No summary available.
ሰኔ 18 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ሽመልሽ አማረ - ጠበቃ ታምሩ ወልደማርያም ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አማረ መኮነን - ከጠበቃ ወልደስላሴ ብርቱ ጋር ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በላለበት ታይቶ ውሳኔ የተሰጠበት ወገን በላለበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ እንዱነሳለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 78(1) መሰረት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሚያቀርበው ጥያቄ የአንድ ወር ጊዜ መቆጠር የሚጀምርበትን ቀን የሚመለከት ነው።ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ፣የአሁኑ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ።የስር ከሳሽ በአሁኑ አመልካች ላይ ክስ መስርተው ፍርድ ቤቱ ለአሁኑ ተጠሪ በሥርዓቱ መሰረት መጥሪያ እንዱደርሳቸው ትዕዛዝ ሰጥቶ የአሁኑ ተጠሪ ተከሳሽን ሉያገኙ እንዲልቻለ ገልጸው ምትክ መጥሪያ በጋዜጣ እንዱደረግ አመልከተዋል። ፍርድ ቤቱም የተጠሪን ጥያቄ በመቀበል አመልካችን በጋዜጣ እንዱጠሩ አድርጎ በጥሪው መሰረት አመልካች ስላልቀረቡ ጉዲዩን አመልካች በላለበት በማየት ዋናውን ጉዲይ ለተጠሪ ወስኗል። ከዚኅም በኋላ የአሁኑ አመልካች የካቲት 30 ቀን 2003 ዓ.ም. በተጻፈ ማመልከቻ በላለበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 78 መሰረት ውሳኔው ተነስቶ ወደ ክርክሩ እንዱገቡ ትዕዛዝ እንዱሰጥላቸው አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ጉዲዩ በሕጉ የተመለከተውን የአንድ ወር ጊዜውን ጠብቆ ያልቀረበ መሆኑን ጠቅሰው አቤቱታው ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ አመልካች ውሳኔው መሰጠቱን የተረደት ጥር 30 ቀን 2003 ዓ/ም ሁኖ በላለበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ እንዱነሳላቸው አቤቱታ ያቀረቡት የካቲት 30 ቀን 2003 ዓ.ም. በመሆኑና ይህም የአንድ ወር ጊዜ ካለፈ በሁዋላ በመሆኑ ጉዲዩ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የአመልካችን ጥያቄ ሳይቀበለው ቀርቷል። ከዚኅም በኋላ የአሁኑ አመልካች ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ውስጥ የተመለከቱት የይርጋ ጊዜዎች አቆጣጠር መታየት ያለበት በራሱ በፍትሕብሓር ስነ ሥርዓት ሕጉ መሰረት እንጂ በፍትህ ብሓር ሕጉ በተመለከቱት ድንጋጌዎች ያለመሆኑን፣ ከዚህ አንፃር ጉዲዩ ሲታይም አመልካች በጉዲዩ ላይ ውሳኔ መሰጠቱን ከተረደበት ከጥር 30 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ የአንድ ወር ጊዜ መቆጠር ያለበት መሆኑን፣ ይህም ጊዜ እስከ የካቲት 29 ቀን 2003 ዓ.ም. ድረስ መሆኑን ገልፆ አመልካች የካቲት 30 ቀን 2003 ዓ.ም. ያቀረቡት አቤቱታ በሕጉ የተመለከተው የአንድ ወር ጊዜ ካለፈ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በሚለ ምክንያቶች የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሙለ በሙለ አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም በፍትሒ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ የተመለከቱት የይርጋ ድንጋጌዎች አቆጣጠርን በተመለከተ ሕጉ የማይገልጽ በመሆኑ ተፈፃሚነት ያላቸው በፍትሒብሓር ሕጉ ከቁጥር 1948 ጀምሮ ያለት ድንጋጌዎች ናቸው፣ ከዚህ አንፃር ጉዲዩ ሲታይም አመልካች በጉዲዩ ላይ በላለበት ውሳኔ የተሰጠ መሆኑን የተረደት ጥር 30 ቀን 2004 ዓ.ም. ከሆነ የይርጋው ጊዜ አቆጣጠር ይህንኑ ቀን መነሻ ሉያደርግ አይገባም በማለት የሚከራከሩ መሆኑን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖበት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ተጠሪ ቀርበው በጽሐፍ በሰጡት መልስ በፍትሃ ብሓር ስነ ስርዓት ሕጉ ውስጥ ያለት የይርጋ ድንጋጌዎች አቆጣጣር በራሱ በፍትሒብሓር ሥነ ሥርኣት ሕጉ መሰረት እንጂ በፍትሀብሄር ሕጉ ላሆን አይችልም ሲለ የተከራከሩ ሲሆን አመልካች በበኩላቸው የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረመው የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ስር የተመለከቱት የይርጋ ድንጋጌዎች አቆጣጠር መታየት ያለበት በራሱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ መሰረት ነው? ወይንስ በፍ/ብ/ህጉ በቁጥር 1848 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ነው? የሚለው ነው። ይህንኑ ጭብጥ ለመወሰን በመጀመሪያ የይርጋ የጊዜ ገደቡ መቆጠር ያለበት ከመቼ ጀምሮ ነው? የሚለውን ጥያቄ መመለስና በሁለተኛ ደረጃ በበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ያቀረበውን አቤቱታ በይርጋ ቀሪ ነው ተብል መወሰኑ ተገቢ መሆኑን መመርመር ያስፈልጋል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች በላለበት ጉዲዩ ታይቶ ስለመወሰኑ የተረደት ጥር 30 ቀን 2003 ዓ.ም. መሆኑንና ውሳኔውን ለሰጠው ፍርድ ቤት ጉዲዩ ባለበት እንዱታይላቸው አቤቱታቸውን ያቀረቡት የካቲት 30 ቀን 2003 ዓ.ም. መሆኑን ነው።የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ያደረጉት ደግሞ የይርጋው ጊዜ መቆጠር ያለበት ከጥር 30 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 78(1) ስር የተመለከተው የአንድ ወር የጊዜ ገደብ የሚያበቃው የካቲት 29 ቀን 2003 ዓ.ም. ስለሆነ እና አመልካችም ከዚህ ቀን በኋላ አቤቱታቸውን ማቅረባቸው ተቀባይነት የለውም በማለት መወሰናቸውን ተገንዝበናል።
በመሰረቱ በፍትሒብሓር ስነ ሥርዓት ሕጉ ስር የተለያዩ የይርጋ ድንጋጌዎች ያለ ሲሆን አቆጣጠራቸውን በተመለከተ ግን ግልጽ ድንጋጌዎች የለም። በልላ በኩል በፍትሒ ብሓር ሕጉ ስር ስላለት የይርጋ ድንጋጌዎች የአቆጣጠር ሁኔታ ሕጉ በቁጥር 1848 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ግልፅ ስላት አስቀምጧል። የሥነ ሥርዓት ሕጎች ዋነኛ ዓላማ ለፍ/ቤት የሚቀርቡ ክርክሮች ባነሰ ወጪ፣ በተቀላጠፈና ፍትሃዊ በሆነ ሥርዓት እልባት እንዱያገኙ ማድረግ ነው።
በመሆኑም በሥነሥርዓት ህጎች የሰፈሩ የጊዜ ገደቦች አፈጻጸም ባንድ ጉዲይ ካለት ተከራካሪዎች ባሻገር የላልች ተከራካሪዎች ጥቅም ፣ በፍርድ ቤት መኖር ያለበትን የሙግት አመራርና አጠቃላይ የሀብትና የጊዜ አጠቃቀምን የሚመለከቱ ናቸው ተብል ይታሰባል። በሥነሥርዓት ሕጉ የሰፈሩ ጊዜን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ይዘትና ዓላማ ይርጋን አስመልከቶ በፍትሀብሄር ሕግ ቁጥር 1856/2/ ከሰፈረው የይርጋ ጉዲይ በተከራካሪዎች ካልተነሣ ፍርድ ቤት አይነሳም ከሚለው ሕግ የተለየ ነው።በፍትሐብሕር ሕግ የሰፈረው የይርጋ ሕግ ዋነኛ ዓላማ የተዋዋዮችን ጥቅም መጠበቅ ነው። የዚህ መብት ተጠቃሚ የሆነ ተከሣሽ ይርጋውን ካላነሣም የሚጎዲው ራሱ ብቻ ነው። ስለሆነም ተዋዋይ ወገን የተወውን መብት ፍርድ ቤት በራሱ አነሣሽነት እንዱያነሣው አይፈቀድም። በሥነሥርዓት ሕጉ የተቀመጡ የጊዜ ገደቦች መከበር አለመከበራቸውን ግን ፍርድ ቤቱ የመከታተል ሃላፉነት አለበት። በተከራካሪ ወገን ባይነሣ እንኳን በሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 195 እንደተደነገገው ጊዜው ካለፈ በኋላ የተከናወነው ነገር ሁለ እንዲልተፈፀመ ሆኖ ስለሚቆጠር የሥነሥርዓት የጊዜ ገደቦች ተሟጋቾችን ብቻ ሳይሆን ፍርድ ቤቱንም ጭምር የሚመለከቱ ናቸው። በመሆኑም በሥነሥርዓት ሕጉ በግልጽ የሰፈረው የጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ የሚቀርብን ማንኛውንም ጉዲይ ፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነትም ቢሆን ውድቅ ማድረግ እንዱሚችል ይህ ችልት ከላይ የተመለከቱትን ሕጋዊ ምክንያቶችን በማንሳት በመ/ በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝን ፍርድ ቤት የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። ይህን ጉዲይ በዚህ መዝገብ ማንሳት ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት በስነ ስርዓት ሕጏች ያለት የጊዜ ገደቦች በመሰረታዊ ሕጎች ካለት የጊዜ ገደቦች የተለዩ ናቸው በማለት የተሰጠ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም በሥነ-ሥርዓት ሕጎች የተካተቱትን የይርጋ ገደቦችን አቆጣጠር በተመለከተ በፍትሐ ብሓር ሕጉ ስር ከተቀመጡት የጊዜ ገደብ አቆጣጠር አንጻር ማየትም አይቻልም የሚል ክርክር ማስነሳቱ የማይቀር በመሆኑ ይህንኑ እልባት ለመስጠት ነው። በመሆኑም ከላይ የተጠቀሰው የአስገዲጅ የሕግ ትርጉም ምክንያቶች የሚያጠነጥኑት በስነ ስርዓት ሕጎች ያለትን የጊዜ ገደቦች ሉነያሳ የሚችለው ፍርድ ቤት ነው? ወይስ ተከራካሪ ወገን ብቻ? በሚለው ጥያቄ በመሆኑ በሥነ-ሥርዓት ሕጉች ያለትን የጊዜ ገደቦችንና በመሰረታዊው ሕግ ውስጥ የተካተቱትን የይርጋ ገደቦችን ባሕርይ መለየቱን የሚያሳይ ከሚሆን በስተቀር በይርጋው ጊዜ አቆጣጠር ላይም ሁለቱም ህጎች መሰረታዊ ልዩነት አላቸው ወደሚለው ድምዲሜ ሉያድርስ የሚችል አይደለም። ይልቁንም ሕጉቹ እርስ በእርሳቸው ያላቸው ትስስርና አላማቸው ሲታይ በሥነ-ሥርዓት ሕጉ በግልጽ ምላሽ ያላገኙትን ጉዲዮች በዋናው ሕግ አግባብነት ባላቸው ድንጋጌዎች ምላሽ በመስጠት ሕጉቹ ውጤታማ በሆነ መንገድ ስራ ላይ እንዱወለ የሚያስችል መሆኑን ያስገነዝባል። ስለሆነም ከዚህ አንጻር ሲታይ በፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ስለይርጋ አቆጣጠር ግልፅ ድንጋጌ የላለ በመሆኑ ይህንኑ የሕጉን ክፍተት መሙላት የሚቻለው ስለጊዜ አቆጣጠር በፍተሐብሓር ሕጉ የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን በመመልከት ላሆን ይገባል።
ይህ አይነቱ አተረጓጎምም ሕጉቹ ውጤታማ በሆነ መንገድ ስራ ላይ እንዱውለ የሚያስችል በመሆኑ በጠቅላላ የሕግ አተረጓጎም ደንቦችም ተቀባይነት ያለው አካሄድ ነው።
አንድ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ትእዛዝ ወይም ውሳኔ የተሰጠበት ወገን ጉዲዩ ባለበት እንዱታይ አቤቱታውን ማቅረብ ያለበት ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ትዕዛዝ መሰጠቱን ወይም በጉዲዩ ላይ ውሳኔ መሰጠቱን በተረዲው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መሆን እንዲለበት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 78(1) ድንጋጌ የሚያሳይ ሲሆን የዚሁ ድንጋጌ የእንግሉዝኛው ቅጅም "Any defendant against whom a decree is passed or order made ex-parte or in default of pleading; may, within one month of the day when he became aware of such decree or order, apply, to the court by which the decree was passed or order made for an order to set it aside." በሚል የተቀመጠ ሲሆን የአንድ ወር ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው አቤቱታ አቅራቢው ስለሁኔታው ከተረዲበት ቀን ጀምሮ ስለመሆኑ በግልጽ አያሳይም። በፍትሒ ብሓር ሕጉ ስር ባለት የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር ድንጋጌዎች ግን የመጀመሪያው ቀን ለይርጋው ጊዜ መቆጠር መነሻ ላሆን እንደማይገባ በግልጽ በቁጥር 1848 ስር ተመልክቶ ይገኛል። ይህ ድንጋጌ መሰረት ሲደረግም አመልካች ጉዲዩን ተረዲሁ የሚለበት ጥር 30 ቀን 2003 ዓ/ም ጊዜ ለአንድ ወሩ የጊዜ አቆጣጠር መነሻ ላሆን አይገባም። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች በፍትሃ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ያለት የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር በፍትሐ ብሓር ሕጉ በተመለከቱት የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር ስላቶች ሉመሩ የሚችለ አይደለም በማለት የደረሱበት ድምዲሜ ሕጉቹ ያላቸውን ትስስርና የትርጉሜው ውጤት በመሰረታዊ ሕጉ ጥበቃ ባገኙት መብቶች ላይ ሉያስከትል የሚችለውን አለታዊ እንድምታ ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል።
በፍተሐብሄር ስነ ሥርዓት ሕጉ የተመለከቱት የይርጋ ድንጋጌዎች አቆጣጠር መገዛት ያለበት በፍተሐብሓር ሕጉ በተመለከቱት የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር ድንጋጌዎች አንፃር ነው ወደሚለው ድምዲሜ ከደረሰን የአመልካች አቤቱታ የአንድ ወር የጊዜ ገደብ ያለፈበት መሆን ያለመሆኑን መመልከቱ ተገቢ ይሆናል። በዚህም መሰረት አመልካች በላለበት ጉዲዩ ታይቶ ውሳኔ መሰጠቱን የተረደት በ30/05/2003 ሲሆን ውሳኔው ተነስቶ ባለበት ጉዲዩ እንዱታይላቸው አቤቱታ ያቀረቡት በ30/06/2003 ዓ.ም. ነው። ከላይ በተሰጠው ትርጉም መሰረት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1848 መነሻ ሲሆን የአንድ ወር ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ከየካቲት አንድ ቀን 2003 ዓ/ም ጀምሮ ነው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አንድ ወር ሲቆጠር ደግሞ የአመልካች አቤቱታ በይርጋ የሚታገደው ከመጋቢት 01 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ባለት ጊዜያት ከቀረበ ነው። አመልካች ጥያቄአቸውን ያቀረቡት ግን የካቲት 30 ቀን 2003 ዓ.ም. በሕጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ነው። እንዱህ ከሆነ አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ ከይርጋ በመለስ ያለት ላልች ሕጋዊ መመዘኛዎች በስር ፍርድ ቤት ታይተው ሉስተናገድ የሚገባው ሁኖ አግኝተናል። ሲጠቃለልም ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሰኔ 15 ቀን 2003 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/6 ጥር 09 ቀን 2004 ዓ.ም የፀናው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ስር የተመለከቱት የይርጋ ድንጋጌዎች አቆጣጠር መታየት ያለበት በራሱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ መሰረት ሳይሆን በፍ/ብ/ህጉ በቁጥር 1848 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ነው ብለናል።
የጊዜ አቆጣጠሩ ከዚህ አንፃር ሲታይም የአመልካች ጥያቄ የአንድ ወር የጊዜ ገደብ ያላለፈበት በመሆኑ በስር ፍርድ ቤት ላታይ የሚገባው ሁኖ ስለአገኘን ከይርጋ በመለስ ባለት ላልች ክርክሮች ጉዲዩ ታይቶ አመልካች በላለበት ታይቶ የተወሰነው ውሳኔ ሉነሳ ይገባል? ወይስ አይገባም? የሚለው ጭብጥ እና በሕጉ አግባብ ተከታዩ ሂደት ታይቶ ጉዲዩ እንዱወሰን ለፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 341(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.