No summary available.
ጥር 03 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የሟች ወንድሙ ደምሴ ሚስትና ወራሾች
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ ቁጥር 49 ድንጋጌ መሰረት ክርክሩ እንዱቀጥል አቤቱታው የሚቀርብበትን የጊዜ ገደብ የሚመለከት ነው። ክርክሩ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካቾች አውራሽ አቶ ወንድሙ ደምሴ ሲሆኑ ተከሳሽ የአሁኑ ተጠሪ ናቸው። የክሱ ይዘትም ነሀሴ 20 ቀን 1997 ዓ.ም. የተጻፈና በአጭር ስርዓት እንዱታይ የቀረበ ሆኖ ዝርዝሩ፡- ተጠሪ ለሟች አቶ ወንድሙ ደምሴ ብር 440,000.00 (አራት መቶ አርባ ሺህ ብር) የያዘና በሚያዝያ 30 ቀን 1997 ዓ.ም. የሚከፈል ቼክ ሰጥተዋቸው አቶ ወንድሙ በሕይወት እያለ ግንቦት 02 ቀን 1997 ዓ.ም. ቼኩን ለባንክ ሲያቀርቡ በተጠሪ ሂሳብ ቁጥር ውስጥ በቂ ስንቅ የለውም ተብል ቼኩ የተመለሰላቸው መሆኑን ገልፀው ተጠሪ የቼኩን ዋጋ ከሚያዝያ 30 ቀን 1997 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድና ብር 1480 (አንድ ሺህ አራት መቶ ሰማንያ) ኮሚሽን ጋር እንዱከፍለ ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። ክሱ ከተመሰረተ በኋላ መስከረም 03 ቀን 1998 ዓ.ም. አቶ ወንድሙ ደምሴ ከዚህ አለም በሞት የተለዩ ሲሆን አመልካቾች መስከረም 25 ቀን 1998 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው ሟች መሞታቸውን በመግለፃቸው ወራሽነታቸውን አረጋግጠው ወደ ክርክሩ ለመግባት እንዱችለ ረዘም ያለ ቀጠሮ እንዱሰጣቸው በጠበቃቸው አማካኝነት ለፍርድ ቤቱ አመልክተው ፍርድ ቤቱ የከሳሽ ወራሾች የወራሽነት ማረጋገጫ ባገኙ ጊዜ መዝገቡን የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ተከትለው የማንቀሳቀስ መብታቸው ተጠብቆ ለጊዜው ተዘግቷል። ከዚህም በኋላ አመልካቾች ሚያዝያ 29 ቀን 2000 ዓ.ም. ክርክሩ እንዱቀጥል አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ክስም በስማቸው አሻሽለው አቅርበዋል። አሻሽለው ያቀረቡት ክስ ይዘቱ ከላይ የተመለከተውን የሚመስል ሲሆን ተጠሪ መከላከያ መልስ ካላቸው እንዱያቀርቡ ማስፈቀጃ እንዱያቀርቡ ተደረጎ ተጠሪ ቀርበው የመከላከያ ማስፈቀጃ አቅርበዋል። በዚህም ዋናው የቼኩ ተቀባይ ከነበሩት ከሳሾች አውራሽ ጋር የነበራቸውን የግል ግንኙነት መሰረት በማድረግ ገንዘቡ በጊዜው የተከፈለ መሆኑን ለማስረዲት እና በቼኩ ላይ የይርጋ ክርክር ለማቅረብ ክሱን ልከላከል ብለዋል። ፍርድ ቤቱም ተጠሪ መከላከያ እንዱያቀርቡ የፈቀደላቸው ሲሆን ተጠሪ ክሱ በይርጋ እንደሚታገድና ገንዘቡም ስለመከፈለ በመግለፅ ተከራክረዋል። እንዱሁም መዝገቡ በወራሾች የተከፈተው በሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተመለከተውን ጊዜ ባለመጠበቅ ነው በማለት ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤትም በን/ህ/ቁጥር 881(3) መሰረት የተነሳውን ይርጋ በተመለከተ ክሱ በአመልካቾች ወራሾች መቅረቡን፣ በአመልካቾች ክሱ የተሸሻለውም ወራሽነታቸውን አረጋግጠው ስለቀረቡ የአውራሻቸውን ስም በራሳቸው እንዱተኩ እንጂ አዱስ ክስ በማቅረብ ያለመሆኑን ገልጾ የይርጋ ተቃውሞውን ሳይቀበለው የቀረ ሲሆን የሥነ-ሥርዓት ሕጉን መሰረት በማድረግ የቀረበውን ተቃውሞም ከሳሾች (የአሁኑ አመልካቾች) ቀደም ብል አውራሻቸው የነበሩት አቶ ወንድሙ ደምሴ ክስ በተጠሪ ላይ ከአቀረቡ በኋላ መሞታቸውን እና መዝገቡም የእነርሱን ወራሽነት እስከሚረጋገጥ ድረስ ተዘግቶ ቆይቶ ከሳሾች ወራሽነታቸውን እንዲረጋገጡ መዝገቡን ማንቀሳቀሳቸውን ገልጸው ክሱን መቀጠላቸውንና ይህም በፍርድ ቤቱ ፈቃድ የተከናወነ መሆኑን ገልጾና የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕቁጥር 49(1) እና 55(3) ድንጋጌዎችን በዋቢነት በመጥቀስ ተቃውሞውን ውድቅ አድርጎታል። ከዚህም በኋላ ተጠሪ አለኝ ያለትን መከላከያ ማስረጃ እንዱያሰሙ ቀጠሮ ተይዞላቸው የሚያሰሙት ምስክር የላላቸውና ይህንኑ መብታቸውን የተው መሆኑን ለፍርድ ቤቱ በማረጋገጣቸው ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ ተጠሪን ለክሱ ኃላፉ በማድረግ ብር 440,000.00 (አራት መቶ አርባ ሺህ ብር) ቼኩ ለባንክ ቀርቦ ከተመለሰበት ከግንቦት 02 ቀን 1997 ዓ.ም. ጀምሮ ተከፍል እስካለቀ ድረስ ከሚታሰብ ከ9% (ዘጠኝ በመቶ) ወለድና ብር 1466.00 (አንድ ሺህ አራት መቶ ስድሳ ስድስት ብር) ኮሚሽን በመጨመር ለአመልካቾች እንዱከፍለ፣ የክሱን ወጪ ዝርዝር የማቅረብ መብታቸውን በመጠበቅ ወስኗል።
No topics extracted.
በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍርድ ቤቱ አመልካቾች በወራሽነታቸው ክሱን የቀጠለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 49(1) እና 55(3) ድንጋጌዎች ስር በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ነው ተብል ብይን የመስጠቱን አግባብነት በጭብትነት በመያዝ ጉዲዩን መርምሮ በወራሽነት ክርክር ለመቀጠል ጥያቄው በማናቸውም ምክንያት ቢሆን ከአንድ አመት ከስድስት ወር የማይበልጥ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 49(1)፣55(2) እና 33(3) ድንጋጌዎች ጥምር ንባብ እንደሚያስረዲ በመዘርዘር ይኸው የጊዜ ገደብ ከአለፈ በኋላ አመልካቾች ክሱን ማቅረባቸውን ማረጋገጡን ጠቅሶ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሽሮታል። በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ጸንቷል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም አመልካቾች በአውራሻቸው የቀረበውን ክስ ፍርድ ቤቱ በሰጣቸው ፈቃድ መሰረት ለጊዜው አዘግተው ወራሽነታቸውን በማረጋገጥ ክሱን የቀጠለና የወራሽነት ማስረጃ በሕጉ አግባብ የተሰጠው ግንቦት 28 ቀን 1998 ዓ.ም. ቢሆንም መብት አለኝ በሚል ወገን ተቃውሞ በመቅረቡ ምክንያት በፍርድ ቤት ታግድ ቆይቶ የተቃውሞ ክርክር ውድቅ ከሆነ በኋላ መጋቢት 04 ቀን 2000 ዓ.ም. የወራሽነት ማስረጃው ለአመልካቾች ሲሰጥ መዝገቡን ሚያዝያ 29 ቀን 2000 ዓ.ም. ማንቀሳቀሳቸው ተረጋግጦ እያለ ቀድሞ ባለቀ ጉዲይ ላይ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተመስርቶ ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 49/(1)፣55(2) እና 55(3) ድንጋጌዎች መሰረት በአንድ አመት ከስድስት ወር ይርጋ የታገደ ነው በማለት መወሰኑ ያለአግባብ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮ አመልካቾች የወራሽነት ማስረጃ ባገኙ ጊዜ መዝገቡን እንዱያንቀሳቅሱ በፍርድ ቤት ፈቃድ መዝገቡ ተዘግቶ ከቆየ በኋላ የወራሽነት ማስረጃው በተገኘ ጊዜ ተሻሽል ለቀረበው ክስ ሟች የሞቱበት ጊዜ መሰረት ተደርጎ ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 49(1)፣ 55(2) እና 55(3) መሰረት በይርጋ የታገደ ነው ተብል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በጽሁፍ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
በመሰረቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 49(1) ድንጋጌ መሰረት ክሱን ለመቀጠል መብት አለኝ የሚለ ወገኖች ዋናው ከሳሽ ወይንም ከሳሾች በሞቱ በአንድ አመት ውስጥ ክሱን ለመቀጠል እንዱፈቀድላቸው ሳያመለክቱ የቀሩ እንደሆነ የተጀመረው ክርክር ውድቅ እንደሚሆን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 49(2) ድንጋጌ በግልፅ ያሳያል። ይህ ድንጋጌ ክሱን ለመቀጠል መብት አለኝ የሚል ወገን ክሱን ለመቀጠል እንዱፈቀድለት ማመልከቻውን የሚያቀርብበትን የጊዜ ገደብ የሚመለከት ሲሆን ከሳሽ ወይም ከሳሾች በሞቱ በአንድ አመት ውስጥ ክሱን ለመቀጠል ሳያመለክቱ መቅረታቸው ከተረጋገጠ የተጀመረው ክርክር ቀሪ የሚሆንበትን አግባብ የሚደነገግ ሲሆን ከዚህ ጊዜ በኋላም ጥያቄው ሲቀርብ ተቀባይነት የሚገኝበት አግባብ መኖሩን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 55(2) ድንጋጌ ያሳያል። በዚህም መሰረት ከሳሹ ራሱ ወይም ከሳሽ የነበረው የሟቹ ንብረት አስተዲዲሪ ነኝ የሚል ባለአደራ ወይም የከሰረው ከሳሽ ንብረት አስተዲዲሪ የሆነ ሰው ወይም የዋናው ከሳሽ መብት ተላልፍልኛል የሚል ሰው ክሱ ቀሪ በሆነ ወይም በተሰረዘ በስድስት ወር ውስጥ የቀረበው ክስ እንዱቀጥል ወይም መሰረዙን እንዱነሳለት ለማመልከት የሚችል ስለመሆኑ የተደነገገ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ክሱ ቀሪ የሆነው ወይም የተሰረዘው በከሳሹ ጉድለት ያለመሆኑን የተረዲው እንደሆነ ይህ ምክንያት ስላደረሰው ኪሳራ ተገቢ መስል የታየውን ወስኖ የቀረው ወይም የተሰረዘው ክስ እንዱቀጥል ለማዘዝ የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 55(3) ድንጋጌ በግልጽ አስቀምጦታል። ይህ ድንጋጌ አቤቱታው ክሱ ቀሪ በሆነ ጊዜ ውስጥ በሚቆጠር ስድስት ወራት ውስጥ መቅረብ እንዲለበትና በበቂ ምክንያት መደገፍ እንዲለበት የሚደነግግ ሲሆን በቂ ምክንያት የሚለውን ሐረግ ግን መመዘኛው ምን እንደሆነ በግልጽ ያስቀመጠው ነገር የለም። ይሁን እንጂ በቂ ምክንያት አለ ወይስ የለም? የሚለው ጥያቄ አመልካቹ በተገቢው ጊዜ አስፈላጊውን ስርዓት ያልፈፀመበት ምክንያት ተገቢ የሆነ ምክንያት ስለነበረው ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን በመመልከት በፍርድ ቤቱ አዎንታዊ ምላሽ ከአገኘ በቂ ምክንያት አለ ብል ለመደምደም የሚችልበትን አግባብ የሚያሳይ ነው። በመሆኑም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 49 እና 55(2) እንዱሁም 55(3) ድንጋጌዎች ሲታዩ ክርክሩን ለመቀጠል የአንድ አመት ጊዜ ከአለፈ ጥያቄው ተቀባይነት የላለው መሆኑንና ይህ የጊዜ ገደብ በማለፍ መዝገቡ ከተዘጋ ወይም ክሱ ቀሪ ከሆነ በኋላ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ክርክሩ እንዱቀጥል ወይም ቀሪ የሆነ ክስ እንዱንቀሳቀስ በቂ ምክንያት ያለው መሆኑን አቤቱታ አቅራቢው ከገለፀ እና ፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅራቢው አስፈላጊውን ስርዓት ያልፈፀመበት ምክንያት ተገቢ በሆነ ምክንያት መሆኑን ከተረዲው ክርክሩ እንዱቀጥል ማድረግ የግድ የሚል መሆኑን የሚያስገነዝቡን ናቸው። ከዚህ አንፃር ሲታይ ከሳሽ በመሞቱ ምክንያት የተዘጋ መዝገብን ለማንቀሳቀስ ፍጹም የሆነ ይርጋ የአንድ አመት ስድስት ወራት ጊዜ ነው ቢባል እንኳ ፍርድ ቤት መዝገቡ ተዘግቶ የቆየበትን ጊዜ በማስላት ብቻ ጊዜውን መቁጠር ያለበት ሳይሆን በጊዜ ገደቡ ውስጥ ጥያቄውን ያቀረበው አቤቱታ አቅራቢ የቆየበትን ሁኔታ ሁለ አግባብነት ካላቸው ላልች የመሰረታዊ ህግ ድንጋጌዎችና አንድ ሰው ከሳሽ ለመሆን መሟላት ያለባቸውን የስነ ሥርዓት ሕግ መስፈርቶች ማየትን የግድ የሚል ነው።
በተያዘው ጉዲይ አመልካቾች ሟች ክስ መስርተው ከዚህ አለም በሞት ሲለዩ መዝገቡ እንዱዘጋላቸው ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ መዝገቡን እንዱዘጋላቸው የጠየቁት የወራሽነት ማስረጃ ይዘው እስከሚቀርቡ ለጊዜው መሆኑን፣ ፍርድ ቤቱም አመልካቾች የወራሽነት ማስረጃ ይዘው እንዱቀርቡና በስነ ስርአት ሕጉ መሰረት አቤቱታቸውን እንዱያቀርቡ ፈቅድላቸው መዝገቡ ተዘግቶ የቆየ ሲሆን አመልካቾች የሟች አቶ ወንድሙ ደምሴ ወራሽነታቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በፍርድ ቤት እንዱሰጣቸው ጥቅምት 17 ቀን 1998 ዓ.ም.
አቤቱታ አቅርበው ወራሽ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ውሳኔ የተሰጣቸው ሚያዝያ 29 ቀን 1998 ዓ.ም. መሆኑን፣ ይሁን እንጂ ይኸው የወራሽነት ማስረጃ በልላ ወራሽ ተቃውሞ ቀርቦበት ወዱያውኑ እንዲይሰጣቸው ታግድ ቆይቶ ማስረጃው መጋቢት 04 ቀን 2000 ዓ.ም. ከተሰጣቸው በኋላ ሚያዝያ 21 ቀን 2000 ዓ.ም. በፍርድ ቤቱ ፈቃድ የተዘጋው መዝገብ እንዱንቀሳቀስላቸው ጥያቄ ማቅረባቸው በፍሬ ነገር የተረጋገጡት ነጥቦች ናቸው። እንዱህ ከሆነ አቤቱታውን ማቅረብ የሚችለት የወራሽነት ማስረጃ ከተሰጣቸው በኋላ በመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 33(2) ድንጋጌ መንፈስ የሚያሳየን ነጥብ ነው። ምክንያቱም አንድ ሰው ከሳሽ ወይም ተከሳሽ መሆን የሚችለው ከሳሽ ወይም ተከሳሽ ለመሆን የሚያስችል መብት ወይም ጥቅም ያለው መሆኑ ሲረጋገጥ ነውና።
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 49 እና 55(3) ሥነ-ሥርዓታዊ ድንጋጌዎች እንደመሆናቸው መጠንም የይርጋ ጊዜው መቆጠር የሚጀምረው መቼ ነው? ከሚለው ጥያቄ አንጻር ጉዲዩ መታየት ያለበት ነው። ይህንኑ ጥያቄ ለመመለስ ደግሞ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1846 እና የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 48 ድንጋጌዎችን ይዘት መመልከት ተገቢ ይሆናል። በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1846 ድንጋጌ መሰረት የይርጋ ጊዜ መነሻው በመብት መስራት የሚቻልበት ጊዜ ነው። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 48 ድንጋጌ መሰረት ደግሞ ክርክሩ እንዱቀጥል የሚያስችለው መብት የማይቋርጥ ከሆነ የከሳሽ ወይም የተከሳሽ መሞት ክርክሩን እንዱቆም አያደርገውም በሚል ተቀምጧል። ከዚህ የስነ ስርዓት ድንጋጌ ውስጥ "ክርክሩ እንዱቀጥል የሚያስችለው መብት የማይቋረጥ ከሆነ" የሚለው ሐረግ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 826(2) እና ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1986 ድንጋጌ ጋር ተጣምሮ የሚታይ ነው።
በዚህም መሰረት በዚህ መብት አንድ ሰው ሉሰራ ይችላል ተብል የሚታሰበው ተገቢውን የወራሽነት ማስረጃ ከያዘ በኋላ ነው። ከዚህ አንፃር የተያዘውን ጉዲይ ስንመለከተው አመልካቾች የወራሽነት ማስረጃውን የያዙበት ጊዜ መጋቢት 04 ቀን 2000 ዓ.ም. በመብታቸው መስራት የሚችለበት ጊዜ ነው ተብል መያዝ የሚገባው ሲሆን ከዚህ ጊዜ በፉት ያለፈው ጊዜ ፍርድ ቤቱ ፈቅድና በተቃውሞ የተነሳ በወራሽነት ማስረጃ ላይ ክርክር ሲደረግ ያለፈ በመሆኑ በአመልካቾች ጉድለት እንደአለፈ ጊዜ ሉወሰድ የሚችል አይደለም። ይኸው ጊዜ ሟች ከሞቱበት ከመስከረም 4 ቀን 1998 ዓ.ም. ጀምሮ ከአለው ጊዜ ጋር ተቆጥሮ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 49፣ 55(2)፣55(3) ስር የተመለከተው የጊዜ ገደብ አልፎል ብል መደምደም ምክንያታዊነት ያለውና በሕግ የሚደገፍ ነው ብል ለማሰብ የሚቻል አይሆንም። ምክንያቱም የይርጋ ጊዜ ማለፍ አይነተኛ አላማም ዲተኛውን ተከራካሪ ወገን መቅጣት ከመሆኑ ጋር ተዲምሮ ሲታይ አመልካቾች የወራሽነት ማስረጃውን ለማግኘት ያለፈባቸው ጊዜ በዲተኝነታቸው ያለፈ ጊዜ ነው ልባል አይችልምና።
በመሆኑም ከመጋቢት 04 ቀን 2000 ዓ.ም. ጀምሮ ያለው ጊዜ ሲታይ አመልካቾች አቤቱታቸውን ያቀረቡት ሚያዝያ 21 ቀን 2000 ዓ.ም. መሆኑ በመረጋገጡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 49፣55(2) እና 55(3) ስር የተመለከተው የጊዜ ገደብ አልፎል ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም። በዚህም መሰረት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ቀጥል የተመለከትነው ኃላፉነትን የሚመለከተውን ጉዲይ ነው። ጉዲዩ የቼክ ጉዲይ ሲሆን ክሱ የቀረበው በአጭር ሥነ-ሥርዓት ሆኖ ተጠሪ በተከሳሽነታቸው የመከላከያ ማስረጃ ካላቸው ማስፈቀጃ እንዱያቀርቡ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቶ ተጠሪ መከላከያ ማስረጃ እንዲላቸው ለስር ፍርድ ቤት ገልጸው ፍርድ ቤቱ ተቀባይነት ያለው ሆኖ በማግኘቱ ተጠሪ የመከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርቡ ፈቅድላቸው የነበረ ሲሆን ተጠሪ ግን ማስረጃ የማሰማት መብታቸውን የተውት መሆኑን ለፍርድ ቤቱ በማረጋገጣቸው ፍርድ ቤቱ ተጠሪን ለክሱ ኃላፉ በማድረግ ውሳኔ ሰጥቷል። በመሆኑም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ተጠሪን ከክሱ ነፃ ያደረጉት በዚህ ችልት ተገቢነት የለውም የተባለውን የስነ ስርዓት ይርጋ መሰረት በማድረግ ሲሆን ፍሬ ጉዲዩ ላይ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱሰጥ ማድረጉ ተጠሪ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መከላከያ ማስረጃ የለኝም በማለት ከአረጋገጡት ነጥብ እና ከፍትሃ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ አይነተኛ አላማ አንጻር ሲታይ ተገቢ ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም ጉዲዩ የቼክ ሆኖ የመከላከያ ማስረጃ ያልቀረበበት እንደመሆኑ መጠን የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከደረሰበት መደምደሚያ ውጪ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሚመለከተው የፍሬ ነገርም ሆነ የሕግ ጥያቄ የላለ በመሆኑ በዚህ ችልት ውሳኔ የመጨረሻ እልባት መስጠቱ የሥ-ሥስርዓት ሕጉን የጠበቀ ሆኖ አግኝተነዋል።
በመሰረቱ ቼክ የተወሰነ ገንዘብ ለመክፈል ሐተታ የላለበት ትዕዛዝ የያዘና እንደቀረበም የሚከፈል ገንዘብን ተክቶ የሚሰራ ሰነድ ስለመሆኑ ከን/ሕ/ቁጥር 827/ሀ/እና 854 ድንጋጌዎች ይዘት የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። ቼክ መብቱ ከሰነደ ተነጥል የማይሰራበት፣ የቼኩ አውጪውም ቼኩ ላይ ለተፃፈው ገንዘብ አከፊፈል ኃላፉነት ያለበት መሆኑንም ከእነዚህ ድንጋጌዎችና ከን/ሕ/ቁጥር 840፣ 868(ሐ) እና 872 ድንጋጌ ይዘት የምንገነዘበው ነው። በመሆኑም ቼክ ባልተከፈለ ጊዜ አውጪውም ሆነ ፈራሚዎቹ ለቼኩ አከፊፈል ኃላፉዎች ይሆናለ። ቼክ በባሕሪው ገንዘብን ተክቶ የሚሰራና በቀላለ ወደ ተለያዩ ሰዎች ሉተላለፍ የሚችል በመሆኑም ማንኛውም መቃወሚያ ላቀርብበት አይችልም። ሕጉ ለይቶ በአስቀመጣቸው ጉዲዮች ካልሆነ በስተቀር የቼክ ክፍያ በማንኛውም ምክንያት ሉቆምና ሉታገድ አይችልም። በዚህም መሰረት በን/ሕ/ቁጥር 717 እና 850 ስር የተመለከቱት መቃወሚያዎች ባጋጠሙ ጊዜ አውጪው ወይም ፈራሚዎች ቼክ ሉከፈል የማይገባበትን መቃወሚያ ሉያነሱ ይችላለ። በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት በቼክ አከፊፈል ላይ መቃወሚያ ላቀርብ የሚችለው እዲ ከፊዩ ሰነደን በያዘው ሰው በሁለቱ የግል ግንኙነት ላይ በተመሰረቱት በሰነደ አፃፃፍ ፍርምና እንዱሁም በሰነደ ላይ በተፃፈት ቃልች ላይ፣ ፊርማን በማስመሰል የተሰራ፣ ችልታ ወይም ሰነደ ሲወጣ የውክልና ሥልጣን ባለመኖሩ ወይም ክስ ለማቅረብ አስፈላጊ የሆኑት ሁኔታዎች ባለመሟላታቸው የተነሱት መቃወሚያዎችን፣ አምጪው ይህን ሰነድ ባገኘበት ጊዜ እዲ ከፊዩን ለመጉዲት እያወቀ ያደረገው ከሆነ ነው።
በመሆኑም በድንጋጌው ተዘርዝረው በተገለፁ ሁኔታዎች በቼክ የተከሰሰ ሰው አንዲንድ መቃወሚያዎችን በማቅረብ ከእዲው ራሱን ነፃ ማድረግ እንደሚችል ሕጉ ሥርዓቱን ዘርግቷል።
በቼኩ የተከሰሰ ሰው የግል ግንኙነትን መሰረት ያደረገ መቃወሚያ ሉያነሳ የሚችለው ከአምጪው ጋር ያለውን ነው።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ተጠሪ ለቼኩ ኃላፉ ተብለው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠው ቼኩን አውጪ መሆናቸውና ቼኩ ባንክ ሲቀርብም በቂ ስንቅ የለውም ተብል በመመለሱና ተጠሪ በን/ሕ/ቁጥር 717 መሰረት አለኝ ያለትን መቃወሚያ ሉያስረዲ የሚችል ማስረጃ የላላቸው መሆኑ ተረጋግጦ ነው። በመሆኑም ውሳኔው ከላይ የተጠቀሱት የንግድ ሕግ ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገ በመሆኑ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም። በአጠቃላይ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 49፣55(2) እና 55(2) ድንጋጌዎችን በክርክሩ ሂደት ከተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች ጋር ባግባቡ ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሲሆን የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ግን ሕጉን የተከተለ ሆኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 05 ቀን 2002 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ መስከረም 26 ቀን 2003 ዓ.ም. የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሸሯል።
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 08 ቀን 2001 ዓ.ም.
የተሰጠው ብይንና በ6/6/2001 ዓ.ም. የተሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።