No summary available.
ሐምል 03 ቀን 2004 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፉሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ/ማ-ነ/ፈጅ ብርሃኑ ታደሰ ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - ነ/ፈጅ አብደልከሪም ዲውድ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የማቅረቢያው ጊዜ ያለፈበት ይግባኝ ይከፈት ዘንድ እንዱፈቀድ የቀረበውን ጥያቄ አንድ ፍርድ ቤት ተቀብል በበላይ ፍርድ ቤት ክርክር ሲደረግ በቆየበት ጊዜ የበታች ፍርድ ቤት በዋናው ጉዲይ ላይ የሚመራው ክርክር ሳይታገድ ቆይቶ የበላይ ፍርድ ቤቱ የይግባኝ ማስፈቀጃው ተቀባይነት ያገኘው ያላግባብ ነው በማለት በስነ ስርዓቱ ላይ ውሳኔ ቀድሞ ከሰጠ እና የበታች ፍርድ ቤቱ ይህንኑ የበላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ ማስፈቀጃው ላይ የሰጠውን ውሳኔ ሳይመለከት በዋናው ጉዲይ ላይ ውሳኔ ቢሰጥ ይኸው የበታች ፍርድ ቤት ውሳኔ ተፈፃሚነት ያለው መሆን ያለመሆኑን የሚመለከት ነው።የማስፈቀጃ ጥያቄው የቀረበው ለፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ሲሆን፣ ጥያቄ አቅራቢው የአሁኑ ተጠሪ ነበር። የይግባኝ ማቅረቢያው ጊዜ ሉያልፍበት የቻለው ወይም ይግባኙን በሥነ ሥርዓት ሕጉ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ሉያቀርብ ያልቻለው ጉዲዩን ይዞ ሲከታተል በነበረው ነገረ ፈጁ ስህተት /ጥፊት/ እንደሆነም በማመልከቻው ላይ ገልጾአል። ፍ/ቤቱም ይህን መነሻ በማድረግ የአሁን አመልካችን በመልስ ሰጪነን አስቀርቦ ክርክሩን ከሰማ በኋላ ጊዜው ያለፈው በነገረ ፈጁ ጥፊት ነው። ነገረ ፈጁም በዚህ ምክንያት የዱሲፔሉን እርምጃ ተወስድበታል የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት የተጠሪን ጥያቄ ተቀብልአል። በዚህ ውሳኔ የአሁኑ አመልካች የሰበር አቤቱታውን ለዚህ ችልት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ይህ ችልት ጊዜ ካለፈ በኋላ ይግባኝ እንዱከፈት ጥያቄ የሚቀርበው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 325 በተደነገገው መሰረት ሁኖ ጥያቄው ተቀባይነት ያለው ስለመሆን አለመሆኑ የሚመረመረው /የሚመዘነው/ ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 326 መሰረት መሆኑን፣ ጥያቄው ተቀባይነት አለው ወይንስ የለውም? የሚለው ነጥብ ሉወሰን የሚገባው እንደየአግባቡ በንኡስ ቁ/1/ ወይም /2/ መሰረት እንደሆነም ግልፅ ስለመሆኑ፣ በንዐስ ቁጥር 1 እንደተመለከተው አመልካቹ ወይም የፈቃድ ጥያቄ አቅራቢው ይግባኙን በጊዜው ለማቅረብ ያልቻለው በበቂ ምክንያት መሆኑ ፍ/ቤቱን ማሣመን ከቻለ ይግባኙን በአሥር ቀናት ውስጥ እንዱያቀርብ እንደሚፈቅድለት፣ በዚህ ረገድ ምክንያቱ በቂ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ፍሬ ነገር በፍ/ቤቱ የሚመዘን ከመሆን አልፍ በሕጉ የተቀመጠ የታወቀ /የተለየ/ መስፈርት እንደላለው፣በንዐስ ቁ./2/ የተቀመጠው ድንጋጌ ግን አመልካቹ ያቀረበው ምክንያት በንኡስ ቁ./1/ አባባል ሉስተናገድ የማይገባ ወይም ተቀባይነት የላለው ነው የሚባልበትን አግባብ የሚያመለክት ድንንጋጌ መቀመጡን፣ይኸውም በፈቃድ መጠየቂያው ማመልከቻ ላይ የተገለፀው ምክንያት ይግባኙን በጊዜው ማቅረብ ያልቻለው በአመልካቹ ጠበቃ ወይም ነገረ ፈጁ ወይም በወኪለ ያለመቅረብ እና በእነዚሁ ጉድለቶች መሆኑን የሚያመለክት ከሆነ ምክንያቱ በንኡስ ቁ./1/ እንደተነገረው በቂ ነው ልባል እንደማይገባ በግልጽ መደንገጉን፣ በዚህ ምክንያትም የይግባኝ ይከፈትልኝ ጥያቄው ተቀባይነት ለማግኘት አይችልም በማለት ግልጽ ድንጋጌ ሕጉ ማስፈሩን በምክንያትነት ይዞ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኙን መፍቀደ ግልፁን ሕግ በሚጻረር አኳኋን ነው በማለት በዚህ ረገድ የተሰጠውን ውሳኔ ሐምል 15 ቀን 2003 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሻረው መሆኑን የሰ/መ/ ያሳያል።
ከዚህ በሁዋላም የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረውን ዋናውን ጉዲይ ሲያከራክር ቆይቶ ጥቅምት 08 ቀን 2004 ዓ.ም. በዋለው ችልት የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ ያቀረበው ክስ በይርጋ የታገደ አይደለም፣በግራ ቀኙ መካከል የተፈረመው የገንዘብ ዋስትና ቦንድ ሕጋዊ ውጤት አለው በማለት በፍሬ ነገር ደረጃ የቀረበውን ክርክር አጣርቶ ተገቢውን እንዱወስን ጉዲዩን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመለሰ ሲሆን ይኸው ውሳኔ የተሰጠው ከሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ውጪ ነው በሚል የአሁኑ አመልካች ውሳኔው እንዱታረም ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ጥቅምት 20 ቀን 2004 ዓ/ም አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ይኸው ችልትም የአመልካችን አቤቱታ መርምሮ የሰበር ሰሚው ችልት ውሳኔ መኖሩን እንዱያውቅ ያለመደረጉንና ክርክሩም እንዲይካሄድ ያለመታገደን በምክንያትነት ይዞ የራሱን ውሳኔ መልሶ የሚሽርበት አግባብ ያለመኖሩን ጠቅሶ የአመልካችን አቤቱታ ሕዲር 07 ቀን 2004 ዓ.ም. በዋለው ችልት ሳይቀበለው ቀርቷል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በዋናው ጉዲይ ላይ የሰጠው ውሳኔ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔን ውጤት አልባ የሚያደርግ ነው በማለት በጊዜውም የሰበር ሰሚ ችልቱን ውሳኔ ግልባጭ ለይግባኝ ሰሚው ችልት እንዱደረሰው ለማድረግ ተገቢውን ሁለ በሚመለከተው አካል በኩል አቅርቦ የይግባኝ ሰሚው ችልት በክረምት ጊዜ በነበረው ስራ ዋናውን መዝገብ መርምሮ ውሳኔ በመስጠቱ ችግሩ መከሰቱን ገልፆ በዋናው ጉዲይ ላይ የተሰጠው ውሳኔ እንዱሻርለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖበት ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪም ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ በሰጠው መልስ የአመልካች የሰበር አቤቱታ አቀራረብ ሕጋዊ ስርዓቱን ተከትል ያለመቅረቡንና በዋናው ጉዲይ ላይ ውሳኔ ላሰጥ የቻለውም በአመልካች ነገረ ፈጅ ችግር ስለመሆኑ ዘርዝሮ የአመልካች አቤቱታ ተቀባይነት ሉኖረው አይገባም በማለት ተከራክሯል።
አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማናገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምረናል። እንደመረመርነውም የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥቅምት 08 ቀን 2004 ዓ/ም በዋለው ችልት በመ/ በሆነው የሰጠው ውሳኔ ሕጋዊ ውጤት ሉኖረው ይገባል ወይስ አይገባም የሚለው ጭብጥ ምላሽ የሚያስፈልገው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በዋናው ጉዲይ ላይ ውሳኔ ላሰጥ የቻለው በተጠሪ በኩል የቀረበውን የይግባኝ ማስፈቀጃ አቤቱታውን በመመርመር ተቀባይነት አለው ወደሚለው ድምዲሜ ከደረሰ በኋላ መሆኑን፣የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው የይግባኝ ማቅረቢያ ፈቃጅ ውሳኔ ግን በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሐምል 15 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የተሻረ ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ችልት በዋናው ጉዲይ ላይ ጥቅምት 08 ቀን 2004 ዓ.ም በዋለው ችልት ውሳኔ መስጠቱን፣ይህ ውሳኔ የተሰጠውም ይግባኙ የማቅረቢያ ጊዜውን ጠብቆ ያልቀረበ፣ጊዜው አልፍም ይግባኙን ለማቅረብ በቂና ሕጋዊ ምክንያት የለም ተብል በሰበር ሰሚው ችልት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ነው።የሰበር ሰሚው ችልት ስለማስፈቀጃው በሰጠው ውሳኔ ላይም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 325 እና 326 ድንጋጌዎችን ይዘትና መንፈስ የተረጎመ ሲሆን በዚህ ችልት ሕግ በመተርጎም የሚሰጠው ውሳኔም በየትኛውም እርከን በሚገኝ ፍርድ ቤት አስገዲጅ መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የምንረዲው ጉዲይ መሆኑንም ተገንዝበናል።
የተጠሪ ነገረ ፈጅ የአመልካች ነገረ ፈጅ የሰበር አቤቱታ አቀራረብ ሕጋዊ ስርዓቱን ተከትል ያልቀረበ ነው በማለት መቃወሚያ አቅርበዋል። ይሁን እንጂ የአመልካች ነገረ ፈጅ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ጥቅምት 08 ቀን 2004 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ከሰጠው ውሳኔ አንፃር ተፈፃሚነት ሉኖረው አይገባም በማለት ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ችልት ሕዲር 07 ቀን 2004 ዓ.ም. በሰጠው ትእዛዝ ያለመሆኑን የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ በዋናው ጉዲይ ላይ ጥቅምት 08 ቀን 2004 ዓ.ም. ውሳኔ ከተሰጠና ይህ ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሞበታል የሚል ቅሬታ ካለው አመልካች የሰበር አቤቱታውን ውሳኔ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ ዘጠና ቀናት ውስጥ ለሰበር ሰሚው ችልት ማቅረብ የሚችል መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 እና 22 ድንጋጌዎች የሚያሳዩት ጉዲይ ነው። በዚህም መሰረት አመልካች የሰበር አቤቱታውን ያቀረበው ህዲር 27 ቀን 2004 ዓ.ም.
በመሆኑና በዋናው ጉዲይ ላይ ውሳኔ የተሰጠው ጥቅምት 08 ቀን 2004 ዓ.ም. እንደመሆኑ መጠን በሕጉ የተመለከተው የዘጠና ቀናት የሰበር አቤቱታ ማቅራቢ ጊዜ ሳያልፍ አቤቱታውን ያቀረበ በመሆኑ በዚህ ረገድ የተጠሪ ነገረ ፈጅ ያቀረቡት መቃወሚያ ተቀባይነት ያለው ሁኖ አልተገኘም።
ወደዋናው ጉዲይ ስንመለስ በአንድ ፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ ስህተት አለበት የሚል ወገን በሕጉ አግባብ ቅሬታውን ለበላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ወገኖች ከተራከሩ በኋላ በጉዲዩ ላይ የበታች ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በበላይ ፍርድ ቤት ከተሻረ በተሻረው ውሳኔ መሰረት የሚፈጸም ነገር ሉኖር አይችልም።የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 349 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስም ይህንኑ ድምዲሜ የሚያጠናክር ነው። በበታች ፍርድ ቤት የሚደረገውን ክርክር ሳያሳግድ በበላይ ፍርድ ቤት ክርክር አድርጎ የበላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ እስከሚታወቅ ድረስ መቆየትና የበላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተከራካሪ ወገን ከአወቀው በኋላ ለበታች ፍርድ ቤት የበላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ሳያስታውቅ በመቆየቱ ወይም በመቅረቱ ብቻ የበላዩን ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚቃረን የበታች ፍርድ ቤት ውሳኔ ሕጋዊ ውጤት እንዱኖር የሚደረግበት የስነ ሥርዓት ሕግ አግባብም የለም።በመሆኑም ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 349 ድንጋጌ መንፈስም ሆነ ከአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀፅ 2(1) ድንጋጌ አንፃር የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ጥቅምት የሰጠው ውሳኔ ሕጋዊ ውጤት የላለው በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሥነ ሥርዓት ሕግ ግድፈት የተፈፀመበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ. 60886 ጥቅምት 08 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሮአል።
የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ. 60886 ጥቅምት 08 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ይግባኙ እንዲይቀርብ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ሐምል 15 ቀን 2003 ዓ/ም ውሳኔ ከሰጠ በሁዋላ የተሰጠ በመሆኑ ተፈጻሚነት ሉኖረው የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የማይነበብ የአመስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.