No summary available.
ግንቦት 09 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገብረሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነገፈ ፈጅ ዮሴፍ ቀውዬ ተጠሪ፡- ለገሰ ጌታሁን ጠበቃ አቶ ለገሰ ማሞ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን የሚከተውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ አንድ ፍ/ቤት በንብረት ላይ የሰጠውን የዕግድ ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 158 እንደተደነገገው መልሶ ለማስነሳት የሚቻልበትን አግባብ የሚመለከት ነው።
በከሣሽ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በተከሣሽ አቶ ኃይለ ሃብቴ መካከል በነበረው የብድር ገንዘብ ክርክር ከሣሽ ለፍርድ አፈፃፀም ዋስትናው ይሆነው ዘንድ በተከሣሽ እና በባለቤቱ ስም ተመዝግቦ በሚገኘው ት/ቤት ላይ ክሱ በቀረበበት ፍ/ቤት አማካኝነት ታግድ እንዱቆይ የሚያስችል ትዕዛዝ ሐምል 29 ቀን 2002 ዓ.ም እንዱሰጥበት አድርጓል።
የአሁን ተጠሪ በበኩል ህዲር 10 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ ይህ የዕግድ ትዕዛዝ የተላለፈበትን ንብረት ከተከሣሽ እና ከባለቤቱ ጋር በተደረገ የሽያጭ ስምምነት በግንቦት 09 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሽያጭ ውል በብር 80,000.00 ገዝቻለሁ። ይህንንም የሽያጭ ውል ያደረግነው በሲዲማ ውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ነው። እንደውለ ሻጭ ሉፈጽሙ ስላልቻለ ለሽቢዲኖ ወረዲ ፍ/ቤት ክስ አቅርቤ ስመ-ሀብትነቱን ወደ ስሜ ለማዞር ስሞክር መታገደን ተረድቻለሁ። ስለሆነም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 158 መሰረት በህግ አግባብ በገዛሁት ቤት ላይ የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ይነሣልኝ በማለት ጠይቋል።
የአሁን አመልካችም የዕግድ ትዕዛዙን የማይነሳበትን ምክንያት በመዘርዘር ተከራክሯል። ጉዲዩን በቅድሚያ የተመለከተው የሲዲማ ዞን ከፍ/ቤት አስቀድሞ የሰጠውን የዕግድ ትዕዛዝ ለማንሳት የሚያበቃ ክርክርና ማስረጃ አልቀረበም። ስለሆነም የዕግደ ትዕዛዝ አይነሣም የሚል ዲኝነት ሲሰጥ፤ ይግባኝ ሰሚው የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በበኩለ የሽያጩ ተግባር የተፈፀመው የዕግድ ትዕዛዝ ከመስጠቱ በፉት ስለሆነ የሽያጭ ውለም በሚመለከተው አካል በመመዝገቡና በህግ የሚጠየቀውም መስፈርት ውለ በመዝገብ መፃፍን እንጂ የስመ ሃብትነት ዝውውር በግልጽ በሕግ እንደ ማሟያ ስላልተመለከተ ቀደም ሲል የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ሉነሣ ይገባል በማለት ሽሮታል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህ በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠው የተለየ ዲኝነት ጉድለት የለበትም በማለት የአሁን ተጠሪን ሳይጠራ አመልካችን በማሰናበቱ ይህ የሰበር ክርክር ሉቅርብ ችሎል።
በዚህ የሰበር ደረጃ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በፅሐፍ ያቀረቡ ሲሆን በይዘቱ ከዚህ በፉት ካቀረቡት የተለየ አይደለም። የተለየው ነጥብ ቢኖር ቀደም ሲል በሻጭ ላይ ባቀረቡኩት ክስ መሰረት አስወስኜ የፍርድ ባለመብት መሆኔም ይታወቅልኝ የሚለው ነው። እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
የአሁን ተጠሪ በፍ/ቤት የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ሉነሣልኝ ይገባል ሲል ያቀረበው ክርክርና ማስረጃ፤ ይግባኝ ሰሚው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠው የዕግድ ትእዛዝ ሉነሣ ይገባል ለሚለው ዲኝነቱ መሰረት ሆኖ የተያዘው የአሁን ተጠሪ የት/ቤቱን የሽያጭ ውል በሲዲማ ውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤቱ አድርጓል፤ አስመዝግቧል የሚለውን ነው። ይሁን እንጂ ይህ በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ፉት ውል የማድረግ ተግባር አስፈላጊነቱ ከውል አመሰራረት ጋር የተያያዘ፤ ውለ ተደርጓል፣ አልተደረገም? የሚለውንና በውለ ስለተካተቱት ዝርዝር ጉዲዩች (As to any terms of the contract) ወደ ፉት በተዋዋይ ወገኖች መካከል ክርክር እንዲይፈጠርና እንዲይነሣ ለማድረግ ሲባል የውል አደራረግን ሂደት የማረጋገጥ (authentication) መሆኑንና ውጤቱም በተዋዋይ ወገኖች መካከል ለሚነሳ ክርክር እልባት በመስጠት ላይ ያተኮረ ነው።
አንድን ንብረት በሽያጭ ውል ገዝቻለሁ፤ ስለሆነም በዚህ ንብረት ላይ ያለ እኔ ላላ ሶስተኛ ወገን መብት የለውም በማለት ማናቸውንም ሶስተኛ ወገን ለመመለስ ግን ት/ቤቱ በሚገኝበት ሥፍራ በሚገኘው ንብረትን መዝግቦ ለመያዝ ስልጣን በተሰጠው ማዘጋጃ ቤት የምዝገባ ሥርዓቱ ሉከናወን እንደሚገባ በንብረት ህጉ እና በውል ህጉ ከተመለከቱት አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች መረዲት ይቻላል።
ከዚህ አንፃር በእነዚህ በውል አደራረግ ሥርዓት ማሟያነት በቀረበው ውልን የማረጋገጥ ተግባር እና ሶስተኛ ወገንን ለመጠበቅም ሆነ ለመመለስ እንዱያስችል የተቀመጠውን የምዝገባ ሥርዓት (registration) ምንነትና ተግባር በውል ካለማጤን በሥር ፍ/ቤት ዲኝነት የተሰጠበት መሆኑን ተገንዝበናል።
No topics extracted.
እንዱሁም የአሁን ተጠሪ በንብረቱ ላይ አስወሰኜ በፍርድ ባለመብትነት ደረጃ ላይ እገኛለሁ በማለት የሚያቀርበው ክርክር እንደ አግባብነቱ ይኸው ንብረት ለፍርድ ማስፈፀሚያነት እንዱውል ለማድረግ በተከበረ ጊዜ የቀደምትነትን መብት ለማስረዲት የሚያግዘው ካልሆነ በቀር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 158 የተሰጠን የእግድ ትእዛዝ ለማስነሣት የሚያስችል አይደለም።
በዚህ ሁለ ምክንያት የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልቶች የዕግድ ትእዛዙ ሉነሳ ይገባል በማለት የሰጡት ትርጉም የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
51779 መጋቢት 20 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ ተሽሯል።
በአንፃሩ የሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 19703 ጥር 23 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ብይን ፀንቷል።
የአሁን ተጠሪ የዕግድ ትዕዛዝ ይነሣልኝ ሲል ያቀረበው ክርክርና ማስረጃ የህግ መሰረት ያለው አይደለም ብለናል።
በዚህ የፋዳራል ሰበር ሰሚ ችልት የተደረገው ክርክር ላስከተለው ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።