No summary available.
ህዲር 06 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አብደልቃድር መሐመድ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ እመቤት መኯንን- ጠበቃ ነቃጥበብ በየነ - አልቀረበም ተጠሪ፡- ወረዲ 2ዐ ቀ. 29 አ/ጽ/ቤት - አልተጠራም ተቃዋሚ፡- አቶ ዓይናዱስ ገዲሙ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
ገዲሙ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በተደገው ክርክር መሰረት የተሰጠው ውሳኔ የእኔን መብት የሚነካ በመሆኑ ሉለወጥ ይገባል በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ አቤቱታ በማቅረባቸው ነው። በዚህ መሰረትም የሰበር አመልካች በቀረበው የመቃወሚያ አቤቱታ ላይ መልስ እንዱሰጡ ተደርጎ ግራ ቀኙ በጽሁፍ ተከራክረዋል።
ከመዝገቡ መገንዘብ እንደሚቻለው አመልካች እና ተጠሪ በመሃከላቸው የነበረው የሆቴል ንግድ ድርጅት ቤት የኪራይ ውል ሉቋረጥ ይገባል፣ አይገባም ላይ ሲከራከሩ ቆይተዋል። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን ከሳሽ የነበሩት የአሁኗ አመልች፣ተከሳሽ ደግሞ ተጠሪ የሆነው የቀበላ አስተዲደር፣የአሁኑ የፍርድ ተቃውሞ አቅራቢና አቶ አንተሁነኝ ገዲሙ ናቸው። ጉዲዩን የተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተጠሪና የአሁኑ ተቃውሞ አቅራቢ ለአመልካች የንግድ ድርጅቱን እንዱያስረክቡ፣ የንግድ ድርጅቱን አከራይተው አመልካች ሉያገኙ ይችለ የነበሩትን ገቢም እንዱከፍለ በማለት ውሳኔ የሰጠ ሲሆን የቀበላ አስተዲደሩ እና የአሁኑ የፍርድ ተቃውሞ አቅራቢ ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ተጠሪ የሚያስተዲድረውን ቤቱን ከፈለገው ሰው ጋር የኪራይ ውል ሉያደርግ ይችላል እንጂ ከአመልካች ጋር ኪራዩን ሉቀጥል አይገባም ተብል የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሽሯል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርበው አመልካችና ቀበላ አስተዲደሩ ከተከራከሩ በኋላ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ ተሽሮ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ በመጽናቱ የአመልካች የድርጅት ቤት ተከራይነት መብት ከመረጋገጡም በተጨማሪ ድርጅቱን ቢያከራዩ ሉያገኙ ይችለ የነበረው ገቢ ሁለ ታስቦ እንዱከፈላቸው የገንዘቡ መጠን ተለይቶ ተወስኖላቸዋል። እንግዱህ የአመልካች የድርጅት ተከራይነት መብት በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የመጨረሻ ውሳኔ አግኝቷል። የአሁኑ ተቃዋሚ የእኔን መብት ይነካል የሚለትም ይህንን ውሳኔ ነው። የአሁኑ የፍርድ መቃወሚያ አቅራቢ አቤቱታውን ሉያቀርቡ የቻለት ለአመልካች ይሰጥ የተባለው የንግድ ድርጅት ቤት በይግባኝ ሰሚው የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለተቃዋሚ እንዱሆን ተወስኖላቸው አመልካች ተቃዋሚን በሚመለከት ከአሁኑ ተጠሪ ነጥለው ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ሶስቱ ዳኞች በሚሰየሙበት የሰበር ሰሚ ችልት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም ተብል የሰ/መ/ በሆነው ተዘግቷል በማለት ነው።
ከላይ እንደተገለጸው የተቃዋሚ አቤቱታ ወይም ክርክር በሰበር ሰሚ ችልት ሶስት ዳኞች በተሰየሙበት ችልት እርሳቸውን የሚመለከት የአመልካች የሰበር አቤቱታ የመጨረሻ ውሳኔ አግኝቶ እያለ አምስቱ ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችልት ደግሞ ተቃዋሚ የክርክሩ ተካፊይ ሳይሆኑ መብታቸውን የሚነካ ውሳኔ ሰጥቷል በሚል ነው። ይህም ተጣርቶ እንዱወሰንላቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት አቤቱታቸውን አቅርበዋል። ይሁን እንጂ የፍርድ ተቃውሞ የሚቀርበው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 ስር በተመለከተው ሥርዓት ሲሆን አቤቱታው የቀረበለት ፍርድ ቤትም ጉዲዩን በማስረጃ አጣርቶ የሚወሰነው ይሆናል። የሰበር ችልቱ ፍሬ ነገሮችን በማስረጃ የማጣራትም ሆነ ማስረጃን የመመዘን ሥልጣን የለውም።
በእግርጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 358 መሰረት የሚቀርበው አቤቱታ የሚስተናገደው ለመቃወሚያው መነሻ የሆነውን ውሳኔ ለሰጠው ፍ/ቤት ነው። ይሁንና አቤቱታው የሚጣራው ወይም የሚስተናገደው ማንኛውም ክስ በሚስተናገድበት ሥርዓት በመሆኑ እና ይህም ማስረጃ መስማትንና ማስረጃውን መዝኖ ውሳኔ መስጠትን የሚጠይቅ በመሆኑ በሕግ አተረጓጎም ረገድ የተፈጸመውን ስህተት የማረም ስልጣን በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት ለተሰጠው በዚህ የሰበር ችልት የሚታይ አይሆንም።
ቀደም ሲል እንደተገለጸው ክርክሩ የተጀመረውና የሰበር ችልቱም ያፀናው በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በመሆኑ መቃወሚያው መቅረብ ያለበት ለዚሁ ፍ/ቤት ነው ልባል ይችላል። ነገር ግን በዚህ ፍርድ ቤት የፍርድ ተቃውሞ አቅራቢ የክርክሩ ተካፊይ ሁነው ተረቺ የነበሩ ሲሆን በአገሪቱ የፍርድ ሰጪ አካላት የመጨረሻ አካል በሆነው ሰበር ሰሚ ችልትም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ውጤቱ ከመጽናቱም በተጨማሪ አፈጻጸሙም እንዱቀጥል በሰበር መዝገብ የመጨረሻ ውሳኔ ተሰጥቶበታል። በመሆኑም ምናልባት ተቃዋሚ አለኝ የሚለትን መብት ለማስከበር ይችለ ዘንድ መብቴን ተጋፍቶአል በሚለት ሰው ላይ በስሙ ክስ መመስረት የሚችለ ከሚሆን በስተቀር ቀድሞ በዚህ መዝገብ የተሰጠውን ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 ለማስተናገድ የሚቻልበትን ሥርዓት ስላላገኘን ተቃዋሚ ያቀረቡትን አቤቱታ በዚህ ሰበር ችልት ደረጃ የሚስተናገድ አይደለም ብለናል። ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ ብለናል።
No topics extracted.