No summary available.
ሰኔ 18 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ካሳዬ ያደቴ ከጠበቃ ኮ/ል መላኩ ካሣዬ ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- ሲኞር ፍራንችስኮ ቬንሲያን የቀረበ የለም መዝገቡ ያደረው ለውሣኔ ሲሆን ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ አመልካች ከፍርድ አፈፃፀም መምሪያ በአደራ የተረከባቸውን የተጠሪ ንብረቶች አልመለሰም በሚል ተጠሪ የንብረቶቹን ዝርዝር እና ግምት በመጥቀስ ባቀረበው ክስ በፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተጀመረ ሁኖ አሁን የሚያከራክረው መቆፈሪያ ማሽን በተመለከተ ሲሆን ይሄው ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤት የፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ማሽኑ ተገምቶ ፍርድ እንዱሰጥበት በመለሰው መሰረት አመልካች ማሽኑ ያለበትን ቦታ ማሳየት ባለመቻለ ከዚህ ቀደም በተሰጠው ውሣኔ መሰረት አሁንም በርትዕ ብር 2ዐዐ,ዐዐዐ/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል በመወሰኑ እና ይሄው ውሣኔ በፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመጽናቱ የተፈጸመው መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች በማመልከቱ የቀረበ ነው።
አመልካች ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞባቸዋል ያለዋቸውን ነጥቦች በማንሳት ያቀረቡ ሲሆን ፍሬ ሃሣቡ፡- በዚህ ጉዲይ የፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማሽኑ ተገምቶ ውሣኔ እንዱሰጥበት በማለት ወደ ታች ፍርድ ቤት መልሶ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች ይሄንን ሳያከብሩ አሁንም በድጋሚ በርትዕ ውሣኔ መስጠታቸው ተቀባይነት ያለው አካሄድ ባለመሆኑ አመልካች በበታች ፍርድ ቤትም ሆነ በተለያዩ አካላት ባቀረበው አቤቱታ ላልች እቃዎችን እንጅ የመቆፈሪያ ማሽን ያልተረከበ ስለመሆኑ ተከራክሮ እያለ እና ላልቹን የተረከባቸውን ደግሞ በብር 8,ዐዐዐ /ስምንት ሺህ ብር/ መሸጣቸውን የተከራከሩ በመሆኑ፣ በበታች ፍርድ ቤቶች ያቀረብናቸውም ሰዎች ብረታ ብረት መግዛታቸውን እና መቆፈሪያ ማሽን ያልገዙ ስለመሆኑ እና ይሄንንም የገዙትን እቃ ብር 4ዐዐ /አራት መቶ ብር/ በማትረፍ የሸጡ ስለመሆኑ የገለጹ በመሆኑ ተጠሪ የክስ ምክንያት የለውም ተብል ክሱ ወድቅ መሆን ሲገባው የተሰጠው ውሣኔ አግባብነት የላለውና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት እንዱታረምላቸው ተከራክረዋል። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ታዞ በሰጠው መልስ በእርግጥ የፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት በላልቹ እቃዎች ላይ በበታች ፍርድ ቤት የተላለፈው ፍርድ በአግባቡ ስለመሆኑ በማመላከት ያጸናው ሁኖ የዚህ አከራካሪ ማሽን ግን አይነቱ ሉታወቅ እና በባለሙያ ሉገመት እየተቻለ ይሄ ሳይደረግ መታለፊ እና በርትዕ መወሰኑ አግባብነት የላለው ነው ተብል ወደ ታች መመለሱ ግልጽ ቢሆንም አመልካች ማሽኑን የገዛውን ሰው ማቅረብም ሆነ ማሽኑ ያለበትን ቦታ ማሳየት ባለመፈለጋቸው፣ ያቀረቡትም ሰው ስለማሽኑ ሲጠየቁ ማሽን ያለመግዛታቸውን ሁኖም ግን ብረታ ብረት ስለመግዛታቸው ብቻ በመግለጻቸው ታልፍ የተሰጠ ውሣኔ በመሆኑ እና ንብረቶቹን ስለመረከቡ ደግሞ ፈርሞ የተረከበበት ሰነድ ስላለ አመልካች ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የላለው በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ የሚነቀፍበት ምክንያት የለም በማለት ተከራክሯል። አመልካችም የመልስ መልስ በማቅረብ ቅሬታቸውን በማጠናከር ተከራክሯል።
ግራ ቀኙ መካከል የተደረገው ክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ ከተያዘው ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
እንደመረመረውም የበታች ፍርድ ቤቶች አከራካሪውን የመቆፈሪያ ማሸን ግምት በተመለከተ ወደ ድምዲሜ የደረሱት ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ስለመሆኑ ወይም ስላለመሆኑ በመመልከት ለተያዘው ጉዲይ እልባት መስጠት ተገቢ ሁኖ ተገኝቷል።
በዚህ መሰረት ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ በመጀመሪያ ደረጃ የመቆፈሪያ ማሽኖቹን በተመለከተ አመልካች አልተረከብኩም የሚል ክርክር በዚህ ደረጃ እያነሳ ስለመሆኑ መመልከት ይቻላል። ሁኖም ግን ኃላፉነትን በተመለከተ ከዚህ በፉት እስከ ፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችልት በተደረገ ክርክር እልባት ያገኘ እና የፋ/ሰበር ሰሚ ችልት በመዝ . ግንቦት 19 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በዋለው ችልት ጉዲዩን ወደ ፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲመልስ አሁን የሚያከራክረውን ማሽን ግምት በርትዕ ለመወሰን በባለሙያ በማስገመት ውሣኔ ላሰጥበት የሚቻል በመሆኑ ይሄው ስርዓት ሉፈጸም ይገባል በሚል ስለመሆኑ መመልከት ይቻላል።
በመሆኑም አመልካች የመቆፈሪያ ማሽኑን አልተረከብኩም በማለት ያነሳው ክርክር ቀደም ሲል በውሣኔ በተቋጨ ጉዲይ ላይ በመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 5/1/ መሰረት ተቀባይነት ያለው አይደለም።
ሁኖም ጉዲዩ የተመለሰለት ፍርድ ቤት አከራካሪውን ማሽን ለማስገመት ተገቢውን ትጋት አድርጓል ወይ ? የሚለውን ነጥብ መመልከት ተገቢነት ይኖረዋል። ጉዲዩ ወደ ታች ፍርድ ቤት ከተመለሰ በኋላ ፍርድ ቤቱ ማሽኑ ያለበትን ቦታ ወይም የገዛውን ሰው እንዱያቀርብ የተጠየቀ ሲሆን አመልካችም ማሽኑን እንደቀድሞ ሁለ እንዲልተረከበ የተከራከረ ሲሆን የገዛውንም ሰው እንዱያቀርብ ታዞ አመልካች ያቀረበው ሰው ማሽን እንዲልገዛ እና ብረታ ብረት እንደገዛ የገዛውንም ብረታ ብረት ብር 4ዐዐ /አራት መቶ ብር/ በማትረፍ እንደሸጠ ገልጧል። ጉዲዩ የተመለሰለት ፍርድ ቤትም ይሄንኑ ምክንያት በማድረግ ቀድሞ በርትዕ ብር 2ዐዐ,ዐዐዐ/ ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ተብል የተወሰነውን ውሣኔ በድጋሚ በመቀበል ወስኗል።
No topics extracted.
ሁኖም ግን አንድ ጉዲይ በበላይ ፍርድ ቤት በነጥብ ሲመለስ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በመጣራት ድምዲሜ ላይ ለመድረስ ተገቢውን ትጋት ማድረግ ያለበት ስለመሆኑ ከፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ 343/1/ ድንጋጌ ይዘት እና ዓላማ መገንዘብ ይቻላል። ይሄ አከራካሪው የመሬት መቆፈሪያ ማሽን ያገለገለ ስለመሆኑ እስከታወቀ ድረስ ፍርድ ቤቱ ዓይነቱን በተመለከተ ከግራ ቀኙ ወይም በመዝገቡ ውስጥ ካለት ሰነድች በመመልከት እና በመግለጽ አግባብነት ባለው ባለሙያ እንዱገመት በማድረግ ቢያንስ በርትዕ ለሚሰጠውም ውሣኔ መነሻ ነገር ማስቀረብ እየተቻለ እንደዚህ ዓይነት እና ተመሳሳይ ጥረት ሳይደረግ በደፈናው በርትዕ ቀድሞ የተሰጠውን ውሣኔ በድጋሚ በመቀበል ውሣኔ መስጠቱ ከፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የተሰጠውን ጉዲዩ የሚጣራበትን አግባብ ያልተከተለ በመሆኑ አግባብነት የላለው የክርክር አመራር በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብለናል። ባጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች ቀደም ሲል ከዚህ የሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠውን መመሪያ ሳይከተለ እና ተገቢውን ማጣራት ሳያደርጉ የደረሱበት ድምዲሜ አግባብነት የላለውና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
የፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝ. ግንቦት 22 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝ. በቀን 24/5/2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት አከራካሪውን የመሬት መቆፈሪያ ማሽን ያገለገለ ስለመሆኑ እና ላልች ስለማሽኑ ከመዝገቡ እና ከክርክሩ የተገኙትን ነጥቦች ለሚመለከተው ባለሙያ በመግለጽ በወቅቱ የነበረው ዋጋ ሙያዊ ግምት እንዱቀርብ በማድረግ እና በማስገመት ቀደም ሲል በዚህ የሰበር ሰሚ ችልት በተሰጠው ውሣኔ መሰረት ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ውሣኔ እንዱሰጥበት በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ 343/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።