጓሜ መሰረት አመልካች ያቀረበው የዲኝነት ገንዘብ ይመለስልኝ ጥያቄ ሕጋዊ መሰረት ያለው ሆኖ ተገኝቷል።
ይህም እንኳ ቢታለፍ ይህ በሕግ ሽፊን ሳይሰጠው በዝምታ የታለፈውን ጉዲይ ከጉዲዩ ጋር ተመሣሣይ ይዘት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማመሳሰል ተገቢውን ትርጉም መከተል እንደሚቻልም ቋሚ ከሆኑት የሕግ አተረጓጏም ዘዳዎች አግባብነት ያለው የሕግ ትርጉም ዘይቤ አመልካች ነው።
ከዚህም አንፃር ሲታይ ተከሳሽ ከመጠራቱ በፉት ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሕ/ሕ/ቁ 232/1/ሀ/ እና /ለ/ መዝገብ በተዘጋ ጊዜ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ 232/1/ለ/ እንደተመለከተው ከሳሹ ከከፈለው የዲኝነት ገንዘብ ውስጥ ተገቢው ተቀንሶ ቀሪው እንዱመለስለት ሕጉ ከፈቀደ ተከሳሹ በመጠራቱ ምክንያት ተከሳሹ ሥልጣንን አስመልክቶ ባነሳው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የተነሣ መዝገብ በተዘጋ ጊዜ እንደ አግባብነቱ ከተከፈለው የዲኝነት ገንዘብ የሚቀነሰው ተቀንሶ ተራፉው እንዱመለስለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ 245/4/ መደንገጉ ከታወቀ መጥሪያው ወጭ መሆኑ ቢታወቅም፣ የዕግድ ትዕዛዝ የተሰጠ ቢሆንም ከሳሹ ለተከሳሹ መጥሪያውን ከማድረሱ በፉት በእራሱ ጠያቂነት ክሱን መተውን ገልፆ መዝገቡን ፍ/ቤቱ በዘጋው ጊዜ ክርክሩ ከደረሰበት የክርክር ደረጃ እና ሙለ የዲኝነት ገንዘብ የተከፈለበት ምክንያት የተሟላ ክርክር ተደርጎ ፍ/ቤቱ የተሟላ የዲኝነት አገልግልት እንዱሰጥ ተከራካሪውም ይህንኑ የተሟላ የዲኝነት አገልግልት ለማግኘት ያለውን መብት መነሻ በማድረግ የሚከፈል ለመሆኑ ከላይ የተመለከቱት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ 232 እና 245/4/ በግልፅ የሚያመለክቱ በመሆኑ በዚህ ጉዲይም የከሳሹ የዲኝነት ገንዘብ ይመለስልኝ ጥያቄ በይዘቱም ሆነ ከሕግ ግብ አንፃር ሕጉ በግልፅ ከሸፈናቸው ጉዲዮች ተመሣሣይ እንጂ የተለየ ሆኖ አይገኝም።
ከዚህም አንፃር ምንም እንኳ ከሳሽ የከፈልኩት የዲኝነት ገንዘብ በሙለ ይከፈለኝ በማለት የከፈለትን የዲኝነት ክፍያ የማግኘት መብት ያላቸው ባይሆንም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ 232/1/ለ/ እና 245/4/ በተነገረው መሰረት ከከፈለው የዲኝነት ገንዘብ የሚቀነሰው ተቀንሶ ተራፉውን መልሶ የማግኘት መብት እያለው የከሳሽ ጥያቄ ሕጋዊ መሰረት ያለው አይደለም በሚል በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው የሕግ ትርጉም መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ በ30/9/2003 ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ በ4/5/2004 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ ተሽሯል።
አመልካች አስቀድሞ ከከፈለው የዲኝነት ገንዘብ ውስጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ 232 በተመለከተው መሰረት ተገቢው የዲኝነት ገንዘብ ከተቀነሰ በኋላ ቀሪው ይመለስልለት ብለናል።
No topics extracted.