No summary available.
ጥቅምት 22 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አመልካች፡- አቶ ገ/እግዚአብሓር ከበደው - ጠበቃ አንተነህ ተካልኝ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ት ሰላማዊት ወ/ገብርኤል - የቀረበ የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በመቀላ ቀዲማዊ ወያኔ ወረዲ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው።
የክሱ መሰረትም ሟች እናታቸው ወ/ሮ ድንቅነሽ ድምጹ ከአመልካች ጋር በባልና ሚስትነት ሲኖሩ በጋራ ያፈሯቸው የማይንቀሳቀስና የሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ጠቅላላ ድምሩ ብር 426,900.00 (አራት መቶ ሃያ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር) ከሆነው የእናታቸውን ድርሻ ግማሽ ብር 213,450.00 (ሁለት መቶ አስራ ሶስት ሺህ አራት መቶ ሃምሳ ብር) እንዱከፍሎቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አመልካችም ጉዲዩ በፍርድ ቀድሞ ማለቁንና በድጋሚ ዲኝነት የማይጠይቅበት መሆኑን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አንስተው ከመከራከራቸው በተጨማሪ የዋና ጉዲይ ክርክርም አቅርበዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የወረዲው ፍርድ ቤትም አመልካችን ለክሱ ኃላፉ በማድረግ ተጠሪ በክሱ የጠየቁትን ግማሽ ገንዘብ ከአራት ወንድሞቻቸው ጋር እንዱወስደ በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለመቐላ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ አመልካችን ለክሱ ኃላፉ ተብል የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል በማጽናት የገንዘቡን መጠን ብቻ ወደ ብር 123,450.00 (አንድ መቶ ሃያ ሶስት ሺህ አራት መቶ ሃምሳ ብር) ዝቅ አድርጎ ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም በጉዲዩ ላይ ሁለቱ የበታች ፍርድ ቤቶች የተለያየ ውሳኔ የሰጡበት በመሆኑ በይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መደበኛ ችልት ከሚቀርብ በስተቀር ለሰበር ችልቱ ላቀርብ የሚችል አይደለም በሚል ምክንያት መዝገቡ ተዘግቶባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ብቁ አይደለም በማለት የሰጠውን ትዕዛዝ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በጉዲዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠበት አይደለም በማለት መዝገቡ የመዘጋቱን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ይህ ችልትም በዚህ ነጥብ ላይ ግራ ቀኙን በጽሐፍ እንዱከራከሩ አድርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ትእዛዝ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ክርክሩ የነበረው በሁለት በተመሳሳይ ክልል ኗሪ በሆኑ ግለሰቦች ሲሆን ክርክሩም የንብረት ግምት ክርክር መሆኑን፣ ክርክሩ የተጀመረው በወረዲ ፍርድ ቤት ሁኖ ወረዲ ፍርድ ቤት አመልካችን ለክሱ ኃላፉ በማድረግ ተገቢ ነው ያለውን ግምት እንዱከፍለ ወስኖ በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው ይኸው ፍርድ ቤትም አመልካች ለክሱ ኃላፉ ተብል መወሰኑን እንዲለ በመቀበል የኃላፉነት መጠኑን ብቻ በማሻሻል መወሰኑን ነው። እንግዱህ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩ ሲቀርብለት የመጨረሻ ፍርድ አልተሰጠበትም በማለት መዝገቡን የዘጋው በሁለቱ የበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ የተለያየ ነው በማለት ነው።
እኛም የዚህኑ ትዕዛዝ ተገቢነት ተሻሽል ከወጣው የትግራይ ብሄራዊ ክልል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 49/1994 አንቀፅ 16(ለ) ድንጋጌ አኳያ ተመልክተነዋል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ባለባቸው የክልል ጉዲዮች የሰበር ስልጣን የሚኖረው በወረዲ ፍርድ ቤት ተወስነው በይግባኝ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ወይም በጠቅላይ ፍርድ ቤት ያለቁ ጉዲዮች መሆናቸው ሲረጋገጥ መሆኑን ተጠቃሹ ድንጋጌ ያሳያል። የድንጋጌው ይዘትና መንፈስ ሁለት ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ ተመሳሳይ ውሳኔ ከሰጡ ውሳኔው የመጨረሻ እንደሚሆንና በውሳኔው ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አለበት የሚል ወገን ደግሞ ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታውን በአዋጁ አንቀጽ 17 መሰረት አዘጋጅቶ እንደሚያቀርብ ነው። በመሆኑም በክልለ የማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 93/1997 አንቀፅ 30(2(ሀ)) ስር የተመለከተው እንደተጠበቀ ሁኖ የበታች ፍርድ ቤቶች ተመሳሳይ ውሳኔ የሰጡበት ጉዲይ በድጋሚ ይግባኝ የላለውና ላቀርብ የሚችለው ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ብቻ መሆኑን ነው።
በተያዘው ጉዲይ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ለመቅረብ ብቁ አይደለም በማለት መዝገቡን የዘጋው የበታች ፍርድ ቤቶች የተለያየ ውሳኔ በጉዲዩ ላይ ሰጥተዋል በሚል ምክንያት ነው። ይሁን እንጂ የአመልካችን ኃላፉነትን በተመለከተ ሁለቱም ፍርድ ቤቶች ተመሳሳይ በሆነ ሁኔታ የወሰኑ ከመሆናቸውም በላይ ይግባኝ አቅራቢም የአሁኑ አመልካች የነበሩ በመሆኑና የይግባኝ መብት የተፈቀደው ከአንድ ጊዜ በላይ ስለመሆኑ የሚያመላክት የክልለ የሕግ ማዕቀፍ በላለበት ሁኔታ (ከይግባኝ አቀራረብ ሥርዓት አንፃር) በጉዲዩ ላይ የተለያየ ውሳኔ ተሰጥቷል ለማለት የሚቻልበት አግባብ የለም። በመሆኑም በጉዲዩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ የተሰጠበትና ላታይ የሚችለውም በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ሁኖ እያለ መዝገቡ መዘጋቱ ከተሻሻለው የክልለ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 49/1994 አንቀጽ 16(ለ) እና 17 ድንጋጌዎች እና ከይግባኝ መብት አንፃር መሰረታዊ የሆነ የሥነ ሥርዓት ሕግ ግድፈት የተፈጸመበት ሁኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ሐምል 22 ቀን 2002 ዓ.ም. የተሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በጉዲዩ ላይ ሁለት የበታች ፍርድ ቤቶች ተመሳሳይ ውሳኔ የሰጡበት በመሆኑና የመጨረሻ ውሳኔ ያረፈበት በመሆኑ አመልካች ጉዲዩን ለማቅረብ የሚችለት ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ነው በማለት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት መሆን ያለመሆኑን በመመርመር ተገቢውን ትእዛዝ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 341(1) መሰረት መልሰንለታል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.